Get Mystery Box with random crypto!

ATTITUDE [ጉልላት አበበ]

የቴሌግራም ቻናል አርማ gullea — ATTITUDE [ጉልላት አበበ] A
የቴሌግራም ቻናል አርማ gullea — ATTITUDE [ጉልላት አበበ]
የሰርጥ አድራሻ: @gullea
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.65K
የሰርጥ መግለጫ

ትረካ
ልቦለድ
እና የግጥም ስራዎችን ለማግኘት
ተቀላቀሉ
join our channel and share
ለአስተያየት
@EthealBot ይጠቀሙ
ለመደወል
@Gulilatab
251930756700

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-03-06 10:24:29 Safaricom ethiopia ሽልማት
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
ያልተገደበ የአንድ ወር ኢንተርኔት
smart phone( s21 ultra)
Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ



https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0280142047
1.0K viewsGulilat Abebe, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-06 10:23:39 Safaricom
ውድ ደንበኞቻችን ብዙዎቻቹ ባቀረባቹልን ቅሬታ መሰረት የሽልማት ማሻሻያ አድርገናል።
ማለትም ከዚ በፊት 50 ሰዎ ወደኛ ገፅ ከጋበዛቹ one month unlimited internet የነበረው ለ wifi ተጠቃሚዎች ስለማይጠቅም ሽልማቱን በብር ቀይረነዋል።
እናም 30 ሰዎ ወደኛ ገፅ ሲጋብዙ የ 3000 ብር ሽልማት
50 ሰው ሲጋብዙ የ 5000 ብር ሽልማት
አንዲሁም ለቤት እመቤቶች (ሴቶች) ከሸዋ ሱፐር ማርኬት የ 10,000 ብር እቃ ሽልማት አዘጋጅተናል።
957 viewsGulilat Abebe, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-25 08:50:37
Safaricom ethiopia ሽልማት
በተጠቃሚዎች ዘንድ እውቅናን ለማትረፍና ደንበኞችን ለማብዛት የቴሌግራም bot ከፍተናል
በውስጡም ብዙ ሽልማቶችን አዘጋጅተናል።
ያልተገደበ የአንድ ወር ኢንተርኔት
smart phone( s21 ultra)
Asus personal computer
ይህንን ለጓደኞችዎ በመላክ ተሸላሚ ይሁኑ

ማሳሰቢያ! ይህ ሊንክ የሚያገለግለው ለ Gulilat ብቻ ነው

https://t.me/Safaricom_ethiopia_new_bot?start=r0280142047
1.2K viewsGulilat Abebe, 05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-29 13:59:23 ረድኤት

