Get Mystery Box with random crypto!

#Somali በሱማሊ ክልል በሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰልጥኑ የነበሩ የ | አዲስ ዘመን ጋዜጣ |Addis Zemen Vacancy

#Somali

በሱማሊ ክልል በሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል ሲሰልጥኑ የነበሩ የሶማሊ ክልል ሚሊሺዎች ዛሬ ተመርቀዋል።

የሻለቃ ከደር መሀሙድ የውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል በብርቆድ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ማሰልጠኛ ውስጥ ሲሰለጥኑ የነበሩ ሚሊሺያዎች ናቸው ዛሬ ተመረቁት።

የተመረቁት አጠቃላይ የሚሊሻዎች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ መረጃውን ይፋ ያደረገው የክልሉ ብዙሃን መገናኛ ያለው ነገር ባይኖርም በተሰራጩት ፎቶች መመልከት እንደተቻለው በርካታ ናቸው።

በምርቃው ስነስርዓት ላይ ፦
- የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ፣
- የሰላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ሁሴን ሃሺ፣
- የሶማሊ ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ፣
- የሶማሊ ክልል ልዩ ሀይል አዛዥ ም/ኮ መሀመድ አህመድ፣
- የሶማሊ ክልል ፖሊስ ኮ/ኮምሽነርና የዞን አስተዳደሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተው ነበር።

Photo Credit : SRTV

@zena_tube11