Get Mystery Box with random crypto!

የ ገ ዢ ኪ ሳ ራ ይህ ሰፊ ገበያ! በመንፈስ ተሞልቶ በፍቅር ሲጣራ! ሸማች የሚጋፋው ቅራ | ሥነ-ግጥም

የ ገ ዢ ኪ ሳ ራ


ይህ ሰፊ ገበያ!
በመንፈስ ተሞልቶ በፍቅር ሲጣራ!
ሸማች የሚጋፋው ቅራቅንቦ ተራ።

“ያ ስንት ነው?” ይላል፣
“ይሄኛውስ?” ይላል፤
የብልጭልጭ አይነት ያነሳል ይጥላል።

ከመንፈስ ገበያ
የውበት ጥሬ እቃ ሞልቶ ተትረፍርፏል፤
ሸማች ግን ልብ የለው
ለኮልኮሌ ፍቅር ማልዶ ተስልፏል።

“ወዴት ነህ?" አይባል -
“ወዴትም! ነው መልሱ!
“ምን በላህ?" ይሉታል -
“ምንም! ልትል ነፍሱ።

እንዲያውም ካሰኘው!
ምን እንደሚፈልግ ፈፅሞ ይዘነጋና፤
“ፀሐይ ስጡኝ!” ብሎ ብቅ ይበል ማምሻውን!
ሰልፈኛ ነውና 'ከጨረቃ ቆርሶ' ይወስዳል ድርሻውን።

የሸማች ሕሊናን መምስል ከሸፈነው፤
ገበያ መታየት ከመግዛት እኩል ነው።

የጠየቀም ገዝቶ፣ የከፈለም ገዝቶ፣
የተላከም ገዝቶ፣ የላክም ሽምቶ፤
እዚያው ይሞታታል!
ያልሞላ ቅርጫቱን ለአምሳዮቹ ትቶ።

ይኸው መጨረሻው !
ሽማቹ ለገላው እየተጨነቀ፣
ገዢው ለብልጭልጭ እየተደነቀ፤
የመንፈስ ከፍታ ተሽርሽሮ አለቀ።



(በረከት በላይነህ - የመንፈስ ከፍታ)


@amharic_poems