Get Mystery Box with random crypto!

ይድረስ ላገሬ ሰው በሆነ ባልሆነው በጩኽት በሆታ ሲበዛ መፈክር ባላየህው ዶሴ ባላወከዉ ነገር | ሥነ-ግጥም

ይድረስ ላገሬ ሰው

በሆነ ባልሆነው
በጩኽት በሆታ ሲበዛ መፈክር
ባላየህው ዶሴ ባላወከዉ ነገር
መሃላቸዉ ገብተህ አብረህ አትጨፍር
ያገሬ ሰው ጠርጥር...
ጥልቅ ጉድጓድ ምሰው
ልክ እንደ መቃብር
ይደፉህ ይሆናል ከመፈክሩ ስር!!!

(ሰለሞን ሳህለ
የልብ ማኅተም
2010 ዓም)


@amharic_poems