Get Mystery Box with random crypto!

አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ amucampus — አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ
የቴሌግራም ቻናል አርማ amucampus — አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ
የሰርጥ አድራሻ: @amucampus
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.14K
የሰርጥ መግለጫ

Official Arbaminch University ®
ማስታወቂያዎችን እና ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነትና በጥራት!
ሀሳቦች እና እንዲተላለፍላችሁ የምትፈጉት ነገር ካለ በ
@newneway
@Fika_Amare
@miko1122
@ADA1249
ላይ ያግኙን፡፡
AMU Info ......
እውነተኛ እና ፈጣን መረጃ ይደርሶታል፡፡
።።ከተማሪ ለተማሪ።።:
Arba_Minch_university

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-24 08:50:05
የሀዘን መግለጫ
Devachn እንወድሃለን ሁለም በልባችን ትኖራለክ RIP

ዳዊት ይልማ ይባላል 08 ባች አርባምንጭ ዪኒቨርስቲ CIVIL ምህንድስና ተማሪ ነበር በጣም ትሁት እና ታታሪ ልጅ ነበር

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተማሪው ዳዊት ይልማ ድንገተኛ ኅልፈተ ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ፣ ለፋከልቲው መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
1.2K viewslast seen recently, edited  05:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 10:10:57

2.2K viewsTy dolla $ign, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 14:30:27 በድጋሚ የወጣ የነባር የክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች ጥሪ ጊዜ ማሻሻያ ማስታወቂያ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ/ም የነባር የክረምት መርሃ-ግብር ትምህርት የምዝገባና የትምህርት መጀመሪያ ጊዜ አስመልክቶ በቴሌቪዥን፣ በዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽና ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ምዝገባ ሐምሌ 11-12/2014 ዓ/ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀምርበት ጊዜ ሐምሌ 13/2014 ዓ/ም መሆኑን ማስተዋወቁ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ ከትምህርት ሚኒስቴር በ27/10/2014 ዓ/ም በተጻፈ ደብዳቤ በኮቪድ - 19 እና በሰሜኑ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች መደበኛ የትምህርት መርሃ-ግብር በተቀመጠለት ጊዜ ባለመጠናቀቁ የ2014 ዓ/ም የክረምት የመምህራንና የት/ቤት አመራሮች ደረጃ ማሻሻያ ትምህርት ከሐምሌ 20/2014 ዓ/ም እስከ መስከረም 10/2015 እንዲካሄድ ስለተገለጸ በዚሁ አግባብ ማሻሻያ በማድረግ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምዝገባ ጊዜ ሐምሌ 20-21/2014 ዓ/ም እንዲሁም ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ ሐምሌ 22/2014 ዓ/ም መሆኑን በድጋሚ ያሳውቃል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

@amucampus
@amucampus
3.4K viewsMusse, 11:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 12:04:41 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዬች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችው በዓሉ የሰላም , የደስታ , የብልግና ,የስኬት እና የፍቅር ይሁንላችው!

መልካም በዓል ለሁላችን
@amucampus
@amucampus
506 viewsMusse, 09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:16:06 የ 2014 ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን አደረሳቹ

Congra

Especially dmoo

Oly
Bela
Eshu
Yoni
Abdu(2)
Rahwi
Fodi
Nahom
Josi
Bebi
Mita
Heli
Elu
Shemsi
Eku
Jem
Tedi
Becho
Ayu
Rich
Elif
.....
.....
.....
.....

G 5 (Mechanical)
1.6K viewsØmãr , edited  07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 10:26:06
#ArbaMichUniversity

አርባ ምንጭ የኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 540 ተማሪዎች ያስመርቃል።

ተመራቂዎቹ ከመጀመሪያ እስከ 3ኛ ዲግሪ በመደበኛ፣ በክረምት፣ በማታ፣ በሳምንት መጨረሻ እና በተከታታይ መርሃ ግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ከዩኒቨርሲቲው 35ኛ ዙር ተመራቂዎቹ መካከል 657ቱ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የተማሪዎች የምረቃ ስነ ስርዓት ነገ ሰኔ 25/2014 ዓ.ም እና እሁድ ሰኔ 26/2014 ዓ.ም ይከናወናል።
1.8K viewslast seen recently, edited  07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 07:55:33 Congratulations !
ዩኒቨርሲቲያችን የ2014 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ሰኔ 25/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን አሳውቋል ።
@amucampus
@amucampus
@newneway
2.4K viewsMusse, 04:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 07:51:21 ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪ የክረምት መርሃ-ግብር ተማሪዎች በሙለ
የ2014 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ሐምሌ 4-5/2014 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት
በየካምፓሶቻችሁ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እየገለጽን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን
ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ እንዲሁም ይህ ማስታወቂያ የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን
የማይመለከት መሆኑን ያስታውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታታይና ርቀት ትምህርት ኮሌጅ

@amucampus
@amucampus
2.2K viewsMusse, 04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 15:03:41
FreelanceEthiopia

በትርፍ ሰዓትዎ ከሚሰርዋቸው ሥራዎች ጀምሮ እንደ ትምህርት ደርጃዎ፣ የሥራ ልምድዎ እና ፍላጎትዎ በሁሉም አይነት ዘርፎች ሁሉንም አይነት ሥራዎች በአንድ ቦታ ያገኛሉ።
2.9K views𝖆𝖘𝖚𝖙𝖎 𝔂𝓲𝓶, 12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 09:48:03 #ማስታወቂያ
ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ“ELT”፣ በ“Environment and Natural Resources Management” እና በ“Disaster Risk Management” ትምህርት ፕሮግራሞች በ3ኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ሰኔ/4/2014 ዓ/ም፣ የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ ማለትም ሰኔ 6 እና 7/2014 ዓ/ም የመጨረሻ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የሀገር ውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡
በዚህ መሠረት ዕጩ ዶ/ር ምኅረትዓብ አብረሃም በ “ELT PhD Program”፣ ቶማስ ቶማ በ “Disaster Risk Management PhD Program”፣ ታሪኩ ዘካሪያስ በ “Environment and Natural Resources Management PhD Program” እና ማሙሽ ማሻ በ “Environment and Natural Resources Management PhD Program” ያከናወኗቸውን የመመረቂያ ጽሑፎች ከላይ በተገለጸው መርሃ - ግብር የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ 
በተመሳሳይም የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ“Biodiversity Conservation and Management” ትምህርት ፕሮግራም በ3ኛ ዲግሪ ያሠለጠነው ዕጩ ዶ/ር ብርሃኑ ጌቦ የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 8/2014 ዓ/ም “Socio-Ecological Drivers of Mammalian Diversity and Human-Carnivore Coexistence in the Faragosa-Fura Landscape of Southern Rift Valley, Ethiopia” በሚል ርዕስ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የሀገር ውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት ያቀርባሉ፡፡
ዕጩ ዶክተሮቹ የምርምር ሥራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ቀደም ብለው የማሳተም ልምድ ያላቸው ሲሆን በዚህ መሠረት ዕጩ ዶክተር ምኅረትዓብ አብረሃም 3፣ ቶማስ ቶማ 3፣ ታሪኩ ዘካሪያስ 2፣ ማሙሽ ማሻ 3 እና ብርሃኑ ጌቦ 5 ጥናታዊ ጽሑፎችን ያሳተሙ ናቸው፡፡
ስለሆነም የሚመለከታችሁ የዘርፉ የ2ኛ ዲግሪና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎችና መምህራን በመርሃ-ግብሩ እንድትሳተፉ የተጋበዛችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያስታውቃል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

@amucampus
@newneway
@amucampus
2.2K viewsMusse, 06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