ክፍል 1

"የሴትነት አቅሙ እስከምን ድረስ ነው? ሴቶች ከወንዶች ይልቅ ጠንካራ ናቸው አላልከኝም?" ትላለች ለብቻዋ አልጋዋን በስስ እጆቿ እየደበደበች
"አልሸነፍም ነበር እኮ......እንዴት.. እንዴት" እንባዋ ከትዕዛዟ ውጪ ይሆናል ። ሳታስበው ታነባለች
ከአልጋዋ መተሻሸት ትራሷን ማቀፍ ከዛም ስለ ሽንፈቷ ማሰብ መቆጨት የዘወትር ተግባሯ ሆኗል
ረድኤት ነው ስሟ
አንድ ቀን ሀዋሳ ከጓደኞቼ ጋር እየተዝናናን ነበር ያገኘኃት ። ጓደኞቼ ውሀ ዳር መዝናናት ይወዳሉና እነሱ እስኪጨርሱ እኔ ዙሪያውን እየቃኘሁ ነበር
የዛኔ ነበር ረዱዬን ለብቻዋ ያገኘኃት ረዱዬ አልኩ እንዴ? ይቅርታ ረድኤት...
"ምነው ከጓደኞችህ ተለይተህ?" አለቺኝ
"ምነው ከቤተሰቦችሽ ተለይተሽ ?" ጥያቄዋን በጥያቄ መለስኩላት
እውነት ለማውራት አጠገቧ ልቀመጥ እንጂ እሷን የመተዋወቅ ሀሳቡም አልነበረኝም በቃ አለ አይደል ጓደኞቼ እስኪጨርሱ ከሰው ጋር ለመሆን...
"ውሀ ከመጠጥነት ባሻገር እንደዚህ ለመበጣጠስ መጠቀም አልወድም" አልኳት
ዝም
"ቦታውን እንዴት አገኘሺው?"
ዝም
ከረጅም ዝምታ በኃላ "ስለተፈጥሮ ልታስረዳኝ ትችላለህ?' አለቺኝ
ውስጤ መናገር እየፈለገ ዝም አልኳት (እሷ ዝም እንዳለቺኝ)
ትንሽ ቆይታ "እኮ የተፈጥሮ መልሱ ዝምታ ነው አንተ ጎበዝ ነህ አየህ ብዙዎቹ እናውቃለን እያሉ ተፈጥሮን በማይረባ የቃላት ጋጋታ ያውኳታል ፣ ጣዕሟን ያሳጡታል፣ ብልሆች ግን ዝምተኛዋን ተፈጥሮ በዝምታ ይገልጿታል።" አለቺኝ በግማሽ ግርምት
ደነገጥኩ !
ልጅቷ ያማታል? ወይስ ትፈላሰፋለች?
ረድኤት ተነስታ ሄደች
"ቤተሰቦችሽን አትጠብቂያቸውም?" አልኳት (እንድትቆይ ፈልጌያለሁ)
"ቤተሰቦቼ አይደሉም" አለቺኝ
ትንሽ አንደተራመደች "መሄድ ከፈለግክ ና.." አለቺኝ
ተከተልኳት
"ጓደኞችህን አትጠብቃቸውም?" አለቺኝ
"ጓደኞቼ አይደሉም" አልኳት
ሳቀች ..ደስ አለኝ
ከሩዱ ጋር ከተዋወቅን ሳምንት አስቆጠርን
ረዱ አንድ ቀን ታሪኳን እንዲህ ስትል አጫውታኛለች...
ቤት ውስጥ አራት ነን እኔ ትንሹ ወንድሜ ሄኖክ አባት እና እናቴ። በጣም የተሳካልን ቤተሰብ እንደሆንን ጓደኞቼ ይነግሩኛል። እኔ ገና ስኬት ማለት ምን እንደሆነ እንኳን በቅጡ አላውቅም ስኬት ማለት ለእነሱ ከብዙሀኑ የተለየ መሆን ማለት ነው። በዚህ ሚዛን ከታየ እኛ ቤት ከአብዛኛው የሀዋሳ ነዋሪ ህዝብ የተለየ ነገር አለ።ዘመናዊ አባት አለኝ። ዘመናዊ እናት እና ዘመናዊ ወንድም አሉኝ። የመጀመሪያ ልጃቸው ነኝ ሲበዛ ይወዱኛል። እያንዳንዱ ድርጊት እኔ ጋር ከመድረሱ በፊት እነሱ መንካት ወይም ማየት አለባቸው። አያምኑኝም የሁልጊዜ ምክራቸው ህይወታቸው እኔ እንደሆንኩ ነው። ይህ ነገር ምናልባት ብቸኛ ልጃቸው ስለሆንኩ መስሎኝ ነበረ ነገር ግን ትንሹ ሄኖክ ከመጣ በኃላም ይህ ጥንቃቄያቸው አልቀነሰም እንዲሁም በእጥፍ ጨመረ።
"አየህ ህይወትን እንዳውቃት አድል አልሰጡኝም! እኔ የማውቃት አለም እነሱ ያሳዩኝን ብቻ ነው። ያም ማለት ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አልተዋወቅም
በአንድ የታጠረ ግቢ ታጥሬ ነው ያለሁት ። የታሪክ መምህራችን የሰው ልጅ ነፃነት ያለው ፍጥረት ነው ሲል እስቃለሁ! ነፃነት በታጠረ ግቢ ውስጥ ከቤት ወደ ትምህርት ቤት መመላለስ ነው? ነፃነት አላደግሽም ተብሎ በእጀባ መንቀሳቀስ ነው?
ነፃነት አልኮረደድሽምና የኤርሚዬን አይን ማየት አትችዪም ማለት ነው?
"ኤርሚዬ ስትል ከተመሰጥኩበት ተመለስኩ፤ጓደኞቼን መካዴ ቆጨኝ"
"የት ሄድክ?" አለቺኝ
አለሁ እየሰማሁሽ ነው
ታሪኳን ቀጠለች.......

ይቀጥላል ሼር ላይክ
3.1K viewsGulilat Abebe, 10:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-29 13:24:28 ረድኤት
ተከታታይ ታሪክ
2.2K viewsGulilat Abebe, 10:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-29 13:23:44
2.1K viewsGulilat Abebe, 10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 16:38:22 ጣፋጭ ታሪኮች ያለማቋረጥ ይቀርባሉ እናመሰግናለን
2.8K viewsተፈጣሪ !!, 13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-24 16:36:51

2.6K viewsተፈጣሪ !!, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-07 19:28:35 ‍ ቢልጌትስ በሐብት የሚበልጠኝ አንድ ጥቁር ብቻ ነው አለ

