Get Mystery Box with random crypto!

የአጥቂው ምንይሉ ወንድሙ ቀጣይ ማረፊያ ? መከላከያ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተጨዋቹን ፊርማ ለማግ | Amhara Sport

የአጥቂው ምንይሉ ወንድሙ ቀጣይ ማረፊያ ?

መከላከያ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ የተጨዋቹን ፊርማ ለማግኘት ተፋጠዋል።ወላይታ ድቻ ውሉን ለማራዘም ድርድር ጀምሯል፣እስካሁን ግን ስምምነት ላይ አልደረሱም።

የቀድሞው የባህርዳር ከነማ ፣ መከላከያ ፣ መቀሌ 70 እንደርታና ወላይታ ድቻ አጥቂ የነበረው ምንይሉ ወንድሙ ከወላይታ ድቻ ጋር የነበረው ኮንትራት መጠናቀቁን ተከትሎ የበርካታ ክለቦች አይን ማረፊያ ሁኗል።

በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመራው መከላከያ እና የክፍሌ ቦልተና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አጥቂውን ምንይሉ ወንድሙ የክለባቸው የመጀመሪያ አዲስ ፈራሚ ለማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው።

ወላይታ ድቻዎች በበኩላቸው አሁንም የአጥቂያቸውን ኮንትራት ለማራዘም ድርድር መጀመራቸው እርግጥ ሁኗል ።

በወላይታ ድቻ የነበረውን ኮንትራት ያጠናቀቀው አጥቂ ምንይሉ ወንድሙ ቀጣይ ማረፊያ መከላከያ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወይስ ወላይታ ድቻ የሚለው ከወዲሁ ተጠባቂ ሁኗል።

የአጥቂው ቀጣይ ማረፊያ የቀድሞ ክለቡ መከላከያ ሊሆን እንደሚችል የበርካቶች ግምት ሁኗል።

ለተጨማሪ መረጃ የቴሌግራም ገፃችን ይቀላቀሉ
https://t.me/AmharaSport

@AmharaSport