Get Mystery Box with random crypto!

#ጥልቅ_እይታ (ናብሪ >ራፊንሀ) ~የክለባችን አመራሮች ይሄንን የ 25 አመት ብራዚላዊ የቀኝ ክን | የኛ ARSENAL

#ጥልቅ_እይታ (ናብሪ >ራፊንሀ)

~የክለባችን አመራሮች ይሄንን የ 25 አመት ብራዚላዊ የቀኝ ክንፍ ተጨዋች (ራፊንሀ) ለማዘዋወር የፈለጉት በቀኝ ክንፍ አጥቂ ቦታ ላይ ከ ኒኮላስ ፔፔ በተሻለ ጥበበኛውን እንግሊዛዊ ቡካዮ ሳካን የመፎካከር አቅም አለው ፣ ወይም ደሞ ለታዳጊው ሳካ የበለጠ ተነሳሽነት በመፍጠር እራሱን ለበለጠ ድል እና ስኬት ያዘጋጃል አንዳንዴም ሳካ ጉዳት ካጋጠመው ወይም እረፍት ሊሰጠው ካስፈለገ ራፊንሀ [ Squad Player] ይሆናል ብለው ስላሰቡ ነበረ።

~እኔ በግሌ ራፊንሀ ቡካዮ ሳካን ተቀያሪ ወንበር ላይ የማስቀመጥ ችሎታ አለው ብየ አላስብም ፣ ሲጀመር እነ ኤዱም ያዩት የልጁን እምቅ ችሎት [ potential ] ነው እንጂ ተጨዋቹ በ ሊጉ ላይ እራሱን prove ያደረገ ተጨዋች ሆኖ አይደለም ፣ በሌላ አነጋገር ራፊንሀ ወደ አርሰናል ቤት መጥቶ በአንድ የውድድር አመት 15 እና ከዚያ በላይ ጎል እንደማያገባ ግልፅ ነው። በእኔ እይታ እራሱን prove ላላደረገ [ Squad Player ] ከ 50 ሚልየን ፓውንድ በላይ ማውጣት ተገቢ አይደለም።

~ባርሴሎናም እንደ አርሰናል ሁላ የዚህን ተጨዋች potential እና bright future በማየቱ ሊያዘዋውረው ፈልጎ ነበር ነገርግን የካታሎኒያው ሀያል ክለብ ባለበት የገንዘብ ችግር ምክንያት ከዚህ ዝውውር እራሱን ካገለለ ሰነባብቷል። ሊድስ ይሄንን ብራዚላዊ ተጨዋች እንዲህ ዋጋው እንደጦፈለት ሳይሸጠው ይሄ የዝውውር መስኮት እንደማይዘጋ ቀድሞ የተገነዘበው ክለባችን ያለፉትን ጥቂት ሳምንታት ያለማንም ተፎካካሪ ከ ዌስት ዮርክሻየሩ ክለብ ጋር ሲደራደር ቆይቷል። ሌላ ፈላጊ ክለብ እስካልመጣ ድረስም ይሄንን ብራዚላዊ በ 50 ሚልዮን የግሌ አደርገዋለውም ብሎ አስቦ እንደነበረ እሙን ነው።

~ነገርግን ባለቤት አልባ እንሆናለን ፣ ክለባችን ሊፈርስ ነው በቃ አለቀልን ብለው በተጨነቁበት ሰአት በነፍሳቸው የደረሰላቸው አሜሪካዊው ቢልዮኔይር ቶድ ቦሊ ከወዲሁ በቼልሲ ደጋፊዎች ልብ ውስጥ በጥልቀት ለመግባት እና የምእራብ ለንደኑን ክለብ በሚቀጥለው የውድድር አመትም ተፎካካሪነቱን ጠብቆ ማቆየት ያስችለው ዘንድ ቆርጦ እንደተነሳ ግልፅ ነው። ለዚህም ይመስላል በአንገብጋቢ ሁኔታ የክንፍ አጥቂ የሚፈልገው ቼልሲ ከየት መጣ ሳይባል በድንገት በ ራፊንሀ ዝውውር ውስጥ በመግባት 65 ሚልዮን + የተጫዋቹን ጥቅማጥሞች እና ሌሎችም በርካታ ክፍያዎችን በመክፈል የ ሊድስን ቀቢፀ ተስፋ እውን ለማድረግ ወስኗል።

~አሁንም ግን ክለባችን ለ ቡካዮ ሳካ ተቀያሪ የሚሆን የክንፍ አጥቂ መፈለጉን አላቆመም ፣ እንደ ራፊንሀ ከችሎታው በላይ ገንዘብ የተቆለለበት ሳይሆን Fair የሆነ ዋጋ የተቆረጠለትን ተጨዋች እስከ 50 ሚልዮን ፓውንድ በማውጣት የመግዛት ፍላጎት አለው። አሁንም ቢሆን እንደ ሰርጅ ናብሪ አይነት እራሳቸውን በትልቅ ደረጃ ላይ prove ያደረጉ የክንፍ አጥቂዎች በዝውውር ገበያው ላይ አሉ። ናብሪ ከ ቡንደስሊጋው ሀያል ክለብ ባየርን ሚውኒክ ጋር የሚያቆየውን አዲስ ውል አልፈርምም በማለቱ እሰጣ ገባ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። ክለባችን አርሰናልም ይቺን ምርጥ አጋጣሚ በመጠቀም ከ 50 ሚልዮን ባነሰ ዋጋ ይሄንን የ 26 አመት የቀድሞው የክለባችን ተጨዋች ወደ ቤቱ ሰሜን ለንደን ቢመልሰው መልካም ነው እላለሁ።

| @Dav_Gooner

VIA #ETHIO_ARSENAL