Get Mystery Box with random crypto!

ባህርዳር ከነማ ያሬድ ባዮን አስፈረመ የፋሲል ከነማው አምበል ያሬድ ባየ በይፋ የጣናው ሞገድ | Amhara Sport

ባህርዳር ከነማ ያሬድ ባዮን አስፈረመ

የፋሲል ከነማው አምበል ያሬድ ባየ በይፋ የጣናው ሞገድ ባህርዳር ከነማ የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚ ሆኖ ሞገዶቹን ተቀላቅሏል።

የአፄዎቹና የዋሊያዎቹ ግዙፉ ተከላካይ ያሬድ ባየ በፋሲል ከነማ ቤት ለመቆየት ውሉን እንደሚያራዝም ሲጠበቅ ውሃ ሰማያዊውን ባህርዳር ከነማ በይፋ ተቀላቅሏል።

ባህርዳር ከነማዎች የቀድሞውን የአፄዎቹን አምበል ያሬድ ባየን በሁለት አመት ኮንትራት ውል የዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚ በማድረግ የተከላካይ ክፍላቸውን የበለጠ ያጠናከሩበትን ምርጥ ዝውውር አጠናቀዋል ።

በበርካታ የአፄዎቹ ደጋፊዎች ተወዳጅ የሆነው ያሬድ ባየ ወደ ባህርዳር ከነማ ማምራቱ ለፋሲላውያን አስደንጋጭ ዜና ቢሆንም በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ላለመውረድ ለተጫዎቱት የጣና ሞገዶቹ ደጋፊዎች ልብን በደስታ የሚያሞቅ የዝውውር መረጃ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ
https://t.me/AmharaSport


@AmharaSport