Get Mystery Box with random crypto!

Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት 🔑ቁልፍ ነዉ📖

የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayamidia — Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት 🔑ቁልፍ ነዉ📖 A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alhidayamidia — Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል📚ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት 🔑ቁልፍ ነዉ📖
የሰርጥ አድራሻ: @alhidayamidia
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.35K
የሰርጥ መግለጫ

#አላማችን ሙስሊሙን ኡማ ቀጥተኛዉን መገድ መምራት ነዉ
#ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት
ከቁርዓንና📖 ከሐዲሥ
ከታማኝ ዑለማዎች የሚሰጡ
ሙሃደራወችና ኢስላማዊ ግጥሞች
የነብያትና የሶሀባ ታሪኮች
ለእናቶቻችና ለእህቶቻችን አስደሳች
ዲናዊ ንግግሮችና ፈትዋ ይቀርቡበታል
#እዲሁም_ወቅታዊ_ኢስላማዊ_ጉዳዮችም_ይዳሰሳሉ
#ለማንኛዉም_ጥያቄና_አስተያየት_ካላቹ
@RidAmirsab

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-22 00:38:13 ወንድሜ ሆይ! እህቴ ሆይ! ልጆቻችን ከአላህ የተሰጡን አማናዎች ናቸው፡፡ አማናን በአግባቡ አለመያዝ ከአላህ ዘንድ ያስጠይቃል፡፡ መቼም የልጆች አስተዳደግ በኢስላም ያለው ቦታ የላቀ እንደሆነ አይሰወርም፡፡ ከልብስና ከጉርስ ባለፈ አጠቃላይ ጤናማ የሆነ አስተዳደግ እንደሚገባቸው ይታወቃል፡፡ ስለ አካላዊ ደህንነታቸው ከምንጨነቀው በበለጠ ስለ አእምሯዊና ስነልቦናዊ ጤንነታቸውም ልንጨነቅ ይገባል፡፡ ስለ አካዳሚ ትምህርታቸው ከምንጨነቀው በበለጠ ዘላለማዊ ህይወታቸውን ስለሚወስነው ስለ ዲናዊ ግንዛቤያቸውም ልንጨነቅላቸው ይገባል፡፡ ዛሬ ለጤናማ የልጆች አስተዳደግ የምናደርገው ጥረት ነገ ጤናማ ማህበረሰብ ይኖረን ዘንድ የመሰረት ድንጋይ ነው፡፡ በእርግጥ አሁን የፈለግኩት ስለ አጠቃላይ የልጆች አስተዳደግ ማውራት አይደለም፡፡ ይልቁንም “ጭራቅ መጣብህ!” “የሰው ጅብ መጣብህ”፣ “አያ ጅቦን እጠረዋለሁ” እያልን ልጆችን የምናስፈራራበት ውርስ ቢቀንስም ዛሬም አለ፡፡ በተጨማሪም አንዳንድ ከነጩ ሰው የሚመጣውን ሁሉ እንደወረደ የሚወስዱ ወላጆች ልጆቻቸው ሲረብሹ በአንድ ክፍል ቆልፎ በመዝጋት ለብቻ እያቆዩ የሚቀጡበት መንገድ አደጋ እንዳለው ማስታወስ ነው የፈለግኩት፡፡ ሀሳቡን የወሰድኩት ከታላቁ ዐሊም ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ረሒመሁላህ ነው፡፡ በአዲስ መስመር እንገናኝ፡-
“… ‘እንትን መጣብህ’ ‘እንደዚህ መጣብህ’ እያሉ በማስፈራራትና በማሸበር አንዳንድ መሀይማን ሰዎች በትንንሽ ልጆቻቸው ላይ የሚፈፅሙት አለ፡፡ ህፃኑ ፈሪ ሆኖ ይቀራል፡፡ ይሄ ፍርሃትና ርደት ከልቡ ይቀርና ባህሪው የሚሆን አለ፡፡ ሁሌ በፍርሃትና በጭንቀት ላይ ይሆናል፡፡ ይሄ እንግዲህ አባት በልጁ ላይ፣ እናት በልጇ ላይ የሚፈፅሙት ግፍ ነው፡፡
