Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኙ ባሕርዳር : ግን | Amhara Media Corporation

ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ከኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ጋር ብሔራዊ ሙዚየምን ጎበኙ

ባሕርዳር : ግንቦት 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ)ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴ እና የኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት ፍራንሲያ ማርኩዌዝ ብሔራዊ ሙዚየምን ጎብኝተዋል፡፡

በኮሎምቢያ ምክትል ፕሬዚዳንት የተመራው የልዑካን ቡድን ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን፥ በነበራቸው የቆይታ ጊዜ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየምን ጨምሮ ሌሎች በአዲስ አበባ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎችን ተዟዙረው ጎብኝተዋል፡፡

የጉብኝቱ መርሐ ግብር በቱሪዝም ሚኒስቴር እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጋራ ትብብር የተዘጋጀ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck