Get Mystery Box with random crypto!

#Facebook ፌስቡክ ታሊባንን እንደ አሸባሪ ቡድን እንደሚመለከተውና ከቡድኑ ጋር የተያያዙ መል | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

#Facebook

ፌስቡክ ታሊባንን እንደ አሸባሪ ቡድን እንደሚመለከተውና ከቡድኑ ጋር የተያያዙ መልዕክቶችን እንደሚያቅብ አስታወቀ።

ፌስቡክ ታሊባንን የሚያደንቁ ይዘቶችን፣ የቡድኑን መልዕክቶችን አግዳለሁ ብሏል።

ይህን ሳንሱር እንዲሠሩለት አንድ ልዩ የአፍጋኒስታን ባለሙያዎች ቡድን ማዋቀሩን እና በእነዚህ ባለሙያዎች እየታገዘ የታሊባን ይዘቶችን ወዲያውኑ ከፌስቡክ ሰሌዳዎች ላይ እንደሚያጠፋ ፌስቡክ ዝቷል።

ታሊባን ለዓመታት መልዕክቶቹን በመላው ዓለም ለማድረስ ፌስቡክን እንደ አንድ መገናኛ ብዙኃን ሲጠቀምበት ቆይቷል።

ታሊባን አሁን የመንግሥትን መዋቅር መቆጣጠሩ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ቡድኑን እንዴት ማስተናገድ እንዳለባቸው በድጋሚ እንዲያጤኑ እያደረጋቸው ነው።

የፌስ ቡክ ቃል አቀባይ ፥ "በአሜሪካ ሕግ ታሊባን አሸባሪ ቡድን ነው። ይህ ሕግ እኛም በዚያው ሁኔታ እንድናያቸው የሚያደርገን ነው። በመሆኑም ከታሊባን ጋር የሚያያዙ ማናቸውንም መልዕክቶች እናቅባለን" ብለዋል።

ፌስቡክ ዋንኛ የአፍጋኒስታን ቋንቋ የሆኑትን ዳሪ እና ፓሽቶን የሚናገሩ አፍጋኒስታዊያን ተወላጆችን ለዚሁ ተግባር ሲል መልምሎ፣ ቀጥሮ እያሠራ እንደሆነ ተናግሯል።

የፌስቡክ ኩባንያ እቀባውን ተግባራዊ የሚያደርገው በእህት ኩባንያዎቹ በኢንስታግራምና በዋትስአፕ የትስስር መድረኮች ጭምር ነው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@zena_tube11
@zena_tube11