Get Mystery Box with random crypto!

ዓለሙ ሰልችቶኝ ዓለሙ ሰልችቶኝ ሰው ሴቱ ወንዱ፤ ሐበሻው ፈረንጁ ትግሬው አማራው፤ አዳሜ ባጭሩ፤ | ሥነ-ግጥም

ዓለሙ ሰልችቶኝ

ዓለሙ ሰልችቶኝ ሰው ሴቱ ወንዱ፤
ሐበሻው ፈረንጁ ትግሬው አማራው፤
አዳሜ ባጭሩ፤
ነገር ክርክር
ፌዙ ቀልዱ ሣቁ ፉከራው ጉራው፤

ሽሙጥና አሽሙሩ ሐሜት ቅናቱ፤
አለመስማማት፤
አለመገባባት፤

ዛፍና ቅጠሉን ሰማዩን ለማየት፤
የሣሩን መዓዛ ሽቶውን ለማሽተት፤
እዚያ ለመንጋለል ካሳብ ለማረፍ፤
በተንቀዠቀዠ ውሻ'ፍ ልለከፍ፤
ማረፍያ ለመሆን ለርግቦቹ ኩስ፤
ለማጨመታተር የሱሬየን ተኩስ ፤
የመንፈስ ጸጥታን ሰላምን አደን፤
ወደ ጫከው ገባሁ ታቅፌሽ አንቺን።

(መንግስቱ ለማ፡ የግጥም ጉባዔ ፡ 1955)