Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ዘይት ደብረ መድኃኒት አንቀፀ መድኃኒት ሰንበት ትምህርት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ anketsemedanitsnbttimhirtbet — የደብረ ዘይት ደብረ መድኃኒት አንቀፀ መድኃኒት ሰንበት ትምህርት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ anketsemedanitsnbttimhirtbet — የደብረ ዘይት ደብረ መድኃኒት አንቀፀ መድኃኒት ሰንበት ትምህርት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @anketsemedanitsnbttimhirtbet
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 198
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የደብረ ዘይት ደብረ መድኃኒት አንቀፀ መድኃኒት ሰንበት ትምህርት ቤት ነዉ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/ቀኖና ዶግማ የጠበቁ ማንኛዉም አሰተማሪ ጹሑፎች ይቀረቡበታል የየዕለቱ ስንክሳሮች ይተላለፉበታል ለመቀላቀል @Anketsemedanitsnbttimhirtbet ይጠቀሙ ሰለተቀላቀሉን በእግዚአብሔረ ሰም እናመሰግናለን።
ለበለጠ መረጃ ሀሳብ አሰታያየት ጥያቄ ካሎት
@Anketse_medanit የሚለዉን ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-24 13:16:17 + ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን? +

አንድ ሁልጊዜም መማር የማይታክታቸው አባት ነበሩ:: በጣም የተማሩ ቅኔ አዋቂ መጻሕፍት የመረመሩ ሊቅ ቢሆኑም ሁሌም ከአትሮንስ ሥር የማይጠፉ ተማሪ ነበሩ:: ይህንን ልምዳቸውን ያየ አንድ ሰው "እርስዎ ብዙ የተማሩና ያነበቡ ሰው ነዎት ከዚህ በኁዋላ ማረፍ ሲገባዎት ለምን ጊዜዎን በትምህርት ያጠፋሉ?" አላቸው:: እርሳቸውም "መልአከ ሞት መጥቶ ወደ ፈጣሪ በወሰደኝ ጊዜ 'የት አግኝተህ አመጣኸው?' ሲባል ከአትሮንስ ሥር ቁጭ ብሎ የአንተን ቃል ሲሰማ አገኘሁት ብሎ እንዲነግርልኝ ነው" አሉ::

መልአከ ሞት አሁን በዚህ ሰሞን መጥቶ ቢወስድህ ምን ሲያደርግ አገኘሁት የሚል ይመስልሃል? ሲጸልይ? ሲመጸውት? ሲመርቅ? ሰዎችን በፍቅር ቃል ሲናገር? ሲያማ? ሲሳደብ? ሲያስታርቅ? ሲያጣላ? እውነትም የእኚህ አባት ጭንቀት እጅግ ተገቢ ጭንቀት ነበር::

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን "እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን" ብላ በቅዳሴዋ የምትጸልየው በሞት የምወሰድበት ወቅት ምናልባትም ክፉ የምንሠራበትና ፈጣሪን የምንክድበት ጊዜ እንዳይሆን ነው:: "ሽሽታችሁ በክረምትና በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ" እንዲል እንደ ክረምትና ሰንበት ሥራ አቁመን ከበጎ ምግባር በራቅንበትና በሰነፍንበት ሰዓት እንዳንሞት እንጸልያለን::

ሌላው ቅዱስ አባት ነባቤ መለኮት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ደግሞ ከሞቱ በኃላ ስለሚከሰተው የመጀመሪያ ክስተት ሲናገር
"ስሞት ዓይኔን በጣቶቹ የሚከድልኝ ማን ይሆን?" (Who will lay his fingers upon my eyes when I die?) ብሎአል:: (On His own life 43)

ምናልባት "ስሞት ዓይኔን ማንስ ቢከድነው ምን ለውጥ አለው?" ብለን እናስብ ይሆናል:: ሆኖም የመጨረሻዋን ቅጽበት የዓይናችን መከደን ጉዳይና የሚከድነው ሰው ማንነት ትልቅ ዋጋ ያለው ነው::

እግዚአብሔር በበጎነታቸው ለወደዳቸው ቅዱሳን ከሚመርቀው ምርቃት አንዱ "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" የሚል ነበር::

ያዕቆብን እንዲህ ሲል መረቀው
"ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ : ከዚያም አወጣሃለሁ
ልጅህ ዮሴፍም እጁን በዓይኖችህ ላይ ያኖራል"
ዘፍ 46:4

የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ መሰናበት "ሲቀብር ይቆርጥለታል" ከሚባለው ልማዳዊ ብሂል በላይ ፍጹም ዕረፍት የሚሰጥ ስንብት ነው:: ምንም ስቃዩና ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆንም የመጨረሻዋን ሕቅታ ሰምቶ የምንወደውን ሰው ዓይን ከድኖ የመሸኘትን ያህል የሕሊና ዕረፍት የለም::

ለአባት "ልጆችህ ዓይንህን ይከድናሉ" መባል ምርቃት የመሆኑን ያህል ለወላጆች የልጅን ዓይን መክደን ግን እጅግ ከባድ ኀዘን ነው:: ሆኖም ምንም ኀዘኑ ጥልቅ ቢሆን ልጅን ዓይን ከድኖ መሰናበት ኀዘንን የሚያቀልል ስንብት ነው:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በአንድ ልጃቸው ሞቶ በኀዘን በተሰበሩ ወላጆች ቤት ገብቶ ይህንን የማጽናኛ ቃል ተናግሮ ነበር :-
"ጻድቁ ኢዮብ የልጆቹን ዓይን ለመክደንና አፋቸውን ለመግጠም ሰውነታቸውንም ለማስተካከል እንክዋን አልታደለም ነበር:: እናንተ ግን ቢያንስ የልጃችሁን የመጨረሻ ቃል ሰምታችኃል ዓይኖቹንም ከድናችኃል አፉንም ገጥማችኃል:: እናንተ ዐሥር ልጆቹን ካጣው ኢዮብ በላይ ስለምን ታዝናላችሁ?"

ቅዱስ ጎርጎርዮስ "ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?" አለ:: ይህንን አስበነው እናውቅ ይሆን? ማን እንዲሸኘን እናስብ ይሆን? ቅድስት መቅሪና ስትሞት ወንድምዋ ጎርጎርዮስ ዓይንዋን እንዲከድንላት ትመኝ ነበር:: ሆኖም በሞተችበት ዕለት ሳትሞት በፊት በወሰዳት እንቅልፍ ምክንያት ዓይንዋ ተከድኖ ነበር:: (St.Gregory of Nyssa, On the life of St Makrina)

ቅዱስ ፍላብያኖስ ዘአንጾኪያም እኅቱ ዓይንዋን እንዲከድንላት ስትመኝ ኖራ በሞተች ዕለት እርሱ ለጸሎት ወደ ቁስጥንጥንያ ሔዶ እንደነበረ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ተናግሮአል::

ለአንዳንድ ቅዱሳን ደግሞ ማን መጥቶ ዓይናቸውን እንደሚከድን አስቀድሞ ፈጣሪ ይገልጥላቸው ነበር:: ከሃያኛው ክፍለ ዘመን ቅዱሳን አንዱ የሆኑት ፓትርያርክ ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ለአንድ ወጣት ጦቢት የሚል ቅጽል ስም አውጥተው ይጠሩት ነበር:: ለምን ጦቢት እንደሚሉት ባያውቅም ስሙን ግን አውቆ በጠሩት ቁጥር አቤት ይል ነበር:: ፓትርያርኩ በሞቱበት ዕለት ይህ ወጣት እግር ጥሎት ቀድሞ የደረሰው እርሱ ነበር:: ዓይናቸውን የከደነና አፋቸውን የገጠመው የዕረፍታቸውን ዜናም ለሌሎች ያሳወቀው ቀብሩንም ያስፈጸመው እርሱ ነበር:: ይህ ከሆነ በኁዋላ "ጦቢት" ብለው የሚጠሩበትን ምክንያት አስታውሶ መጽሐፈ ጦቢትን ሲያነብ ይህንን ጥቅስ አገኘ :-
"ጦቢትም እንዲህ አለ :- በነነዌ አደባባይ የሞተ ሰው ሳገኝ እቀብረው ነበር" ጦቢ 1:4
ጻድቁ ይህ ወጣት እንደሚቀብራቸው አውቀው ራሱን ለአደጋ አጋልጦ ድሆችን ይቀብር በነበረው በጦቢት ስም ይጠሩት ነበር::
እኔና አንተ ግን የማናውቅ ስለሆንን እንዲህ እንላለን
"ስሞት ዓይኔን የሚከድንልኝ ማን ይሆን?"

