Get Mystery Box with random crypto!

ሥነ-ግጥም

የቴሌግራም ቻናል አርማ amharic_poems — ሥነ-ግጥም
የቴሌግራም ቻናል አርማ amharic_poems — ሥነ-ግጥም
የሰርጥ አድራሻ: @amharic_poems
ምድቦች: ቴሌግራም
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.22K
የሰርጥ መግለጫ

____________________
ማንኛውንም ሃሳብ በ @Amharicpoembot ይላኩልን።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-23 11:22:27 ተጣልተን-ተኳርፈን

ተጣልተን-ተኳርፈን
ተኳርፈን-ተጣልተን
"ሴጣን ነህ !!" ብለሺኝ
"ሴት አይረባም !!" ብዬ
አንጎራጉራለሁ...
አፍዝዞኝ ስቃዬ
አንቺ ልጅ-አንቺ ልጅ
አንቺ ልጅ አንቺዬ

መንግስቱ ለማ
2.3K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 21:41:28 ተወኝ
(ጸጋዬ ገብረ መድኅን)

ላታስታምም አትመመኝ
ላትወስደኝ አታንጠልጥለኝ
ይቅር፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ጋሽዬ፥ አልወድሽም በለኝ።
እጅ እጅ አልበል አታባክነኝ
ባክህ፥ ወንድ ነው ቆራጡ፥ እንትፍ-እርገህ ተወኝ።
አየህ፥ እንዳንተ አባት አለኝ
ሴት በወለድኩ ተዋረድኩ፥ ረከስኩ ቀለልኩ እሚለኝ፥
እኔም እንዳንተ እህት አለኝ
ሥጋሽን ሳይሆን ልብሽን፥ ከፍተሽ ጥለሽ ነው እምትለኝ
እና ተወኝ፥ ባክህ ተወኝ፤
እንዳንተ እኔም አለኝ እናት
የሴት ቁንጮ እምመስላት
ጐረቤት ፊት እምታፍር፥ እንዲህ ሆነችልሽ ሲሏት!
እና፥ አልሆንሽም በለኝ
ባክህ አንጀቴን ቁረጠኝ
ፍቅር እንደሁ የኔ ይበቃል፥ ላንተም ለኔም እኔው ልውደድ
ከዘመድ ግንባር ደብቄ፥ እኔ ለብቻዬ ልንደድ፥
ብቻ፥ ከወጥመድህ ለየኝ
አልችልህም፥ ንቀህ ማረኝ
ካንተም ከስሜም ከቤቴም፥ ያጣሁ ብኩን አታድርገኝ፥
ባክህ፥ አንጀቴን ቁረጠኝ
ተወኝ፥ ተወኝ፥ ተወኝ።
---------------------------
3.4K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 08:57:13 ዝኑፍ ወቀሳ !
( በረከት በላይነህ )

ይለኛል ታዛቢ...
"በእኛ ተረማምዶ - ስኬቱን ሸመተ ፤
ሲመቸው፣ ሲደላው - ትቶን ሰነበተ ! "
ይለኛል ታዛቢ...
"አቅፈን አሳድገን - ከሰው መሐል
ለየን ፤
አለፈለትና - ዞር ብሎም አያየን !"
እኔ ግን እላለሁ !..
"ስህተት የለብኝም ፤
ያለፍኩበት ሁሉ አላሻገረኝም ፤
የረገጥኩት ሁሉ አልተሸከመኝም !"
10.9K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 08:54:42 ዓለሙ ሰልችቶኝ

ዓለሙ ሰልችቶኝ ሰው ሴቱ ወንዱ፤
ሐበሻው ፈረንጁ ትግሬው አማራው፤
አዳሜ ባጭሩ፤
ነገር ክርክር
ፌዙ ቀልዱ ሣቁ ፉከራው ጉራው፤

ሽሙጥና አሽሙሩ ሐሜት ቅናቱ፤
አለመስማማት፤
አለመገባባት፤

ዛፍና ቅጠሉን ሰማዩን ለማየት፤
የሣሩን መዓዛ ሽቶውን ለማሽተት፤
እዚያ ለመንጋለል ካሳብ ለማረፍ፤
በተንቀዠቀዠ ውሻ'ፍ ልለከፍ፤
ማረፍያ ለመሆን ለርግቦቹ ኩስ፤
ለማጨመታተር የሱሬየን ተኩስ ፤
የመንፈስ ጸጥታን ሰላምን አደን፤
ወደ ጫከው ገባሁ ታቅፌሽ አንቺን።