ኧረ እንዲያውም አንዳንድ ቂላቂሎች ህፃኑ ሲያጠፋ ብቻውን ከአንድ ክፍል ውስጥ አስገብቶ የሚዘጋ እንዳለ ተነግሮናል፡፡ ህፃኑ ይጮሃል፤ ነገር ግን አያዝንለትም፤ በሩንም አይከፍትለትም፡፡ ይሄ በጂን እንዲያዝ ከሚያደርጉ መንሰኤዎች ውስጥ ነው፡፡ ልክ በአንዳንድ በጂን በተለከፉ ልጆች ላይ ያለ ጂን እንደተናገረው ማለት ነው፡፡ ወላጆቹ በር ዘግተውበት ሲጮህ ጊዜ እንደያዘው የተናገረ አለ፡፡ ስለዚህ ለእንዲህ አይነት አደጋዎች መንሰኤ ከሚሆኑ ዛሬ ብዙ ሰዎች ከተዘፈቁባቸው ነገሮች ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡…”
ስለዚህ ልጆቻችን ቢቻል ከምክር በዘለለ ወደ ሌላ ቅጣት ልንገባ አይገባም፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ግን የምንቀጣበት መንገድ ጤናማ መሆኑን በውል መፈተሽ ይገባል፡፡ ዛሬ በልጆች ላይ የምንወስደው የተዛባ “ቅጣት”፣ ከብልሹ ቅጣትነቱ ባለፈ እነሱም በተራቸው በዚህ መልኩ ልጆቻቸውን እንዲቀጡ የተበላሸ ውርስ ማቀበል ነው፡፡ በእርግጥ “ልጆች በምንም መልኩ፣ የፈለገ ቢያጠፉ ሊነኩ አይገባቸውም” የሚለው አስተምህሮት ምክንያታዊ አይደለም፡፡ የሰው ልጅ ባህሪው ብዙ አይነት ነው፡፡ ስትመክረው የሚሰማ እንዳለ ሁሉ ለምክር ደንታ የሌለው ብዙ አለ፡፡ ከምክር ይልቅ ቁጣ የሚመልሰው በተጨባጭ አለ፡፡ ከዚህም አልፎ ካልተቀጣ በስተቀር ከጥፋቱ የማይታቀብ ብዙ ልጅ አለ፡፡ ገና ጥፋትን ሲያስብ የሚጠብቀውን ቅጣት ፈርቶ ሊቆም ይችላል፡፡ አዋቂውም እንዲሁ ነው፡፡ ህግ ባይኖርም የሰው ሐቅ የሚፀየፍ፣ ከሰው ላይ እጁን የማያሳርፍ ብዙ እንዳለ ሁሉ ቀጪ ህግ ባይር ኖሮ፣ በአጥፊዎች ላይ የሚወሰዱትን እርምጃዎች ባያይ ኖሮ ከጥፋት የማይመለስ ብዙ ሰው አለ፡፡ ይሄ ለማንም የማይሰወር ሐቅ ነው፡፡ ልጆችም እንዲሁ ናቸው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ልጆቻችሁን የሰባት አመት ልጆች ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፡፡ የአስር አመት ልጆች ሲሆኑ ደግሞ (ካልሰገዱ) ግረፏቸው” ማለታቸው ይህንን ሐቅ ፍንትው አድርጎ ያሳያልል፡፡ [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 5868] መቼም ለጠቢብ ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳይኮሎጂ አስተምራለሁ ብሎ የሚዳፈር አይኖርም፡፡ “ከልብ ወለድም አይናገምና፡፡ ይልቁንም እሱ (ንግግሩ) ረእይ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡” [አንነጅም፡ 3-4]
ስለዚህ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ልጆችን መቅጣት ተገቢ ነው፡፡ ባይሆን ከግምት ሊገቡ የሚገባቸው ነገሮች እንዳሉ ዐሊሞች ይጠቅሳሉ፡፡ እነሱም፡-
1. ልጆቹ ለቅጣት የደረሱ ሊሆኑ ይገባል፡፡
2. ቅጣትን የሚረዱ (የሚያውቁ) ሊሆኑ ይገባል፡፡ ቅጣትን የማይረዱ ከሆኑ እድሜያቸው ደረሰም አልደረሰም መቅጣቱ ተገቢ አይደለም፡፡
3. የሚቀጣው በምክር ወይም በቁጣና መሰል ነገሮች የማይመለሱ ከሆነ ነው፡፡
4. ቅጣቱ ሲያጠፉ ብቻ ሊሆን ይገባል፡፡ አንዱ ባጠፋውም ሌላውንም መጨመር፣ በማያስቀጣ ጥፋት መደብደብ፣ የውጭ ብስጭትን ልጆች ላይ ማራገፍ፣ ወዘተ ተገቢ አይደለም፡፡
5. በልኩ ሊሆን ይገባል፡፡ የቅጣት አላማው ልጆችን ወደ መስመር መመለስ እንጂ ንዴትን ማብረድ አይደለም፡፡ ጥፋት እንኳን ቢኖር በትንሽ በትልቁ መቀጥቀጥ ሁሌ የሚፈፀም ከሆነ ቅጣት እራሱ ትርጉም ያጣል፡፡ ልጆችም ይደነዝዙና በቅጣት የማይማሩ ይሆናሉ፡፡
6. ቅጣቱ ጉዳት የሚያስከትልባቸው መሆን የለበትም፡፡ ወላሁ አዕለም፡

