Get Mystery Box with random crypto!

ግዮን ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ andromedamt — ግዮን ቲዩብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ andromedamt — ግዮን ቲዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @andromedamt
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.80K
የሰርጥ መግለጫ

👇👇👇👇👇👇👇
"እነሆ የመለያያ ሰዓታችን ደርሳለች
በየፊናችን እንጓዝ እኔም ወደ ሞቴ እናንተም ወደ ሕይወታችኁ
የትኛው እንደሚሻል ግን የሚያውቀው #እግዚአብሔር ብቻ ነው።"
ለሐሳብ አስተያየትዎ
👇👇👇👇👇👇
@Akirma_bot
#Mesfin_Teshome (ነቢር)

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-02-16 07:47:14 ራስህን እመነው!

ለችግርህ ጊዜ የራቁህ ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ። የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው።

ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከፈጣሪህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!

አስገራሚ እሮብ ተመኘንላችሁ
#Inspire_Ethiopia
የእናንተ ምርጥ ጓደኛ!
@ANDROMEDAMT
@ANDROMEDAMT
@ANDROMEDAMT
ሼር ሼር
836 views HENILOGY፯፯፯ኖን , edited  04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-13 13:53:46 ራስህን አክብር!

ሰዎች ላንተ የሚሰጡህ አክብሮት አንተ ለራስህ ከምትሰጠው ቦታ እና ከሁኔታህ ተነስተው ነው። ስለዚህ ሰዎች እንዲያከብሩህ ከፈለክ መጀመሪያ አንተ ራስህን አክብረው፤ ግድ የለሽ አትሁን፤ ለራስህ ቦታ ስትሰጥ ልበሙሉ ስለምትሆን አንተን ማወቃቸው ብቻ ያስደሰታቸዋል!

አስደሳች ምሽት ተመኘን #Inspire_Ethiopia
የእናንተ ምርጥ ጓደኛ
@ANDROMEDAMT
@ANDROMEDAMT

ሼር ሼር ሼር
1.1K views HENILOGY፯፯፯ኖን , 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 17:45:40 ዦንቶዦራ ሶስተኛ አን
1.1K viewsNebir Virgo, 14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 15:13:03 የጎረቤት ወግ
/ በ በዕውቀቱ ስዩም /

