Get Mystery Box with random crypto!

ፋኖነት ሕይወቱ ነው! ከምርጫ 97 ማግስት ገና በልጅነቱ ነው የአርበኝነት ትግሉን የተቀላቀለው! | የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

ፋኖነት ሕይወቱ ነው!

ከምርጫ 97 ማግስት ገና በልጅነቱ ነው የአርበኝነት ትግሉን የተቀላቀለው! በአማራ ተጋድሎ ምልክት የነበረው የጎቤ ጦር አካል ነበር። ያውም ቀኝ እጁ!
በአርበኝነት ትግሉ ደጀኔ ማሩን ሊያፍኑ የመጡ አንድ መኪና የአፋኝ ቡድን አባላት መንገድ ላይ ተመትተው አላማቸው የከሸፈው አጋዬ በሚመራው ጦር ነበር።

ከተመቱት መካከል የቆሰሉትን ታዲያ ከሕዝብ መኪና ጠይቀውም ወደ ጎንደር ሆስፒታል ልከዋቸዋል። መንግስት የተባለው "ሽፍታ" ብሎ አስከሬን በሚጎትትበት ወቅት ፋኖዎቹ እነ አጋዬ ሊገድላቸው የመጣን ቁስለኛ አሳክመዋል።

በ2008 ዓ/ም በነበረው ንቅናቄ ወደ አማራ ክልል መጥተው ንፁሃንን ሊያፍኑ የትህነግ የትህነግ የአርማጭሆን በርሃ ሳያልፉ መምገድ ላይ የቀሩት በእነ አጋዬ ጦር ነበር። እነ አጋዬ ጫካ ሆነውም የከተማውን ሕዝብ ጠብቀዋል።

አጋዬ አድማሱ ለእስር ተዳርጎ ማዕከላዊና ሌሎች እስር ቤቶችንም አይቷል። ሲመለስ ወደ ግብርና ስራው ገብቷል። ጠላት ሲመጣ ደግሞ የግብርና ስራውን ትቶ በርካታ ጀብዱዎችን ሰርቷል። ዛሬ የአማራ ክልል በሕልውና ትግሉ ላደረገው አስተዋፅኦ ሸልሞታል። ሲያንሰው ነው! አጋዬ የሕልውና ትግሉ ፋኖ ብቻ አይደለም። ፋኖነት ያደገበት ነው። ፋኖነት የኖረበት ሕይወቱ ነው!

https://t.me/Amhara_students_association