=
@AlhidayaMidia
477 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 21:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 22:11:41 “አልበያን፡- ጀምዒያ፣ ሱሪና የተብዲዕ ህግጋት”

በውስጡ የተካተቱ ጉዳዮች
- የማህበር ምንነት፣ ጥቅሞችና ጉዳቶች
- ማህበርን በተመለከተ የዑለማዎች እይታ ምን ይመስላል? ከ30 በላይ የሚሆኑ ዑለማዎች ፈትዋዎች፣ ተግባሮችና ንግግሮች ተካተዋል፡፡
- የሚፈቅዱ ዑለማዎችን ፈትዋዎች ዋጋ ለማሳጣት የሚደረጉ አጉል ብልጠቶችና ምላሾች
- በማህበራት ላይ የሚነሱ ብዥታዎችና መልሶች፡፡ ለምሳሌ፡-
o “ማህበር ቢድዐ ነው”፣
o “ማህበራት ለሰው ሰራሽ ህግ እውቅና መስጠት አለባቸው”፣
o “በከሃዲዎች መመሳሰል አለባቸው”
o “ማህበራት የፖለቲካ ማስፈፀሚያ ናቸው!”
o “ገንዘባቸውን በወለድ ባንኮች ያስቀምጣሉ”
o “ማህበራት የልዩነት መንስኤ ናቸው” እና ሌሎችም
[2] ሱሪ
- ሱሪና ሲርዋል ይለያያሉን? የሚነሱ ብዥታዎችና መልሶች፣
- በሱሪ ላይ የተለያዩ የዑለማዎች አቋም፣
- ሱሪን ለመከልከል የሚነሱ ምክንያቶች በዑለማዎች ንግግሮች ሲፈተሹ፣
- ሶላት በሱሪ (የአራቱ መዝሀቦችና የዘመናችን ዑለማዎች እይታ ጋር ሲገናዘብ)፣
[3] የተብዲዕ ቅድመ-ሁኔታ
- ከተብዲዕ በፊት ሊስተዋሉ የሚገባቸው ከጥንት ጀምሮ ባሉ ታላላቅ ዑለማዎች የተጠቀሱ ጥቂት መሰረታዊ የአህሉ ሱንና መርሆዎች፣
- አስፈላጊ ጥንቃቄዎች
መፅሐፉ በአላህ ፈቃድ በቅርብ ቀን ገበያ ላይ ይውላል፡፡