@Anketsemedanitsnbttimhirtbet
72 viewsAbay Getaneh, 10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 15:17:12 "አስቀድማችሁ መንግስቱትንና ጽድቁን ፈልጉ "
ማቴ 6÷33
............. ........... ................. ........... ......
" ስለዚህ እላችኋለሁ፥ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?" አላቸው
ማቴ 6:25

ጌታችን ይህንን ትምህርት የሰው ልጆች ከሁሉ የቱን ማስቀደም እንዳለባቸው ያስተማረው ትምህርት ነው፡

አንድም ከሁለቱ የቱን ማስቀደም እንዳለባቸው ያስተማረው ነው፡፡

ከሁለቱ የተባለው
1ኛ ከሚያልፈው ዓለምና ከማያልፈው ዓለም

፡-የሚያልፈው ዓለም ይህኛው አሁን የምንኖርበት ዓለም ሲሆን፡፡
፡-የማያልፈው ዓለም ፡- መንግስተ ሰማያት ነው፡፡

2ኛ ከሥጋና ከነፍስ ማለት ነው፡፡
ይህም ስጋ ፡-በሚያልፈው ዓለም ውስጥ ምቾት ተድላ ደስታን ትናፍቃለች ጊዜአዊ ደስታና እርካታ ላይ ታመዝናለች ::
ነፍስ፡- ይህኛው ዓለም ጠፊ ኃላፊ መሆኑን ተገንዝባ የማያልፈውን ያኛውን ዓለም ትናፍቃለች፡፡

ይህንንም ጌታችን በጥልቅ መለኮታዊ ምስጢር ሲያስረዳን፡-

"ለነፍሳችን ምን እንበላለን ምን እንጠጣለን ለሥጋችን ምን እንለብሳለን ብላችሁ አታስቡ " ይለናል::

ምስጢራዊ ትርጉሙ፡- መብል መጠጥን ለነፍስ ሰጥቶ ተናገረ ስለምንድ ነው ብንል የበሉት የጠጡት ደም ይሆናልና ነው በዚህም ምክንያት ነፍስ ከስጋ ጋር ተዋህዳ ትኖራለችና " እስመ ነፍስ ተኃድር በደም " እንዲል፡፡

ልብስን ለስጋ ሰጥቶ ተናገረ ምንም የምታፍር ነፍስ ብትሆን አጊጦ ከብሮ የሚታይ ሥጋ ነውና፡፡

አንድም ካለመኖር ወደመኖር ነፍስን አምጥቼ ሥጋን ከአራቱ ባህርያት አዋሕጄ የፈጠርኳችሁ ለእናንተ ምግብ ልብስ እንዴት እነሳችሗለሁ ሲለን ነው፡፡

አንድም ነፍስን ካለችበት አምጥቼ ሥጋን ካለችበት አስነስቼ ሗላ በመንግስተ ሰማያት መንፈሳዊ ምግብን የምመግባችሁ ዛሬ ለእናንተ ምግብ ልብስ እነሳችሗለሁን ሲለን ነው፡፡

እናንተግን ከሁሉ አስቀድማችሁ መንግስቱንና ጽድቁን ፈልጉ ሊለን ይህን ተናገረን ምክንያቱም የምስጢሩ ፍጻሜ ለነፍሳችሁ ምን እንበላለን ካላችሁ "#ሥጋዬን" ምን እንጠጣለን ካላችሁ ደሜን አንድም ለስጋችሁ ምን እንለብሳለን ካላችሁ #እኔን ሲለን ነው ምክንያቱም የምንራቆተው ከእርሱ ስንለይ መሆኑን ሲነግረን::
ይህንን ሁሉ በምሳሌ ካስረዳን በሗላ እናንተ መጨነቅ ሳይሆን ይህንን ፈልጉ ብሎ ተናገረን እሱም፡- "መንግስቱንና ጽድቁን"

መንግስተ ሰማያት የተባለ ክርስቶስ ፈልጉ ለነፍሳችሁ እረፍት ታገኛላችሁና፡፡

ጸሀየ ጽድቅ ክርስቶስ ፈልጉ ሥጋዊ ፍላጎትን ንቃችሁ ስለ ስሙ ስደትን ትመርጣላችሁና፡፡ " ስለጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና " ማቴ 5÷10 ሲለን ነው፡፡

