Get Mystery Box with random crypto!

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተገለፀ። ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2015 ዓ | Amhara Media Corporation

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተገለፀ።

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ)በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ኹኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የኾኑ ተማሪዎች ፈተና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ የትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጿል።

ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት መላክ እንዳለበት ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንደሚያዝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ተማሪዎችም በ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ኾነው ለመገኘት የሁለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማሥተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የኾኑ ተማሪዎችን ለይተው እስከ ሰኔ 30/2015 ዓም እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ሥራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት መርሐ ግብር የተስተካከለ እንዲኾን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!