Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ በጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ በጣለው በረዶ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምክንያት በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ተከስቶ በሰዉ ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።

ይህን ያሳወቁት የአ/አ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ናቸው።

ምክትል ከንቲባዋ በጎርፍ አደጋው በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን በመግለፅ ከልብ አዝኛለሁ ብለዋል።

- በአስኮ፣
- በአደይአበባ፣
- በጀርመን አደባባይና በጎልፍ ክለብ አካባቢ በደረሰው ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ እስከአሁን ድረስ መንገዶች ጭምር የተዘጋጉ ሲሆን የድንገተኛና የእሳት አደጋ ሰራተኞች በቦታዎቹ በመገኘት የከፋ ሰብዓዊ ጉዳት እንዳይደርስ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ሲሉ አሳውቀዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ተጎጂዎችንም ወደ ህክምና መስጫ በማጓጓዝ እና የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከክረምቱ ማየል ጋር ተያይዞ አስቀድሞ የመከላከል ስራዎችን እየሰራ የነበረ ቢሆንም የዛሬው አደጋ ተጨማሪ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ያመላከተ ነው ብለዋል።

ወ/ሮ አዳነች አሁን እንዳለው መረጃ በመጪዎቹ ቀናት ከፍተኛ መጠን ያለዉ የዝናብ ስርጭት ስለሚኖር ነዋሪዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ

@Amhara_Media_Corporation