Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያግዝ መንገድ ለመገንባት ስምምነት ተ | Amhara Media Corporation

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን

የሚያግዝ መንገድ ለመገንባት ስምምነት ተፈራረሙ

ባሕር ዳር: ግንቦት 11/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የፓሎች - ማቲያንግ - ማይውት - ፓጋክ መንገድን ለመገንባት በጁባ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

መንገዱ ምዕራብ ኢትዮጵያን ከሰሜን ምሥራቅ ደቡብ ሱዳን ጋር የሚያገናኝ የፍጥነት መንገድ መኾኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማርዲያት የተገኙ ሲሆን÷ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ.ር) እና የደቡብ ሱዳን የገንዘብ ሚኒስትር ዴር ቶንግ ንጎር (ዶ.ር) መፈራረማቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ÷ "ተስፋችን እርስ በእርስ ለመረዳዳት በጋራ መንቀሳቀስ ነው፤ ሕዝባችን ማየት የሚፈልገው ይህንን ነው፤ ይህ ሕዝባችንን የሚያስተሳስርና ፍላጎቶቹን የሚያሟላ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት ነው ብለዋል"።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ.ር) እንደተናገሩት የዚህ መንገድ መገንባት የሀገራቱን የንግድ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ ሰው ሠራሽ የድንበር መለያየትን በማስቀረት የእህትማማች ሀገር ሕዝቦችን ይበልጥ ያቀራርባል።

በፊርማ ሥነ ሥርአቱ ወቅት ሀገራቱ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ውህደትን የሚያሳልጡ የኤሌክትሪክና የነዳጅ ማስተላለፊያን ጨምሮ ሌሎች የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን ለማጠናከር ሃሳብ ተለዋውጠዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!