Get Mystery Box with random crypto!

ዩኒሴፍ በአፋር ክልል በተፈናቃዮች ላይ ተፈጸመ የተባለው ግድያ እንዳስደነገጠው ገለጸ የተባበሩት | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

ዩኒሴፍ በአፋር ክልል በተፈናቃዮች ላይ ተፈጸመ የተባለው ግድያ እንዳስደነገጠው ገለጸ

የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በአፋር ክልል በጤና ተቋም እና ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የነበሩ ከ100 በላይ ህጻናትን ጨምሮ፤ 200 የሚልቁ ተፈናቃዮች ተገድለዋል መባሉ በእጅጉ እንዳስደነገጠው አስታወቀ። በአፋር እና በሌሎች የትግራይ አዋሳኝ ቦታዎች የሚደረገው ውጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ለህጻናት አስከፊ መሆኑንም ድርጅቱ ገልጿል።

ዩኒሴፍ በአፋር ክልል ተጠልለው በነበሩ ተፈናቃዮች ላይ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ በተመለከተ መግለጫ ያወጣው ዛሬ ሰኞ ነሐሴ 3፤ 2013 ነው። በድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ሄንሪታ ፎር ስም የወጣው ይኸው መግለጫ፤ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት በዚህ አካባቢ፤ ወሳኝ የምግብ አቅርቦቶች ወድመዋል መባሉንም ጠቅሷል።

የተመድ የህጻናት መርጃ ድርጅት በአፋር ክልል ተፈጸመ ስለተባለው ጥቃት እና ስለ ደረሰው ጉዳት በመግለጫው ቢጠቅስም፤ ድርጊቱን የፈጸመው አካል የትኛው ወገን እንደሆነ ከመግለጽ ተቆጥቧል። የአፋር ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባለፈው አርብ ሐምሌ 30 ባወጣው መግለጫ ለጥቃቱ የህወሓት ኃይሎችን ተጠያቂ አድርጎ ነበር።

@zena_tube11
@zena_tube11