Get Mystery Box with random crypto!

የቀድሞዉ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን ግለ ታሪክ የማስታወሻ መጽሐፍ እየተመ | የአማራ ተማሪዎች ማህበር [አተማ]

የቀድሞዉ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን ግለ ታሪክ የማስታወሻ መጽሐፍ እየተመረቀ ነዉ!

በዶ/ር ሞላ ፈለቀ የተጻፈዉ ይህ የማስታወሻ መጽሐፍ የኮሚሽነር አበረ አዳሙን ከትዉልድ ቀያቸዉ እስከ በረሃ ትግላቸዉ ብሎም ህይወታቸው እስካለፈበት ዕለት የሚያትት ሲሆን ይህ መጽሐፍ በሃሳብ ሙሉ እንዲሆን የተለያዩ ማስረጃዎችም ተካተዉበታል።

በዚህ የመጽሐፍ ምረቃም የኢፌዲሪ የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌዉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ፤ፕሮፌሰር ሲሳይ አውጋቸውና የተለያዩ ከፍተኛ የክልል አመራሮች ምሁራኖች ተገኝተዋል።

የመጽሐፍ ምረቃዉን ሙሉ ፕሮግራም በአሻራ ሚዲያ ይጠብቁን።

( አሻራ ሚዲያ )