Get Mystery Box with random crypto!

ቀለም ያዘ ልቤ ! ከእምነት - ተለይቶ ከፍቅር - ተ'ፋቶ ሰው ፈርቶ - ሰው ጠልቶ ቀለም ላይቀበ | ሥነ-ግጥም

ቀለም ያዘ ልቤ !

ከእምነት - ተለይቶ
ከፍቅር - ተ'ፋቶ
ሰው ፈርቶ - ሰው ጠልቶ
ቀለም ላይቀበል- ምሎ ተገዝቶ
የተሸሸገውን
የተደበቀውን
አገኘሽውና የልቤ ስፍራውን ፣
አንኳኩተሽ - ብትከፍችው
ከፍተሽ - ብታጸጂው
አጽድተሽ - ብታጥኚው
አጥነሽ - ብታጠምቂው
የተሸሸገበት - ምሽጉን ናደና
ፊደል አልቀበል - ማለቱ ቀረና
ለእውቀት ተሸንፎ - ልቤ እጁን ሰጠና፣...
በአንቺው ፍቅር ጠርቶ
በአንቺው እውነት ጸድቶ
በእምነትሽ ተ'ረቶ
"መውደድ" ተፃፈበት፦
ቀለም ያዘ ልቤ ፤ ልብሽን አግኝቶ።

ገጣሚ ጌትነት እንየው
ከዕውቀትን ፍለጋ የግጥም መድብል የተወሰደ


@amharic_poems