አንድም አስቀድማችሁ ሃይማኖትን ምግባርን ፈልጉ
አንድም ልጅነትን መንግስተ ሰማያትን ፈልጉ ሲለን ነው፡፡ ይህ ማለት የዚህ ዓለምስ ነገር ሁሉ በእራት ላይ ዳረጎት እንዲጨመር ይጨመርላችሗል፡፡

አንድም ሰለነገ አትጨነቁ ይለናል ይልቁንስ እንዲህ ይለናል "ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።"
ሉቃስ 12:22

ከመጨነቅ ይልቅ ይህንን አድርጉ ሲለን ነው ፡-

" በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።"
ፊል 4:6
ምክንያቱም ይለናል ቅዱስ ጴጥሮስ፡-

" እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።"
1ኛ ጴጥ 5:7
ስለዚህ ክርስቲያን ከምድራዊው ይልቅ ሰማያዊውን ከሚያልፈው ይልቅ የማያልፈውን የሚያስቀድም በምድራዊ ህይወቱ መላካዊ ባህርይን ተለማምዶ በዚች በምታልፈው ዓለም የማያልፈው ዓለም ለማግኘት ከኃላፊው ከጠፊው ቁስ በፊት ጽድቁንና መንግስቱን ሲያስቀድም የሚያስፈልገው ነገር እንደሚሰጠው በማመን ከጭንቀት ተላቆ ተስፋ ክርስቶስ ለብሶ እንዲኖር የተሰጠ ትምህርት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
@Anketsemedanitsnbttimhirtbet
87 viewsAbay Getaneh, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 12:20:16 +++ እግዚአብሔር ሲቀጣን ... +++

"[አንድ] ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡

"እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገ. 36
---------------
146 viewsAbay Getaneh, 09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 13:08:45 + አልፋና ኦሜጋ ክርስቶስ +

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ‘አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ’ አለ:: A እና Ω የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ፊደላት ናቸው፡፡ ጌታችን መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ሲል ከዓለም መፈጠር በፊት የነበርሁ ዓለምንም አሳልፌ ለዘላለም የምኖር እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡

ወደ ጥልቁ መለኮታዊ ዘላለማዊነት ሳንገባ ያለንባትን የምድርን ታሪክ ይዘን ብቻ እንዲሁ ካየነው ክርስቶስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው፡፡ ‘እግዚአብሔር ‘በመጀመሪያ’ ሰማይና ምድርን ፈጠረ’ ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አብ ‘መጀመሪያ’ በተባለው በልጁ በክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሮአል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህችን ምድር በግርማው መጥቶ የሚያሳልፋትም እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለምድርም መጀመሪያዋና መጨረሻዋ ክርስቶስ ነው፡፡

መቼም እኛም ከምድር ተፈጥረናልና ይህ ነገር እኛንም ሳይመለከተን አይቀርም፡፡ ነቢዩ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ እንዳለ በእናታችን ማሕፀን የሳለንና በኋላም ለእኛ ምጽዓት በሆነችው የሞታችን ዕለት ነፍሳችንን ወደ እርሱ የሚወስዳት መጀመሪያችንና መጨረሻችን እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡
ይህ ግን ለሁሉ የማይቀር ነው፡፡ ወዳጄ ክርስቶስን አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ታምናለህ፡፡ በአንተ ሕይወት ውስጥ ግን ክርስቶስ እውነት መጀመሪያና መጨረሻ ነው?

ለአንዳንዶች ክርስቶስ መጀመሪያቸው ነበር፡፡ ዴማስ ለክርስቶስ አልፋ ብሎ ዘምሮለት ነበር፡፡ ከጳውሎስ ጋር ሆኖ ለፊልሞና ሰላምታ ሲልክም ነበረ፡፡ በኋላ ግን ዓይኑ በተሰሎንቄ ውበት ተማረከ፡፡ የአሁኑን ዓለም ወደደና ከሐዋርያት ጋር ማገልገሉን ተወ፡፡ ክርስቶስ ለእርሱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልሆነም፡፡

