Get Mystery Box with random crypto!

ከድር ኩሊባሊ ከአፄዎቹ ጋር ይቆያል !! የአፄዎቹ አምበል ያሬድ ባየ ወደ ባህርዳር ከነማ ማቅናቱ | Amhara Sport

ከድር ኩሊባሊ ከአፄዎቹ ጋር ይቆያል !!

የአፄዎቹ አምበል ያሬድ ባየ ወደ ባህርዳር ከነማ ማቅናቱን ተከትሎ አጣማሪው ከድር ኩሊባሊም እንደሚያመራ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው።

ባለፈው አመት ከድር ኩሊባሊ በአፄዎቹ ቤት ሁለት ዓመት የሚያቆየውን ኮንትራት መፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ተጨዋቹ አሁን ላይ ከፋሲል ከነማ ጋር የሚያቆየው የአንድ ዓመት ውል ይቀረዋል።ይሄን ተከትሎ ተጨዋቹ ወደየትኛውም ክለብ የሚሄድበት ዕድል የለም።

የጣናው ሞገዶች የኩሊባሊ ፈላጊ መሆናቸው እርግጥ ቢሆንም በመጪው ዓመት የአስቻለው ታመነ አጣማሪ ሆኖ በአፄዎቹ ቤት ይቆያል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ
https://t.me/AmharaSport

@AmharaSport