=
@AlhidayaMidia
298 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 14:34:13 ረመዳንና የስድስቱ የሸዋል ቀናት ምንዳ
ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
"مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ"
“ረመዳንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀን ያስከተለ ልክ አመት እንደፆመ ነው፡፡” [ሙስሊም፡ 1160]
30 የረመዳን ቀናት + 6 የሸዋል ቀናት = 36 ቀናት
36 x 10 = 360
አላህ በቁርኣን እንዲህ ይላል፡-
﴿من جاء بالحسنة فله عشر أمثالها﴾ الأنعام : 160
“በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለእርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት፡፡” [አልአንዓም፡ 160]
አላህ ለሻለት ሰው የመልካም ስራ ሽልማት ከዚህም በላይ እስከ
- 700 እጥፍ ወይም
- ከዚያም በላይ
ሊሆን ይችላል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
)كُلُّ عَمَلِ ابْنِ آدَمَ يُضَاعَفُ ، الْحَسَنَةُ عَشْرُ أَمْثَالِهَا إِلَى سَبْعمِائَة ضِعْفٍ ، قَالَ اللهُ عَزَّ وَجَلَّ : إِلَّا الصَّوْمَ ، فَإِنَّهُ لِي ، وَأَنَا أَجْزِي بِهِ ، يَدَعُ شَهْوَتَهُ وَطَعَامَهُ مِنْ أَجْلِي ) رواه مسلم (1151 .
“እያንዳንዱ የአደም ልጅ (መልካም) ስራ ይታጠፋል፡፡ መልካም ስራ በአስር አምሳያዎቿ ነው (የምትታሰበው)፣ እስከ 700 እጥፍ ድረስ፡፡ አሸናፊውና የላቀው አላህ እንዲህ ብሏል፡ “ፆም ሲቀር፡፡ እሱ ለኔ ነው፡፡ እኔ (በተለየ) እመነዳበታለሁ፡፡ ስሜቱንና ምግቡን ለኔ ሲል ስለተው፡፡” [ሙስሊም፡ 1151]
ፆም የሶብር ክፍል ነው፡፡ ታጋሾችን በተመለከተ ደግሞ አላህ እንዲህ ይላል፡-
( إنما يوفى الصابرون أجرهم بغير حساب )
“ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚስሰጡት ያለ ሂሳብ ነው፡፡” [አዝዙመር፡ 10]
ማሳሰቢያ፡-
የሸዋል ስድስቱን ቀናት ከዒድ አልፊጥር በኋላ አስከትሎ መፆሙ በላጭ ቢሆንም እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ መፆም እንደሚቻል በርካታ ዐሊሞች ይገልፃሉ፡፡

