Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል የውድድር አመቱን በ42 ነጥቦች 6ኛ ደረጃን ይዘው ያጠ | Amhara Sport

ኢትዮጵያ ቡና ሁለት ተጫዋቾችን አስፈርሟል

የውድድር አመቱን በ42 ነጥቦች 6ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁት ቡናማዎቹ በዝውውር መስኮቱ የመጀመሪያ ቀን ሁለት ተጫዋቾችን ከሰበታ ከተማ ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል ።

ሁለቱ ተጫዋቾች በሰበታ ከተማ መልካም እንቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩት የግራ መስመር ተከላካዩ ኃይለሚካኤል አደፍርስ እና አማካኙ አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ ሲሆኑ በቡናማዎቹ ቤት ለሶስት አመታት የሚያቆያቸውን ኮንትራት ፈርመዋል ።

ኃይለሚካኤል አደፍርስ ከ2011 ጀምሮ እከተጠናቀቀው የውድድር አመት መጨረሻ ድረስ በሰበታ ከተማ መጫወት የቻለ ሲሆን በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች እና በዋናው ብሄራዊ ቡድንም መመረጥ ችሎ ነበር ። ተጫዋቹ በውድድር አመቱ 25 ጨዋታዎችን አድርጎ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል ።

አብዱልሀፊዝ ቶፊቅ በደደቢት የታዳጊ ቡድኖች እና ዋናው ቡድን ተጫውቶ በ2013 ዓ.ም ሰበታ ከተማን መቀላቀል ችሏል ። በክለቡም ጥሩ ሁለት አመታትን ማሳለፍ የቻለ ሲሆን በ2013 ባህርዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረው የሴካፋ ውድድር ላይ የብሔራዊ ቡድኑ አባል ነበር ። ተጫዋቹ በውድድር አመቱ በሰበታ ከተማ 26 ጨዋታዎችን በማድረግ አንድ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

Hatrick Sport

ቴሌግራም https://t.me/AmharaSport