Get Mystery Box with random crypto!

ለ32ኛ ዙር የአማራክልል መደበኛ ፖሊስ ምዝገባ ተጀምሯል #የመመልመያ_መስፈርቶች፦ 1)ዜ | የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

ለ32ኛ ዙር የአማራክልል መደበኛ ፖሊስ ምዝገባ ተጀምሯል

#የመመልመያ_መስፈርቶች

1)ዜግነት ኢትዮጵያዊ የሆነ / የሆነች

2) ከሚኖርበት ቀበሌ 2 አመት እና ከዛ በላይ የኖረና የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ማቅረብ የሚችል /የምትችል

3)ለሀገሪቱ ህጎች ታማኝና ተገዥ የሆነ/የሆነች

4)ከማንኛውም ደባል ሱስ ነጻ የሆነ/ች

5, የአማራ ክልል መደበኛ ፖሊስ ሆኖ ለመስራት ፍላጎት ያለው ያላትና ለመሰልጠን ፍቃደኛ የሆነ / ች በክልሉ ዞኖች ፣ወረዳዎች ተመድቦ መስራት ፍቃደኛ የሆነ/ች

6) መልካም ስነ_ምግባሩ / ሯ የተመሰከረትላት / ለት

7)በማኛውም ወንጀል ተከሶ ያልተቀጣ / ያልተቀጣች ክርክር የሌለበት

8/የትምህርት ደረጃው በድሮው 1ዐኛ ያጠናቀቀ እና የማትሪክ ውጤት ማቅረብ የሚችል በአዲሱ 12ኛ ክፍል እና በዚያ በላይ

9)ዕድሜ ከ18 ዓመት ያላነሰች ከ25 ዓመት ያልበለጠች

10) ማሰልጠኛ ማዕከሉ በስልጠና ወቅት የሚያቀርበውን ምግብ ለመመገብ ፍቃደኛ የሆነ /ች

11)የተሟላ ቁመናና ጤና ያለው / ያላት በህክምና የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል

12) ቁመት ለወንድ 1.65 ሜትር ለሴት 1.55 ሳ.ሜትር እና በላይ የሆነ/የሆነች

13) ክብደት ለወንድ ከ50 ኪ .ግራም ያላነስ ከ70 ኪ.ግራም ያልበለጠ _ ለሴት ከ45 ኪ.ግራም
ያላነሰች ከ65 ኪ.ግራም ያልበለጠች

14) ሴት ተመልማዮች ከእርዝና ነጻ ማረጋገጫ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በኮሌጁ ህክምና
በድጋሜ የሚረጋገጥ ይሆናል፤

15) በክልሉ ውስጥ በየትኛውም ቦታ ተመድቦ/ባ/ ለመስራት ፍቃደኛ የሆነች!
16) የክልሉን የስራ ቋንቋ መፃፍ እና መናገር የሚችል/የምትችል
17) ከስልጠና በኀላ 7 አመት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች ውል የሚወስድ
ምዝገባ ከግንቦት 1እስከ ግንቦት 25/9/2014 ዓ,ም

️ መመዝገብ የምትፈልጉ የደብረማርቆስ ወጣቶች በአቅራቢያችሁ ባሉ የደብረማርቆስ ፖሊስ ጣቢያዎች በስራ ሰዓት በመሄድ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።