የቴሌግራም ቻናል፡-
=
@AlhidayaMidia
1.0K viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, edited  11:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 14:28:54
177 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:31:49 ለናይል ወንዝ የተላከ የዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ደብዳቤ ታሪክ
(አጭር ምርመራ)
ኢስላምን ከሌሎች እምነቶች ልዩ የሚያደርገው በእምነቱ ስም የሚወሩ ዘገባዎችን የሚያጣራ የረቀቀ የሐዲሥ ጥናት ማካተቱ ነው፡፡ በዚህ የሐዲሥ ጥናት መሰረት መስፈርት የማያሟሉ ዘገባዎች መልእክታቸው ጣፈም መረረም ይጣላሉ፡፡ መስፈርት የሚያሟሉ ከሆነ ደግሞ መልእክታቸው ጣፈጠንም መረረንም መቀበል ግዴታችን ነው፡፡ ይህንን ሐቅ ጠንቅቆ ማወቅና ማክበር በተለይ በዚህ ያማራቸውን ቂሳ ሁሉ ሳያጣሩ የሚያግበሰብሱ ሰባኪዎች በበዙበት ዘመን እጅግ አንገብጋቢ ይሆናል፡፡ በዚህ ዘመን የሰው መለኪያው ስሜት ሆኗል፡፡ ነፍስያው የወደደችውን “ወሬ” ሳያጣራ “ሶሒሕ” የሚያደርግ፣ ነፍስያው ያልጣማትን ደግሞ በብዙ መረጃ እንኳን ቢደገፍ በሆነ ሰበብ መጣል ብዙዎች የተለከፉበት በሽታ ሆኗል፡፡
ወደ ርእሳችን ስንመለስ ብዙዎቻችን ደጋግመን የሰማነው አንድ ቂሳ አለ፡፡ እሱም እንዲህ የሚል ነው፡-
በቅድመ-ኢስላም ታሪክ ግብፅ ውስጥ አንድ እምነት ነበር፡፡ እሱም የናይል ወንዝ ላይ በያመቱ ቆንጆ ልጃገረድ ካልተጣለበት በስተቀር በቂ ውሃ አይፈሰውም የሚል እምነት ነበር፡፡ ታዲያ ሃገሪቱ በታላቁ ሶሐባ ዐምር ኢብኑል ዓስ ረዲየላሁ ዐንሁ በተከፈተች ጊዜ ይህን የተለመደ ልማድ ኢስላም እንደማይፈቅድ በማሳሰብ ይከለክሏቸዋል፡፡ ግብፃውያኑ እንደፈሩት ውሃው ብዙው ቀርቶ ትንሹም ጠፋ፡፡ ሃገራቸውን ለመልቀቅ መዘጋጀት ያዙ፡፡ ሁኔታውን ያስተዋሉት ዐምር ኢብኑል ዓስ ጉዳዩን ለኸሊፋው ዑመር አሳወቁ፡፡ ከዑመርም እንዲህ የሚል ደብዳቤ መጣ፡ “የአላህ ባሪያ ከሆነው የሙእሚኖች መሪ ዑመር ለናይል ወንዝ!! የምትፈሰው በራስህ ከሆነ አትፍሰስ፡፡ እንዳትፈስ ያደረገህ አንድየውና ሀያሉ አላህ ከሆነ አንደየውንና ሀያሉን አላህ እንዲያፈስህ እንጠይቀዋለን፡፡” ዐምር ኢብኑል ዓስ ስለደብዳቤ አሳወቋቸው፡፡ ከዚያም በናይል ወንዝ ላይ ጣሉት፡፡ ውሃው በጣም በዝቶ መጣ፡፡ ያ ክፉ ልማድ በዚያ ሳቢያ ቆመ፡፡” ልብ በሉ ባጭሩ ነው ያሰፈርኩት፡፡ ብዙዎቹ ተራኪዎች በታሪክ መዛግብት ላይ ከሚገኘውም ባለፈ “ማጣፈጫ ቅመሞችንም” እየጣጣሉ ያደምቁታል፡፡
ቂሳውን የተለያዩ የታሪክ ዘጋቢዎች ዘግበውታል፡፡
ቂሳው ግን ግልፅ ድክመት ያለበት በመሆኑ ለመረጃነት የማይበቃ “ዶዒፍ” ነው፡፡ እንመልከት፡-
1. ከሐዲሡ ሰንሰለት ውስጥ ያለው ኢብኑ ለሂዐህ ደካማ ነው፡፡ ይህንን በርካታ የዘርፉ ምሁራን ገልፀውታል፡፡ ለአብነት ያክል ቡኻሪ [አድዱዓፉ አስሶጊር፡ 190]፣ ኢብኑ ሒባን [አልመጅሩሒን፡ 2/2]፣ ኢብኑ ሐጀር [ጦበቃቱል ሙደሊሲን፡ 54] እና ሌሎችም፡፡ እንዳውም ኢብኑ መህዲ “ከኢብኑ ለሂዐ ጥቂትም ሆነ ብዙ አልወስድም” ብለዋል፡፡ ነሳኢ “ታማኝ አይደለም” ብለዋል፡፡ ኢብኑ መዒን “በሐዲሡ የማይመረኮዙበት ደካማ ነው” ብለዋል፡፡ አልጁዘጃኒ “ሊመረኮዙበት አይገባም” ብለዋል፡፡ ሌሎችም ብዙ የተናገሩ አሉ፡፡ እነዚህ ጥቆማዎች የኢብኑ ሐጀር ተህዚብ ኪታብ ላይ ይገኛሉ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
