Get Mystery Box with random crypto!

ዝኑፍ ወቀሳ ! ( በረከት በላይነህ ) ይለኛል ታዛቢ... 'በእኛ ተረማምዶ - ስኬቱን ሸመተ ፤ | ሥነ-ግጥም

ዝኑፍ ወቀሳ !
( በረከት በላይነህ )

ይለኛል ታዛቢ...
"በእኛ ተረማምዶ - ስኬቱን ሸመተ ፤
ሲመቸው፣ ሲደላው - ትቶን ሰነበተ ! "
ይለኛል ታዛቢ...
"አቅፈን አሳድገን - ከሰው መሐል
ለየን ፤
አለፈለትና - ዞር ብሎም አያየን !"
እኔ ግን እላለሁ !..
"ስህተት የለብኝም ፤
ያለፍኩበት ሁሉ አላሻገረኝም ፤
የረገጥኩት ሁሉ አልተሸከመኝም !"