Get Mystery Box with random crypto!

'በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መካከል ሲደረግ የነበረው የልምድ ልውውጥ ጠቃሚ ግብዓት የ | Amhara Media Corporation

"በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መካከል ሲደረግ የነበረው የልምድ ልውውጥ ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበት ነው" አቶ ተስፋዬ በልጅጌ

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መካከል ሲደረግ የነበረው የልምድ ልውውጥ ለምክር ቤቱ ቀጣይ ሥራ ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበት መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ገለጹ፡፡

በሁለቱ ምክር ቤቶች መካከል ሲደረግ የነበረው የልምድ ልውውጥ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ተካሂዷል።

በመድርኩ ላይ የተገኙት አቶ ተስፋዬ የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ ልምድ ልውውጥ ለማድረግ ኢትዮጵያን በመምረጣቸው አመስግነው ፤ በነበረው ጊዜም ያገኙት ልምድ ለቀጣይ ምክር ቤታዊ ሥራ አጋዥ የሚኾኑ ግንዛቤዎችን ስለመውሰዳቸው ጠቅሰዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት ወዳጅነት ዘመናትን የተሻገረ ታሪክ ያለው በመሆኑ ይህንን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደዚህ ዓይነት ልምድ ልውውጦች አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ወደ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ማሸጋገር እንደሚያስፈልግም ነው ያስረዱት፡፡

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ አባላትም በነበራቸው ቆይታ እና በልምድ ልውውጡ መደሰታቸውንና ቀጣይነት እንዲኖር ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ላለፉት ሶስት ቀናት በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ፓርላማ መካከል የልምድ ልውውጥ ሲደረግ መቆየቱ ከምክር ቤቱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!