Get Mystery Box with random crypto!

መጥኔ ጥፍሬ ተሰንጥቆ ፣ ቆዳዬ ተልጦ የ'ግሬን መድማት ያዩ እንቅፋት መቶት ነው ፣ በማለት ታበዩ | ሥነ-ግጥም

መጥኔ

ጥፍሬ ተሰንጥቆ ፣ ቆዳዬ ተልጦ
የ'ግሬን መድማት ያዩ
እንቅፋት መቶት ነው ፣ በማለት ታበዩ
ጉዳዩን ሳያጤን
ነገሩ ሳይገባው ፣ ለሚሰጥ ብያኔ
ለጥፋቱ ሁሉ ምክንያት ለሚሻው
ለሰው ልጅስ መጥኔ.....
አስተውሎ 'ማይሄድ ፣ ችኩል በመሆኔ
እንቅፋት መች መታኝ ፣ የመታሁት እኔ

(አቤል እና መሃመድ የጋራ መድብል፤ ከ. . . እስከ)

@amharic_poems