“ኢብኑ ለሂዐህ ከኢብኑ ሙባረክ፣ ከኢብኑ ወህብ እና ከሙቅሪ ካወራ ዘገባው ሶሒሕ ነው” ያሉ አሉ፡፡ ይህንን መነሻ በማድረግም ከላይ የተዘረዘሩትን ትችቶች ወደ ጎን በመተው ወይም ደግሞ በዚህኛው በመገደብ የኢብኑ ለሂዐን ዘገባዎች ዋጋ የሰጡ አሉ፡፡ ነገር ግን አሁን የምንነጋገርበት የናይል ታሪክ በነዚህ ሶስቱ ሰዎች አማካኝነት ስላልተላለፈ በዚህኛው መስፈርት እንኳን የማለፍ አቅም የለውም፡፡
2. በሰነዱ ውስጥ የማይታወቅ ሰው አለ፡፡ ታሪኩን ኢብኑ ለሂዐህ ከቀይስ ኢብኑል ሐጃጅ የወሰደ ሲሆን እሱ ከማን እንደወሰደው ግን ግልፅ አይደለም፡፡ ሰውየው አይታወቅም፡፡ ከዚህ ካልታወቀ ሰው ያስተላለፈው ቀይስ ብቻ ነው፡፡ ከቀይስ ደግሞ ብዙ ትችቶችን ያስተናገደው ኢብኑ ለሂዐህ፡፡ እንዲህ አይነቱ ታሪክ በሐዲስ ጥናት ሳይንስ “ሙብሀም” ይባላል፡፡ ሙብሃም የሆነ ሐዲሥ በሰንሰለቱ ውስጥ ስሙ በውል ያልተገለፀ ዘጋቢ ያለበት ሐዲሥ ነው፡፡ ሐፊዝ ኢብኑ ሐጀር “ዘጋቢው ያልታወቀን ሐዲሥ በውል እስከሚታወቅ ድረስ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ምክንያቱም አንድን ወሬ ለመቀበል መስፈርቱ አስተላላፊው ብቁ ሆኖ መገኘቱ ነው፡፡ ስሙን ግልፅ ካላደረገ ማንነቱ አይታወቅም፡፡ ታዲያ እንዴት ብቁነቱ ይታወቃል?!!” ይላሉ፡፡ [ኑኽበቱል ፊክር፡ 511] ሌላው ቀርቶ ብቁነትን በሚጠቁም መልኩ ቢወራ እንኳን ዘጋቢው በውል እስካልተለየ ድረስ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ [ኑኽበቱል ፊክር፡ 19] ስለዚህ ይሄኛውም ምክንያት ቂሳው ተቀባይነት እንዳይኖረው የሚያደርግ ሰበብ ነው፡፡
3. ሌላኛው ታሪኩን ውድቅ የሚያደርገው ምክንያት በሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኘው ሌላኛው ዘጋቢ ቀይስ ኢብኑል ሐጃጅ ዐምር ኢብኑል ዓስንም ሆነ ዑመር ኢብኑል ኸጣብን ያላገኘ መሆኑ ነው፡፡ ሁለቱንም አላያቸውም፡፡ ይሄ ከሁለተኛው ነጥብ ጋር ተደምሮ የሚታይ ነው፡፡
ሲጠቃለል ቂሳው ጠንካራ መሰረት የሌለው “ታሪክ” ነው ማለት ነው፡፡ ምናልባት ይሄ ታሪክ ስለሆነ የሐዲሥ መስፈርቶችን ባያሟላም ችግር የለውም የሚሉ ሊኖሩ ስለሚችሉ የአላህ ፈቃዱ ከሆነ በዚህ ረገድ ዑለማዎች ምን እንደሚሉ ለማየት እሞክራለሁ፡፡ የተጠቀምኩት መረጃ በአብዛሀኛው ከሸይኽ ዐሊ ሐሺሽ ጥናት የተወሰደ ነው፡፡ [ተውሒድ መፅሔት፡ ቁ. 442፣ ሸዋል 1429፣ ገፅ፡ 53-55]
ሼር ማድረግ አይርሱ፡፡
=
@AlhidayaMidia
1.0K viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 10:11:24 ታላቁ የእውቀት ባህር ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ:–
"ዲናዊ ዝምድና ከጭቃዊ ዝምድና የላቀ ነው። በልቦችና በሩሖች መካከል ያለው መቀራረብ በአካላት መካከል ካለው መቀራረብ የበለጠ ነው።"
(ሚንሃጁ አስሱንናህ: 7/78)

