Get Mystery Box with random crypto!

ተወኝ (ጸጋዬ ገብረ መድኅን) ላታስታምም አትመመኝ ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ ይቅር፥ አንጀቴን ቁረ | ሥነ-ግጥም

ተወኝ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ጋሽዬ፥ አልወድሽም በለኝ።
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ፥ ወንድ ነው ቆራጡ፥ እንትፍ-እርገህ ተወኝ።
አየህ፥ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩ፥ ረከስኩ ቀለልኩ እሚለኝ፥
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ
ሥጋሽን ሳይሆን ልብሽን፥ ከፍተሽ ጥለሽ ነው እምትለኝ
እና ተወኝ፥ ባክህ ተወኝ፤
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት
የሴት ቁንጮ እምመስላት
ጐረቤት ፊት እምታፍር፥ እንዲህ ሆነችልሽ ሲሏት!
እና፥ አልሆንሽም በለኝ
ባክህ አንጀቴን ቁረጠኝ
ፍቅር እንደሁ የኔ ይበቃል፥ ላንተም ለኔም እኔው ልውደድ
ከዘመድ ግንባር ደብቄ፥ እኔ ለብቻዬ ልንደድ፥
ብቻ፥ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም፥ ንቀህ ማረኝ
ካንተም ከስሜም ከቤቴም፥ ያጣሁ ብኩን አታድርገኝ፥
ባክህ፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ተወኝ፥ ተወኝ፥ ተወኝ።
---------------------------