ወደቤቴ ከመግባቴ በፊት ከጨዋ ሚኒ ማርኬት ሁለት ኪሎ ማንጎ ገዛሁ፤
“በጥቁር ፌስታል አርጊልኝ” አልኩዋት ማሾን(ማሾ የሚኒ ማርኬቱ ባለቤት
ናት)
“አንተ ደሞ የጥቁር ፌስታል ልክፍት አለብህ “አለችኝ
እየሳቀች።
ውነቷን ነው! ከፍራፍሬው ጥራት በማይተናነስ መጠን የፌስታሉ ቀለም
ያሳስበኛል፤ ጥቁር ፌስታል በውስጡ ምን እንዳዘለ አያሳብቅም፣ ጥቁር
ፌስታል እንደ ጥሩ ወዳጅ ምስጢር አያዝረከርክም፤ያው መችም የኛ ሰው
፣በርሻና በንግድ ቢሰማራም በትርፍ ጊዜው ፓፓራዚ ነው፣ ምን እንደበላሽ
ለምን እንደበላሽ ካላወቀ የኖረ አይመስለውም። ገና ወደግቢ ስትዘልቂ
አይኑ ወርዶ ያንጠለጠልሽው ፌስታል ላይ ይተከላል፤
“ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ እይኖርም” ይላል አበሻ።እዚህ ግኝት
ላይ ለመደረስ የጎረቤትን ኑሮ ማወቅ ግድ ይላል፤ጎረቤት እንዴት አባቱ
አድርጎ እንደሚኖር ማጥናትና መሰለል ያስፈልጋል፤ ይህ ለኛ ብቻ የተሰጠ
ህዝባዊ ባህርይ ይመስለኛል።
እኔ አሜሪካ ውስጥ አንድ አመት ኖርያለሁ፣ ያን ያህል ጊዜ ስኖር :
አይደለም የጎረቤቴን ኑሮ : ጎረቤቴ ሰው ይሁን ይፎ አላውቅም
ነበር፤ርግጥ ፣ደጃፉ ላይ ባለረጅም ተረከዝ ጫማ ጥላ ስለምትገባ ሴት
እንደሆነች ገምቻለሁ፤ ግን ርግጠኛ መሆን አይቻልም። የተበየደ ፍናፍንት
(transexual)ሊሆንም፤ይችላል።
አሜሪካ ውስጥ ዜጋው መንግስትን የማወቅ መብት አለው። ኢትዮጵያ
ውስጥ ደግሞ ዜጋው ዜጋውን የማወቅ መብት አለው! ባለፈው ምኡዝ
ሁለት ኪሎ ስጋ ይዞ ሲገባ ፣ዘበኛው ከሚደግሙት ዳዊት ቀና ብለው ወደ
ስስ ፌስታሉ በጥልቅ አምሮት እየሾፉ፣
“እሱ ነገር ስጋ ነው?”
“የለም ስጋጃ ነው!” አለ ምኡዝ
የጥቁር ፌስታልን ጥቅም ከማወቄ በፊት በውሃ ቀለም ፌስታል አንድ ኪሎ
ሙዝ ገዝቼ ወደ ቤቴ ስገባ የግቢው ህፃናት ኩዋስ ጨዋታቸውን ትተው
መጥተው ከበቡኝ፤ ልጆቹ ካባታቸው ጋር ሳያምታቱኝ አልቀሩም”አንተ
ሰውየ ሙዝ ስጠኝ” አለኝ ፊት መሪው ልጅ። “ሙዝ ስጠኝ”ከሚለው
የድርቅና ጥያቄ በላይ፣” አንተ ሰውየ” መባሌ አናደደኝ።
በቁንጥጫ ልምዝግ ላረገው እጄን ወደ ወፍራም ጭኑ አካባቢ ስሰድ
ጭኑን አጣሁት። ሶስት ቁምጣ ደራርቦ ስለለበስ፤ጭኑን ለማግኘት
ኤክስሬይ ያስፈልጋል፤ ለምን በኩርኩም አልቆጋውም ብየ የቁንጮ
ማብቀያው ላይ አነጣጠርኩ። ግን ለማንኛውም ባካባቢው ሰው መኖር
አለመኖሩን ለማረጋገጥ ግራ ቀኝ ሾፍኩ፤ ፊትለፊት ካለው በረንዳ ላይ
የፊት መሪው ልጅ እናት እያየችኝ ነው። ባለስልጣን ናት፤ በኢፌድሪ
መንግስት በግብርናው ዘርፍ የጠቅላይ ምኒስትሩ አማካሪ ሻይ ቡና
በሚልበት ካፍቴሪያ ውስጥ ሲኒየር አስተናጋጅ ናት፤
“ሙዝ ነፍሳቸው ነው፤ካልሰጠካቸው አይለቁህም “አለች እየሳቀች፤
“ሴትዮ እነዚህን ልጆች እንደሚሆን አርጊያቸው፣ ታልሆነ ቁርጡን ንገሪኝና
በጉዲፈቻ ላሳድጋቸው”
አልሁ ድምፄን ዝቅ አድርጌ።
በይሉኝታ ሙዜን አከፋፈልኩ፤ ለኔ ፌስታልና ንዴት ተረፈኝ
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ፣ የመላው ኮንዶ ግቢ ልጆች መተኛታቸውን
ካላረጋገጥሁ በቀር የሚበላ ነገር ገዝቼ ለመግባት አልደፍርም።
ዛሬ በጥቁር ፌስታል ማንጎየን ሸክፌ ወደ ቤቴ የምጣደፈው ያለምክንያት
አይደለም፤ ቶሎ ገብቸ ቀኑን ሙሉ በፊኛየ የቁዋጠርኩዋትን ተረፈ ምርቴን
መገላገል ቸኩያለሁ።
ወደ ፎቁ መወጣጫ ላይ ስደርስ ባሻ አመዴ እየተጎተቱ ተጀርባ ደረሱብኝ፤
ባሻ ጥንታዊ አርበኛ ናቸው። ባርበኝነታቸው ዘመን ሞትን እጅግ
ከመናቃቸው የተነሳ ተኝተው መተኮስ አይወዱም ነበር። በማይጨው
ጦርነት ርማቸውን ተኝተው ቢተኩሱ በዚያው እንቅልፍ ወሰዳቸው።
“እንኩዋን ለድል ቀን አደረሶት! ይለፉ ብየ አስቀደምኩዋቸው፤ ወድያው
ግን ፀፀት አንገበገበኝ፤ ባሻ መወጣጫውን በሰውነታቸው ሞልተው
እያቃሰቱ ወጥተው እስኪጨርሱ ፊኛየን እያስታመምኩ መጠበቅ ሊኖርብኝ
ነው።
፣(ሰው ግን ለምን እሺ ብሎ ያረጃል?! ማርጀት እንደ እንጥል መቁረጥ ጎጅ
ልማድ ነው፤)
እግራቸው በመከራ ሲጎትቱ ሳይ ቁርጭምጭሚታቸው ላይ ግማሽ
ኩንትል ጤፍ ያሰሩ መሰለኝ፤ግራ እግራቸውን ካንዱ ደረጃ አንስተው
ሁለተኛው ደረጃ ላይ እስኪያሳርፉ ድረስ፣ሰሜን ኮርያ ሶስት ሚሳይል
ሞክራለች፣ አሜሪካ ሰባት ጊዜ ፎክራለች፤
የቅድሙ ትግስቴ ስላለቀ፤ ተጨማሪ ትግስት እየሞላሁ ጠበቅሁ፤
ባለፈው ከባሻ ጋር ጦቢያ ጠጅ ቤት ተቀምጠን ስናወጋ የማውቀውን
የጀግነት ዘፈን እንድዘፍንላቸው ጠይቀውኝ ነበር ። በልጅነቴ እሰማው
የነበረውን ዘፈን ዘፈንኩላቸው።
“ክላሽንኮቡን በጎኑ አንግቦ
አርፒጂውን በጎኑ አንግቦ
አላማና ቦንቡን በጎኑ አንግቦ
50ካሊቬሩን ከሁዋላው ወድሮ
ኮዳና ስንቁን ከሁዋላው አዝሎ
ይምጣ ቆራጡ ነፃ አውጭው ታግሎ”
ባሻ አላስጨረሱኝም።
“አይ ጦርነትን አለማወቅ! ” አሉ በትካዜ” ይሄን ሁሉ ተሸክሞ በምን አቅሙ
ነው የሚዋጋው! በሰሜን ተራራ ላይ እንኩዋን ይሄን ሁሉ ተሸክመህበት
የገዛ ቆለጥህ ይከብድሃል”
1.4K viewsNebir Virgo, 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