‘ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው’ የሚለውን ቃል ዘንግተን ያመሰገንናቸው እንደ ሰማልያል አብርተው ጀምረው እንደ ሰይጣን ጨልመው የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ‘የዛሬን አያድርገውና እንዲህ እንዲህ ነበርሁ’ ብለው የሚተርኩ መነሻዬ ቤተ ክርስቲያን ነበረ የሚሉ መዳረሻቸው ሌላ የሆኑ በመንፈስ ጀምረው በሥጋ የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ግን መነሻም መድረሻም እኔ ነኝ ይላል፡፡ ክርስቶስ የማጣት ጊዜ አምላክህ የማግኘት ጊዜ ትዝታህ አይደለም፡፡ በማግኘትህ ውስጥም እግሩን አትልቀቀው፡፡ በደጅ ጥናትህ ጊዜ ጌታዬ ካልከው ስትሾምም አትርሳው፡፡

ቀንህን ስትጀምር ስሙን ጠርተህ ከጀመርህ ወደ ሥራህ ቦታም ስትሔድ ቤትህ አስቀምጠኸው አትውጣ፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነውና በእርሱ የጀመርከውን ቀንህን ከእርሱ ጋር ጨርሰው፡፡ ሰው በሥራ ቦታው በንግዱ ብዙ ወንጀል የሚሠራው ፈጣሪውን ሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሲያደርገው ነው፡፡

እግዚአብሔር መፍጠር የጀመረባትን የሳምንቱን መጀመሪያ እሑድ ዕለትን አሐዱ ብለን በቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር እንጀምራለን፡፡ በማግሥቱ ወደ ሥራና ማኅበራዊ ሕይወታችን ስንገባ ግን ክርስትናችን ይጠፋል፡፡ ሳምንቱን አልፋ ብለን የጀመርንበት አምላክ ኦሜጋ ሆኖ አብሮን እንዳይሰነብት እናደርገዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያው እንጂ መቃብሩ አይደለችም፡፡ እርሱ በቤተ ክርስቲያን በረድኤት ቢገለጥም በሁሉ ቦታም የሞላ አምላክ ነው፡፡

ክርስቶስን የምናስበው እሑድ ብቻ ከሆነና በሌሎቹ ቀናት በምንውልበት ሥፍራ የማናስበው ከሆነ ፤ ‘’ሥራ ሌላ ክርስትና ሌላ’’ ብለን የምንገድበው ከሆነ ትንሣኤውን ሳይሰሙ እሑድ ዕለት በመቃብሩ ሽቱ ሊቀቡ እንደሔዱት ቅዱሳት ሴቶች በእኛ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ገና አልተነሣም ማለት ነው፡፡ ‘ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ ክርስቶስን ከረሳኸው ክርስቶስ ለአንተ አልተነሣም ማለት ነው’ ይላል ቅዱስ አምብሮስ፡፡

ሐዋርያት ጌታ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ሁሉን ትተው የተከተሉት መጀመሪያቸው እርሱ ነበር፡፡ ዐርብ ዕለት ግን ከመካከላቸው ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ ኮበለለ፡፡ እነርሱም መከራ ፈርተው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ብቻ የወደደውን እስከ መጨረሻው ወድዶ ተከተለው፡፡ እርግጥ ነው የቀሩት ወንድሞቹም ከትንሣኤው ወዲያ በንስሓ ተመልሰው መጀመሪያቸውን ክርስቶስ መጨረሻቸው አደረጉት፡፡

ክርስቶስን ከማንም በላይ መጀመሪያዋም መጨረሻዋም ያደረገችው አልፋና ኦሜጋ የተጻፈባት ድንግል ማርያም ነበረች፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ሊሠጥ ሲፈቅድ ዓለምን ወክላ የተቀበለችው ድንግል አልፋ ክርስቶስ በማሕፀንዋ ተጽፎባት በቤተልሔም ግርግም በእቅፍዋ ነበረ፡፡ ከመስቀሉ ሥርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር፡፡ ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ ዕለት በልጅዋ ሥቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሎ ዮሐንስን ሠጣት፡፡ በእርስዋ ሕይወት ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ ነበረ፡፡