የአለማችን ቀዳሚ ባለጠጋ በአንድ ኢንተርቪው እንዲህ ተጠየቀ
ከአንተ የሚበልጥ ባለጠጋ ማን ነው ?
ከአንተ የሚበልጥህ ባለጠጋ አለ ?
‹‹አዎ የሚበልጠኝ ሰው አለ፡፡ የሚበልጠኝ አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡ ከብዙ ዓመት በፊት ወደኒውዮርክ መሄድ ነበረብኝ፡፡ ወደ ኒውዮርክ ለመሄድ አየር መንገድ ላይ ሳለሁ የተለያዩ ጋዜጦችን የጋዜጣ አዟሪዎች እጅ ላይ አየሁ፡፡ ካየኋቸው ጋዜጦች መካከል አንዱን ወደድኩት ለመግዛት አስቤ ኪሴ ስገባ ዝርዝር ስላጣሁ ሳልገዛው መልሼ ተውኩት፡፡
በድንገትም አንድ ጥቁር ጋዜጣ አዟሪ ልጅ መጣና ጋዜጣውን ሰጠኝ፡፡ ዝርዝር የለኝም አልወስደውም አልኩት እርሱም ችግር የለውም በነጻ ውሰደው አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡

ከሦስት ወር በኋላ ተመልሼ በዚያው አየር መንገድ ማለፍ ነበረብኝና በዚያ አየር መንገድ ሳልፍ አሁንም አጋጣሚ ሆነና ያንን ጋዜጣ አዟሪ ጥቁር ልጅ አገኘሁት፡፡ አሁንም በነፃ ጋዜጣ ሰጠኝ፡፡ እኔም በነፃ አልቀበልህም አልኩት እርሱም ግድየለም ከትርፌ ላይ እቀንሳለሁ ውሰድ አለኝና በነጻ ሰጠኝ፡፡
ከ19 አመትም በኋላ ባለጠጋ ከሆንኩ በኋላ ያንን ልጅ ፈልጌ ለማግኘት ወሰንኩና ፈለኩት ከአንድ ወር ተኩል ፍለጋም በኋላ አገኘሁት፡፡ ከዚያም አወከኝ ብዬ ጠየኩት ፡፡ አዎ አውቅሃለሁ ዝነኛው ቢልጌት አይደለህም አለኝ፡፡ ከብዙ አመት በፊት ሁለት ጊዜ ጋዜጣ በነጻ ሰጥተኸኛል፡፡ ያንን ውለታህን አካክሼ መመለስ እፈልጋለሁና የፈለከውን የትኛውንም ነገር እሰጥሃለሁ ጠይቀኝ አልኩት፡፡
ያም ጥቁር ሰው በምንም መካካሻ ልትሰጠኝ አትችልም አለኝ
እኔም ለምን አልኩት
እኔ የሰጠሁህ ደሃ በነበርኩ ጊዜ ከድህነቴ ነው፡፡ አንተ ግን ልትሰጠኝ የመጣኸው ባለጠጋ በሆንክ ጊዜ ነው፡፡ እነዚህን ሁለቱን እንዴት አካክሰህ ልትሰጠኝ ትችላለህ፡፡
ቢልጌትም ያጥቁር ወጣት በርግጥም ከእኔ የሚበልጥ ባለጠጋ ነው፡፡
ለመስጠት ባለጠጋ መሆንህን ወይም ባለጠጋ እስክትሆን ድረስ አትጠብቅ ፡፡ መስጠት የልብ ጉዳይ ነው እንጂ የአቅም ጉዳይ አይደለም፡፡

ከመፃህፍት አለም
꧁༻༒༺꧂
3.4K viewsተፈጣሪ !!, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-20 09:29:12 ነገሮችን ሁሉ ከአእምሮ ጋር በሚያያዝ መልኩ ለመተርጎም እንሞክራለን። በዚሁ አካሄዳችን የጽናትን ሁሳብ ስንመለከት በምን መልኩ ውስጣችንን ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ ይኖርብናል። እስኪ ማንም ለቁም ነገር ባይፈልግህ ወይም አንተ ልታደርገው የተገባህ ነገር በተደጋጋሚ ለሌላ ሰው ታልፎ ቢሰጥ አለመስራትህ ከሚያስደስትህ ይልቅ አለመታመንህ ሊያምህ ይችላል። እምነትን ምንገበየው ደግሞ አንዱ መንገድ ታማኝ ማንነት የሚያሰጠንን ጽናት መያዝ ነው። ችግር ሚፈጠረው ግን ወጥ የሆነ ማንነትን ለመያዝ ከወላዋይነት ስንሸሽ ድንበሩን ጥሰን ግትርነት ጋር እንደርሳለን። ግትር መሆን ማለት በአጭሩ በቂ ምክንያት ተሰጥቶንም አለመንቀሳቀስ ነው። ይሄ እጅግ የከፋ ነው።

