Get Mystery Box with random crypto!

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በ 4 ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ የተሳታፊዎች ልየታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵ | Amhara Media Corporation

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በ 4 ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ የተሳታፊዎች ልየታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ ።

አዲስ አበባ፡ ግንቦት 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) መግለጫውን የሰጡት ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መሥፍን አረዓያ በጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሀረሬ ክልሎች እና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የተሳታፊዎች ልየታ ተግባር እንደሚጀመር ገልፀዋል።

ጉዳዩ ሀገራዊ ቢሆንም ሁሉንም ዜጎች ማሳተፍ ስለማይችል ዜጎችን በውክልና ማሳተፍ የግድ መሆኑን የተናገሩት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ወረዳዎች 50 ሰዎችን መርጠው ይልካሉ። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንም በውክልና የሚሳተፉበትን አሠራር መዘርጋታቸውንም ነው የተናገሩት ።የሃይማኖት ተቋማት፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን እና የንግድ ተቋማትም በልየታ ሥራው ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል ።

ሥራ በሚጀመርባቸው አካባቢዎች ህኅብሰተሰቡ ተባባሪ እንዲሆን ሚዲያዎች ስለ ሀገራዊ ምክክሩ መረጃ እንዲሰጡም ዋና ኮሚሽነሩ ጥሪ አስተላልፈዋል። መረጣው እጅግ አካታች እና ተአማኒነት የተሞላበት እንደሚሆንም ተገልጿል ።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
ዲስከቨር አማራ አሚኮ https://www.facebook.com/DiscoverAmharaAMECO
አሚኮ ስፖርት https://www.facebook.com/AMECOSport
አሚኮ እውነታ ማጣሪያ https://www.facebook.com/AMECOFactCheck