ወዳጆች ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፤ ነገ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ አልክድህም ብለን እንዳንዝት ሦስቴ እንዳንክደው እንፈራለን፡፡ መጀመሪያችን የሆነው አምላክ መጨረሻችን እንዲሆን ግን ‘እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን’ እያልን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጸልያለን፡፡
100 viewsAbay Getaneh, 10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 13:20:02
‹‹ጌታችን በመለከት ድምጽ ዐረገ›› (መዝ. ፵፮፥፭)
ነቢዩ ዳዊት አስቀድሞ በመንፈሰ ትንቢት ‹‹አምላካችን በዕልልታ፥ ጌታችንም በመለከት ድምጽ ዐረገ፥ ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ›› በማለት እንደተናገረ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ሥራውን ፈጽሞ ከሙታን ተለይቶ ከተነሣ በኋላ በዐርባኛው ቀን ዐርጓል።
በዕርገቱም ዕለት ሐዋርያት በተሰበሰቡበት እንዲህ አላቸው፤ ‹‹እነሆ፥ እኔ የአባቴን ተስፋ ለእናንት እልካለሁ፤ እናንተ ግን ከአርያም ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ተቀመጡ፡፡›› ከዚያም እስከ ቢታንያ አውራጃ መውጫ ድረስ ወሰዳቸውና ባረካቸው፡፡ እየራቃቸውም ሄደ፤ በደመናም ወደ ሰማይም ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝም ተቀመጠ፤ ሐዋርያቱም ሰገዱለት፤ እጅግም ደስ ብሏቸው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ አምላካቸውን እግዚአብሔርንም ዘወትር በምስጋና ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ (ሉቃ ፳፬፥፵፱-፶፪፣ማር፲፮፥፲፱)
እንኳን አደረሳችሁ!
141 viewsAbay Getaneh, 10:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 09:27:15 ቅዱሳን መላእክት ለሰዉ ልጆች ድኅነት እጅግ የሚጓጉ
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ጠባቂዎቻችን ናቸዉ። እርግጥ ነዉ፤ በመጀመሪያ እኛም እንደ መላእክት
ክብሩን ለመዉረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠርን ነበርን
ግንኙነታችንም እነርሱ ከእኛ ቀድመዉ በመፈጠራቸዉ
ታላላቅ ወንድሞቻችን ናቸዉ። ከሰዉ ልጅ ዉድቀት
በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። በእኛ የባህርይ መጎስቆል
ምክንያት ታላቅ ወንድም የታመመ ታናሹን እንደሚጠብቅ ጠባቂዎቻችን ሆኑ።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳለዉ፦ የሰዉ ልጅ
ከመላእክት ጋር ክቡር ሆኖ ሲፈጠር፤ ጠባቂን
አይሻም ነበር፤ ሰዉ በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን
እግዚአብሔር መላእክትን ጠባቂ አደረገለት።
ምክንያቱም ዲያብሎስ ሰዉን ለማጥፋት ሁል ጊዜ
ምክንያቶችን ስለሚፈልግ ነዉ።

እነዚህ መላእክት ከጠባቂነታቸዉ ባሻገር ለሰዉ ልጅ
መዳን እጅግ የሚጓጉ ሰዉን ወዳጆች ናቸዉ። አምላክ
ሰዉ ሆኖ በተወለደበት በዚያች ምሽት ሲዘምሩ
ያደሩት በአምላክ ሰዉ መሆን የሚያገኙት ጥቅም ኖሮ
ሳይሆን ለሰዉ ልጅ መዳን ካላቸዉ ፍላጎትና ፍቅር
የተነሳ ነዉ። በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
በምድርም ሰላም የሚለዉ ዝማሬያቸዉ የእኛ ሰላም
ለእነርሱ ምስጋና ምክንያት መሆን የሚያሳይ ምስጋና
ነበር። ሉቃ 2:14

የማያገቡትና የማይጋቡት እነዚህ መላእክት በሰማይ
የሰርግ ያህል ደስ የሚሰኙት በምድር አንድ ኃጢአተኛ
ንሰሓ ሲገባ መሆኑ ምን ያህል የእኛ ወዳጆች
መሆናቸዉን ያሳያል ሉቃስ15;10።

ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የተላኩ ስላላቸዉ ለማገዝ
የሚላኩ መናፍስት አይደሉምን?
148 viewsAbay Getaneh, 06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 12:57:57 +++ አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ +++

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት" ቅዱስ አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ" አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም
124 viewsAbay Getaneh, 09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 10:53:03 + አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ! +

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፣ መሐሪ ነው ፣ ይቅር ባይ ነው፡፡ ፍቅር ይቆጣል ወይ? ይቅር ባይስ ይቀጣል ወይ? ብዙዎቻችን ስለ ክርስቶስ ሲነገረን መሐሪነቱና ፍቅሩ ብቻ ቢነገረን አንጠላም፡፡ ጨርሶ የማንፈራው እግዚአብሔር እንፈልጋለን፡፡ እንዲህ አታድርግ! የሚለን ሲመጣ ‘አትፍረድ’ እንላለን ፤ ቆይተን ግን የሰማዩን ዳኝም አትፍረድ ማለት ይቃጣናል፡፡ ቅጣት የሌለበት ክርስትና እንሻለን፡፡