ስለዚህ "ባላንሱን" ማወቅ ይኖርብናል። ከወዲህ በኩል ምክንያታዊነትን እና ተራማጅነትን መያዝ ከግትርነት ይጠብቀናል። ከወዲያ ደግሞ በቃል አለመጽናትን በሀሳብ አለመዝለቅን መራቅ አለብን። ይህ ካልሆነ የአእምሮአችን ጤና ከግንኙነቶቻችን ጋር እጅግ የተቆራኘ በመሆኑ የባህርይ ችግራችን መልሶ የኛኑ ጤና ይነሳናል። ጭንቀት ድብታ ሊሰፍርብን ሰፊ እድልም ይኖረዋል።

ጀምሮ መቀጠል ተናግሮ መተግበር አስቦ ማድረግ እጅግ ከባድ ቢሆንና ፍጹም መሆን ባንችልም ቢያንስ ልንታመን ሚያበቃን ያህል መሆን ይኖርብናል።

ይህን ሀሳብ ስናጠቃልል የመጨረሻው ነጥብ ሊሆን የተገባው እጅግ ግልጽ የሆነው የአለመጽናት በሽታችን ሚገለጥበት ስፍራ ላይ ጥቂትም ቢሆን ማውራት ይጠበቅብናል። በሀሳብና በአቋም አለመርገጥ በቃላት ከሀሳብና ከቃላት ጋር አለመስማማትን በቂ በሚባል ደረጃ ጀምረናል። ቀረን ምለው ቢኖር ቃላት ከተግባር ጋር እንዲሁም ተግባር ከሌላ ተግባር ጋር ሚያጋጥማቸውን መፋለስ ነው። ኤመርሰንን "ምትሰራው እጅግ ይጮሃልና ምታወራውን መስማት አልቻልኩም" ያስባለው ይሄ ስፍራ ነው። ብዙ ጊዜ ይህ መፋለስ በግንኙነቶቻችን ያጋጥሙናል። በርግጥ ምናስተውለው ከሰው በኩል ሲደርስብን እንጂ የኛን ጥፋት ለማስተዋል እጅግ ታውረናል። የሆነው ሆኖ ጓደኛ ለማቆየት ወይም ስሜቱን ላለመጉዳት ስንል የውሸት ተስፋዎችንና የሀሰት ፍቅሮችን እያዘነብን እንከርምና ብዙ ሳይቆይ በአንደበታችን ከሰቀልነው ፎቅ ላይ ስራችን ያለ ርህራሄ ይፈጠፍጠዋል። (እንዳልኩት አይምሮህ ሚያስታውሰው የፈጠፈጡህን ብቻ ነው) ስለዚህ ከኛ በኩል ስንነሳ ለማንም ሰው መራራ እውነታ ወይም ከባድ ሀቅ ለጊዜው ቢያስከፋና ቢያቃቅር እንኳ ከዚህ ሁሉ አድነዋለው ሚለን ውሸታም አንደበት የኋላ ኋላ ማይሽር ቁስል ሰውየው ላይ በስማችን እንዲፈረም ያደርጋል። ይህን ካስተዋልን እንግዲህ በጊዜውና በቦታው መነገር ያለበትን ነግረን መፍትሄ መፈለጉና ርቀት መጠበቁ እጅግ የተሻለ አማራጭ ነው። ከሰው ወደኛ ለሚመጣው ደግሞ ሁል ጊዜም ሰዎች ሌላውን ላለመጉዳት ወይም መልካቸውን ላለመበላሸት ከሁለት በአንዱ ወይም በሁለቱም አንድ ላይ እየተመሩ ሚኖሩ ፍጡራን ስለሆኑ ሚነግሩህን ከነዚህ አንጻር ተመልክተህ ብዙ ላለማመን ሞክር ተጨባጭና ቀጣይነት ያለው ቃላቶቹንና ቅጽበታዊ ተግባሮቹን ሚያጸና ባህርይ እስክትመለከት ድረስ። ለኔ ይህን ያህል ቦታ አለው ብለህ ለመደሰት አትቸኩል።

እንግዲህ አንድ ሆነን ሳለን ብዙ እንሆናለን አንድ አንደበት እርስ በርስ ሚዋጉ ቃላትን ያፈልቃል አንድ አካል እጅግ የተራራቁ መልኮችን ያሳያል የሰውን እንደ አመጣጡ መመለስንና መረዳትን እየተማርን የራሳችንን ማንነት ደግሞ መልሰን ወደ አንድነት ለመመለስ መሮጥ ይኖርብናል። በዚህ ሂደት ምናስመዘግበው ለውጥ ሁሉ በቅርብም ይሁን በሩቅ ብዙ ዋጋ ይከፍለናል። አዲስ በመሸለምም ይሁን ጉዳትን በመቀነስ መልካም ይሆንልናል። በአእምሮአችን ጤና በግንኙነቶቻችን መዓዛ በስራችን ውጤታማነት ብዙ መኸር አጫጆች እንሆናለን።

The Bored Therapist

ከመፅሐፍ ቤት
3.1K viewsተፈጣሪ !!, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