Get Mystery Box with random crypto!

#Kabul የታሊባን ታጣቂዎች ካቡል ደጃፍ ቆመዋል። ለመሆኑን ከሰሞኑ በአፍጋኒስታን ምን ሆነ ? | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

#Kabul

የታሊባን ታጣቂዎች ካቡል ደጃፍ ቆመዋል።

ለመሆኑን ከሰሞኑ በአፍጋኒስታን ምን ሆነ ? በአጭሩ ...

- "ታሊባን" በአሜሪካ መራሹ ጦር እአአ ጥቅምት 2001 ነው ከስልጣን የወረደው ፤ ቡድኑ ኦሳማ ቢን ላደንን እና ሌሎች መስከረም 11 በአሜሪካ ላይ ከተፈፀመ ጥቃት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ግለሰቦች እና ቡድኖች ዒላማ ያደረገ ነበር።

- ታሊባን ከስልጣን የተገፋው አሜሪካ አፍጋኒስታን ላይ ባካሄደችው ወረራ ነው።

- የአሜሪካ እና ኔቶ ጦር ኃይሎች በአፍጋኒስታ ለ20 ዓመታት ያህል ቆይተዋል።

- የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን አፍጋኒስታን የነበሩትን የአሜሪካ ወታደሮች የማወጣት ውሳኔ አሳልፈው ወታደሮቻቸውን አስወጥተዋል።

- 20 ዓመታት በአፍጋኒስታን የነበሩት የአሜሪካ እና ሌሎች ኃይሎች /ኔቶ/ ከአፍጋኒስታን መውጣታቸው ተከትሎ ታሊባን የተለያዩ ከተሞችን ከአሁኑ መንግስት ማስለቀቅ ጀመረ።

- አሜሪካ በአፍጋን ያሉ ዜጎቿን ለማስወጣ 5 ሺህ የሚደርሱ ወታደሮችን ልካ በዛው ያሉ ዜጎቿን፣ በኤምባሲ የሚሰሩ ሰራተኞቿን እያስወጣች ነው።

- በአጭር ጊዜ ውስጥ ታሊባን በርካታ ከተሞችን ወሳኝ መስመሮችን ተቆጣጥሯ ፤ አሁን ደግሞ በመንግስት እጅ በብቸኝነት ቀርታለች የተባለችውን ካቡልን (ዋና ከተማ) ከቧል።

- ካቡል ዙሪያዋ በታሊባን ታጣቂዎች ተከባ ምጥ ላይ ነች። የታሊባን ታጣቂዎች በመዲናዋ መውጪያና መግቢያዎች ላይ ታጣቂዎቻቸው እንዲጠብቁ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

- የአፍጋኒስታን የሃገር ውሰጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ይደረጋል ፥ ለሽግግር መንግሥቱም ስልጣን ይሰጣል ብለዋል።

- ታሊባን ካቡልን በኃይል እንደማይወስድ ገልጿል፤ ከመንግስት ጋር ድርድር ላይ መሆኑንም አሳውቋል።

(ከቢቢሲ እና AFP የተውጣጣ)

@zena_tube11
@zena_tube11