ይህ ዓይነቱን ክርስትና ‘ጣፋጭ ክርስትና’ {የስኳር ክርስትና ይሉታል} ምንም ምሬት የሌለበት ሁሌም ማር ማር የሚል ሕይወት አድርገው ክርስትናን የሚሰብኩም ብዙ ናቸው፡፡ ‘አይዞህ ብትታመም ትፈወሳለህ ፣ ቤትህ ይሞላል ፣ ቀዳዳህ ይደፈናል ፣ ብትበድልም አትቀጣም’ ብቻ የሚሉ ስብከቶች የስኳር ክርስትና ስብከቶች ናቸው፡፡ ይህንን ብቻ የሚያጮሁ ሰዎች ክርስቶስ ‘የምድር ጨው ናችሁ’ ያለውን ትተው የምድር ስኳር ለመሆንና ዓለምን ለማስደሰት የሚፈልጉ ናቸው፡፡
በእርግጥ እግዚአብሔር ይቆጣል ወይ? አዎን ይቆጣል! እንዲህ ይላል መጽሐፉ

‘እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል። በቍጣው ፊት የሚቆም ማን ነው? የቍጣውንም ትኵሳት ማን ይታገሣል? መዓቱ እንደ እሳት ይፈስሳል፥ ከእርሱም የተነሣ ዓለቶች ተሰነጠቁ’ ናሆ 1፡1፣6
‘‘ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች አሕዛብም መዓቱን አይችሉም’’ ኤር 10፡10
‘‘እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመዓትህም ደንግጠናልና’’ መዝ. 90፡7

እግዚአብሔር በተቆጣ ጊዜ የሚመልሰው የለም፡፡ ቅዱሳን የቁጣውን መጠን ስለሚያውቁ በትሕትና ይለምኑታል፡፡

ይሁንና መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ ደጋግሞ ቢነግረንም አንድ ሌላ ደስ የሚያሰኝ ነገርም ነግሮናል፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣው ለዘላለም አይደለም፡፡ "ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" ይላል እንጂ "ቁጣው ለዘላለም ነውና" አይልም:: የእግዚአብሔር ቁጣ ጊዜያዊ ነው፡፡

‘መሐሪ ነኝና ለዘላለም አልቆጣም’ ኤር 3፡12
‘ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን ነው’ መዝ 29፡5
‘ጌታ ለዘላለም አይጥልም ቢያሳዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል ፤ የሰው ልጆችን ከልቡ አያስጨንቅም አያሳዝንምም’ ሰ.ኤር 3፡31

የፈጣሪን የነነደ የቁጣ እሳት ማጥፋት የሚቻለን በዕንባ ነው፡፡ በደላችንን አምነን ቅጣት ይገባናል ነገር ግን መሐሪ ነህና ማረን ማለት ይገባል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘አቤቱ በቁጣህ አትቅሠፈኝ በመዓትህም አትገሥፀኝ’ ብሎ የፈጣሪን ቁጣ አበረደ፡፡ /መዝ 38፡1/ ነቢዩ ኤርያስም ‘አቤቱ ቅጣኝ ነገር ግን እንዳታዋርደኝ በመጠን ይሁን እንጂ በቁጣ አይሁን’ ብሎ ተለማመጠ፡፡ ኤር 10፡24

አንድ ሠዓሊ በጣም ብዙ ደክሞ የተጠበበትን ሥዕሉን የፈለገ ቢበሳጭ ለረዥም ጊዜ ያንን ሥዕል ለመሳል የተጠበበትን ጥበብ አስቦ ሥዕሉን ወደ እሳት አይጨምረውም፡፡ አባ ጊዮርጊስ እንዲህ ሲል ይለምናል ‘ሠዓሊ ሥዕሉን ያጠፋል ወይ? [ጌታ ሆይ እኔን ስትፈጥር የተጠበብክበትን] የቀደመ ጥበብህን አስብ እንጂ! አስበህም ማረኝ! [ያጠፋዖኑ ለሥዕሉ ሠዓሊ ፤ ኪነተከ ዘትካት ኀሊ]