=
@AlhidayaMidia
180 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 22:54:04 ስንቶታችን ነን ቤተሰቦቻችን እረጋ ለስለስ ባለ መልኩ ወደ ተውሒድ
ጥሪ ያደረግነው? የተውሒድ አባት
ኢብራሒም አባዬ እያለ አባቱ ወደ
ተውሒድ ሲጠራው እንዲህ ይላል


إِذْ قَالَ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ لِمَ تَعْبُدُ مَا لَا يَسْمَعُ وَلَا يُبْصِرُ وَلَا يُغْنِي عَنكَ شَيْئًا

ለአባቱ ባለ ጊዜ (አስታውስ) «አባቴ ሆይ! የማይሰማንና የማያይን ከአንተም ምንንም የማይጠቅምህን (ጣዖት) ለምን ትግገዛለህ

يَا أَبَتِ إِنِّي قَدْ جَاءَنِي مِنَ الْعِلْمِ مَا لَمْ يَأْتِكَ فَاتَّبِعْنِي أَهْدِكَ صِرَاطًا سَوِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ ከዕውቀት ያልመጣልህ ነገር በእርግጥ መጥቶልኛልና ተከተለኝ፡፡ ቀጥተኛውን መንገድ እመራሃለሁና፡፡

يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا

«አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና፡፡

يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا

«አባቴ ሆይ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ፡፡»
///ሱረቱ መርየም///

ወደ ተውሒድ ሰዎችን ስንጣራ ሊሰድቡን፦ ሊያመናጭቁን፦ ሌላም ነገር እንደሚሰሩ ማወቅ አለብን።
እና አባቱ ተውሒድን ተቀበለ እንዴ ላ እንደው ማስፈራራት ጀመረ።


قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا

(አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ፡፡
(((((ሱረቱ መርየም))))

ባይቀበሉንም ትግስት ልናረግ ጥሩ ንንግግር ልንናገራቸው ይገባል አሁንም ኢብራሒም የራሱ ጉዳይ ብሎት አልሄደም እንዲህም አለው።


قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا

«ደህና ኹን፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ፡፡
///ሱረቱ መርየም////
=
@AlhidayaMidi
1.0K viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, edited  19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 22:29:51 የምስራች አስደሳች ዜና


ስታነቡ ቀስ ብላቹ አብቡ በደስታ ዉስጣቹ እንደሚሞላ እርግጠኛ ነኝ


አስደሳቹ ዜናም ይሄ ነዉ አለማቀፉ ታዋቂዉ የእዉቀት ባለቤት የሆነዉ ዶክተር ዛኪር ናይክ ወደ ኢትዮፕያ...............................

ቀስበሉስኪ ተረጋጉ ይሄን ያህል ጉዳዩን ለማወቅ መጓጓት ቆይማ ረፍት ዉሰዱ አንድ ጊዜ ......


አለማቀፉ ታዋቂዉ የእዉቀት ባለቤት የሆነዉ ዶክተር ዛኪር ናይክ ወደ ኢትዮፕያ እንዲመጣ ከወዲሁ ከአህመዲን ጀበል ጋር ንግግር እያደረጉ እንደሆነ ከራሱ ከአህመዲን ጀበል ሰማዉ

አለማቀፉ ታዋቂዉ ዶክተር ዛኪር ናይክ እንዲመጣም የፌደራል መጅሊስ ከወዲሁ የዉጪ ግንኙነት ያለዉ ኡስቴዝ አህመዲን ጀበል ከዶክተር ዛኪር ናይክ ጋር ንግግር መጀመራቸዉን ከአህመዲን ጀበል ጉዳይ መጀመሩንም ይፋ አድርጓል



አሏሁ አክበር
አሏሁአክበር
አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር
አሏሁ አክበር


አሏህ ያሳካዉ ዘንድ በዱአ ያጀማአ እባካቹ በዱአ
Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ

=
@AlhidayaMidia
= @AlhidayaMidia
1.6K viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 20:54:05
በዛሬው ዕለት በከንባታ ጠንባሮ ዞን በዳንቦያ ወረዳ በወንዶ ቀበሌ በተደረገው ታላቅ ሃገር አቀፍ የዳዕዋና የአንድነት ኮንፍረንስ ላይ 24 ወንድና 7 ሴት በድምሩ 31 ሰዎች ወደተፈጠሩበት ዲን እስልምና ተመልሰዋል።

አላሁ አክበር! አላህ ጽናቱን ይስጣቸው!
235 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, 17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 20:52:05 Al HiDAYA MidiA የተበዳይ ሙስሊሞች ጉዳይ ያሳስበኛል ተዉሂድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ነዉ :
220 viewsإذلم تتعلم التو حيد والعقيدت الصحيحت ستخيفك البو مت ويغير مزاجك, edited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