(መንግስቱ ለማ፡ የግጥም ጉባዔ ፡ 1955)
10.0K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-08 08:54:22 የመጀመሪያ ቀን

አየችው ተያዩ
አየና ወደዳት
ቀኑ ማታ ነበር
ወደ ሆቴል ሄዱ
ሁለት እራት መጣ
ብርጭቆው ተጋጨ
አየችው ተያዩ
አያት ተሳሳቁ
በጠረጴዛው ስር
ጭኗ ጭኑን ነካው
አየችው ፈገገ
እጇን በእጁ ያዘው
ጠበቅ አደረጋት
ጠበቅ አረገችው
ከፈሉና ወጡ
በከሰለው ሌሊት
ሁለቱ ነደዱ
ታፋቸው ጋለ
ቤቱ ተቃጠለ
ፍራሹ ነደደ
ፍቅር ተያያዘ፡፡

(ገብረክርስቶስ ደስታ)
8.4K views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-07 08:37:24 እቴቴ
--------
(ደበበ ሰይፉ)
ድሮ ነው ፊት
በልጅነቴ ሰዐት፤
“ፉራፉሬ” ከማበርበት ቦታ
መጥታ
ትጠራኝ ነበር ያች እቴቴ
የጎረቤቴ፤
“ቡጡ ና፣ ወንዝ እንውረድ
ሸንኮራ ቆርጨልህ እንደትጎምድ…”
“እሺ እቴትዬ” ብዬ
ጣሳውን ከእጅዋ ተቀብዬ
እከተላታለሁ ወንዝ እቴቴን
እቴቴን- የጎረቤቴን፡፡
ውሃውን
ፀሐይዋ ስታፀኸየው
በወርቅ መርገፏ ስታጌጠው
እቴቴም
ጨርቋን ስታንጠፈጭፈው
ስታሽ ስትጠመዝዘው
ስትዘረጋ ስትቀለብሰው፤
ደሞም ስትዘፋፍነው
“የኔ ቤት እቆላ ያንተ ቤት አፋፉ
ልቤን አመጡልህ እየደጋገፉ”
ስትለው… ስትለው
ትንሹን ልቤን እንዴት ነበር ደስ የሚለው
ደስ የሚለው?
ታዲያ አፍታም ሳትቆይ እቴቴ
እቴቴ የጎረቤቴ
ዘረረረረር አድርጋ ልብሷን፣
ውሃ ውሃ እሚል ጨርቋን
ሣሩም ላይ ጉቶውም ላይ
በየቅርንጫፉም ላይ፣
ትለኛለች እኔን
እኔን ትንሹን ቡጡን
ውሃ ውስጥ የምንቦራጨቀውን፤
“እስቲ ደግሞ ተራዬን
እኔ ልታጠብ ገላዬን
አፋፏ ላይ ቁምልኝ
መንገድ መንገዱን እይልኝ
ሰው አለመምጣቱን ጠብቅልኝ … ”
እሺ ብዬ ዲዲዲዲ ወዳፈፏ
እሷም ፈታ ፈታ መቀነቷን
ገልመጥ ገልመጥ ዙሪያዋን
ፍትት ፍትት ፍትትትት ሻሿን
ግልብ ግፍፍ ውልቅልቅ ቀሚሷን
ሙልጭልጭልጭ ውስጥ ልብሷን
ብቅ ጥልቅ ብቅ ጥልቅ ራቁቷን፤
እኔም ዐየት - ዐየት መንገዱን
ገረፍ ገረፍ - ደሞ ወንዙን
እቴትዬ እርቃኗን የምትንቦራጨቅበቱን፤
ጸጉሯን ወደ ኋላዋ እየሳበች እየጎተተች
ጡቶቿን ለፀሐይዋ እየሰጠች እየለጠጠች
ኋላዋንም ነካ ነካ — ነካ እያደረገች
ስትጫወት እያሾለቅሁ አየት … አየት
ደግሞ መንገዱንም መልከት… መልከት፤ …
ታዲያ በጉርምስና ዘመኔ
ያ የጥንቱ ትይታ ተመልሶ መጣ ካይኔ
የረሳኋት እቴቴ
ብዥ ትልብኝ ጀመር ከፊቴ፤…
ወንዙ ውስጥ ስትንቦራጨቅ
ጸጉሯን ወደ ኋላዋ እየሳበች እየጎተተች
ጡቷን ለፀሐይዋ እየሰጠች እየለጠጠች
ኋላዋንም ነካ – ነካ እያደረገች፤…
------------
1964
(ከ"የብርሃን ፍቅር" ፣ ገፅ 42 የተወሰደ)
7.8K views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 21:03:00 መጥኔ

ጥፍሬ ተሰንጥቆ ፣ ቆዳዬ ተልጦ
የ'ግሬን መድማት ያዩ
እንቅፋት መቶት ነው ፣ በማለት ታበዩ
ጉዳዩን ሳያጤን
ነገሩ ሳይገባው ፣ ለሚሰጥ ብያኔ
ለጥፋቱ ሁሉ ምክንያት ለሚሻው
ለሰው ልጅስ መጥኔ.....
አስተውሎ 'ማይሄድ ፣ ችኩል በመሆኔ
እንቅፋት መች መታኝ ፣ የመታሁት እኔ

(አቤል እና መሃመድ የጋራ መድብል፤ ከ. . . እስከ)

@amharic_poems
7.4K viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-05 21:02:55 የ ገ ዢ ኪ ሳ ራ


ይህ ሰፊ ገበያ!
በመንፈስ ተሞልቶ በፍቅር ሲጣራ!
ሸማች የሚጋፋው ቅራቅንቦ ተራ።

“ያ ስንት ነው?” ይላል፣
“ይሄኛውስ?” ይላል፤
የብልጭልጭ አይነት ያነሳል ይጥላል።

ከመንፈስ ገበያ
የውበት ጥሬ እቃ ሞልቶ ተትረፍርፏል፤
ሸማች ግን ልብ የለው
ለኮልኮሌ ፍቅር ማልዶ ተስልፏል።

“ወዴት ነህ?" አይባል -
“ወዴትም! ነው መልሱ!
“ምን በላህ?" ይሉታል -
“ምንም! ልትል ነፍሱ።

እንዲያውም ካሰኘው!
ምን እንደሚፈልግ ፈፅሞ ይዘነጋና፤
“ፀሐይ ስጡኝ!” ብሎ ብቅ ይበል ማምሻውን!
ሰልፈኛ ነውና 'ከጨረቃ ቆርሶ' ይወስዳል ድርሻውን።

የሸማች ሕሊናን መምስል ከሸፈነው፤
ገበያ መታየት ከመግዛት እኩል ነው።

የጠየቀም ገዝቶ፣ የከፈለም ገዝቶ፣
የተላከም ገዝቶ፣ የላክም ሽምቶ፤
እዚያው ይሞታታል!
ያልሞላ ቅርጫቱን ለአምሳዮቹ ትቶ።

ይኸው መጨረሻው !
ሽማቹ ለገላው እየተጨነቀ፣
ገዢው ለብልጭልጭ እየተደነቀ፤
የመንፈስ ከፍታ ተሽርሽሮ አለቀ።



(በረከት በላይነህ - የመንፈስ ከፍታ)


@amharic_poems
7.1K viewsedited  18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-04 20:30:42 ቀለም ያዘ ልቤ !

ከእምነት - ተለይቶ
ከፍቅር - ተ'ፋቶ
ሰው ፈርቶ - ሰው ጠልቶ
ቀለም ላይቀበል- ምሎ ተገዝቶ
የተሸሸገውን
የተደበቀውን
አገኘሽውና የልቤ ስፍራውን ፣
አንኳኩተሽ - ብትከፍችው
ከፍተሽ - ብታጸጂው
አጽድተሽ - ብታጥኚው
አጥነሽ - ብታጠምቂው
የተሸሸገበት - ምሽጉን ናደና
ፊደል አልቀበል - ማለቱ ቀረና
ለእውቀት ተሸንፎ - ልቤ እጁን ሰጠና፣...
በአንቺው ፍቅር ጠርቶ
በአንቺው እውነት ጸድቶ
በእምነትሽ ተ'ረቶ
"መውደድ" ተፃፈበት፦
ቀለም ያዘ ልቤ ፤ ልብሽን አግኝቶ።

ገጣሚ ጌትነት እንየው
ከዕውቀትን ፍለጋ የግጥም መድብል የተወሰደ


@amharic_poems
6.9K viewsedited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-03 20:14:24 ይድረስ ላገሬ ሰው

በሆነ ባልሆነው
በጩኽት በሆታ ሲበዛ መፈክር
ባላየህው ዶሴ ባላወከዉ ነገር
መሃላቸዉ ገብተህ አብረህ አትጨፍር
ያገሬ ሰው ጠርጥር...
ጥልቅ ጉድጓድ ምሰው
ልክ እንደ መቃብር
ይደፉህ ይሆናል ከመፈክሩ ስር!!!

(ሰለሞን ሳህለ
የልብ ማኅተም
2010 ዓም)


@amharic_poems
7.0K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