ይቅርታውን በንስሓ ለሚለምኑ ሁሉ ምሕረቱ ቅርብ ነው፡፡ በቀኝና በግራው ወንበዴዎች በተሰቀሉበት በዕለተ አርብ የግራው ወንበዴ ሲሰድበው ጌታ መልስ አልሠጠም፡፡ የቀኙ ወንበዴ ማረኝ ሲለው ግን ከአፉ ተቀብሎ በገነት ትሆናለህ አለው፡፡ ቁጣው የራቀ ምሕረቱ የበዛ እርሱ የራበው ሰው ለምግብ የሚቸኩለውን ያህል ይቅር ለማለት ይቸኩላል፡፡ ‘ምሕረትን ይወድዳልና ቁጣውንም ለዘላለም አይጠብቅም ተመልሶ ይምረናል ፤ ክፋታችንንም ይጠቀጥቃል ፤ ኃጢአታችንንንም በባሕሩ ጥልቅ ይጥለዋል’ ሚክ 7፡18

ልጆች ሳለን ጥፋት ስናጠፋ ከወላጆቻችን እንደበቃለን፡፡በተደበቅንበት ሰዓት ውስጣችን በፍርሃት ይርዳል፡፡ ‘ዛሬ ገደለኝ’ ‘ዛሬ መሞቴ ነው’ ብለን እንጨነቃለን፡፡ የሚደርስብንን ቅጣት እጅግ አጋንነን ከመፍራታችን የተነሣ መሬት ተሰንጥቃ ብትውጠን አንጠላም፡፡ በዚያ ሁሉ ጭንቀት ውስጥ ግን ወላጆቻችንም እስኪያገኙን ይጨንነቃሉ፡፡ እግዚአብሔርም እንዲህ ነው፡፡ አጥፍቶ በገነት ዛፎች መካከል የተሸሸገ አዳምን ወዴት ነህ ብሎ የፈለገ እርሱ እኛንም ይፈልገናል፡፡ አዳም ከገነት ሳይባረር ገነት ውስጥ እንደጠፋ ፈጣሪ ሳያባርረን ራሳችንን በኃጢአት ተሸማቅቀን ያባረርን እኛን ይፈልገናል፡፡ እርሱ ስለመጥፋትህ ይጨነቃል አንተ ‘ዛሬስ አይምረኝም’ ትላለህ፡፡

የሚገርመው በጥፋታችን ከተደበቅንበት ወላጆቻችን ካገኙን በኋላ ሁለተኛው ዙር ጭንቀታችን ‘ምን አጥፍተህ ነው የተደበቅከው’ መባል ነው፡፡ ጥፋታችንን ሲያውጣጡን እንንቀጠቀጣለን፡፡ ያጠፋነውን ስለምናውቀው ስንት እንደሚያስገርፈንም እናውቀዋለን፡፡ ‘ብትናገር ይሻላል? ግዴለህም!’ ብለው አግባብተውም አስፈራርተውም ወላጆቻችን ጥፋታችንን ያውጣጡናል፡፡ እየፈራን ያጠፋነውን ጥፋት ስንናዘዝ ግን ወላጆቻችን በጥፋታችን ቅጥል ብለው ‘አልመታህም ተናገር’ ያሉንን ረስተው የዱላ ዝናም ያዘንቡብናል፡፡ እግዚአብሔር ግን ጥፋትህን ስትነግረው ቁጣው የሚገነፍል አባት አይደለም፡፡
’’ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነፃን የታመነና ጻድቅ ነው’ 1ዮሐ 1፡9

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መጋቢት 18 2012 ዓ ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
171 viewsAbay Getaneh, 07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 09:28:55
"እውነተኛው ክርስትና "#እኔ" ሳይሆን "#እኛ" እያሉ የሚኖሩት ህይወት ነው። ክርስትናም ፍቅር ነው። እንደ አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ እንደነ ቅዱስ ባስልዮስ የድሆች ቁስል ከተሰማህ ረሃባቸው ከራበህ አንተ ክርስትያን ነህ። እስከ መስዋዕትነት ለመድረስ ከችግረኞች ጎን ከቆምክ የሚያስፈልግህ ሁሉ የሚያስፈልጋቸው መሆኑን ካመንክ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ ነህ፡፡"

+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ሽኖዳ +
74 views@Đäŵã, 06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-09 19:04:11
103 views@Đäŵã, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