Get Mystery Box with random crypto!

ጥላ ለ ሙት መሪያችን የተናገሩትን ንግግር ሰምቼ ሙት አያቴ መቃብር ላይ ሄጄ ዛፍ ለመትከል አሰብ | Alex Abreham በነገራችን - ላይ

ጥላ ለ ሙት

መሪያችን የተናገሩትን ንግግር ሰምቼ ሙት አያቴ መቃብር ላይ ሄጄ ዛፍ ለመትከል አሰብኩ።
ከዛ እንዴት መትከል እንዳለብኝ፥ የሚያስፈልጉኝን መሳሪያዎች አዘጋጅቼ ሲነጋልኝ መጠዋት ለመትከል አስቤ ተኛሁ፤ኤጭ መተኛት አይባል ሙት አያቴ ጋር ጭቅጭቅ ልበለው ንዝንዝ ልበለው ክርክር ወይም ውይይት ይዘን ነበር።
ይመስለኛል ነግቶልኝ ዛፍ ልተክል ሂጄ ነው፤
ግራ ገብቶኝ ቆሚያለሁ መቃብሯን ልፈነቀለው ነው? እንደዛ ካላረኩማ እንዴት መትከል ይቻለኛል እያልኩ እራሴን እየጠየኩ ና ለራሴ መልስ እየሰጠሁ፡ ከዛ መቃብሯን ልፈነቅል አንዴ ድም ሳረገው
-ኧረ ልረፍበት...የሚል ከሩቅ.... ምን ከሩቅ ከመሬት ስር የወጣ ድምፅ ሰማሁ የአያቴ ነበር።
- እንዴ አያቴ..አልኩ እንባ እያቀረርኩ...እዚህ መቃብር መጥቼ ስንቴ ለምኜሽ ነበር ይቅር ብዬሻለሁ እንድትይኝ ለምኜሻለሁ አሁን ግን.... ብዬ ወሬዬን ከመቀጠሌ በፊት አያቴ አቋረጠችኝ
- ኤዲያ ዝም በይልኝ እባክሽ አሁን ልረፍበት ሰው ሞቶ እንኳን አያርፍም እንዴ እናንተ ሀገር.. ነው አዲሱ ስትራቴጂ ነው? መቃብር ብጥበጣውስ በዘር ነው? እ? በዘር ጭፍጨፋ ያልሞቱትን በመቃብ ብጥበጣ ረብሿቸው ብሏቹ ነው?
-ማ? አልኩ ጥያቄዋ ግራ አጋብቶኝ
-ማ? ህ መሪያቹህ አለችኝ ምሬት በተቀላቀለበት ድምፅ
-እንዴ አያቴ መቃብር ቦታ ላይም የእይታ መስኮት አለ እንዴ? ፖርላማ ይቀርባል?
- ሃሃሃሃሃሃ ስኖር እንዲህ ስቄ አቃለሁ ቤቦ? አለችኝ ሳቅ ባፈነው ድምፅ። እህ እህ ለመሆኑ ምን ልታደርጊው ነው መቃብሬን የምፈነቅይው አንቺ?
-ከሄድኩበት ሀሳብ እንደመባነን ብዬ ዛ ዛፍ ተክልልሽና ጥላ እንዲሆንሽ።
መቃብሩን የሚያናጋ ሳቅ ተከተለው ንግግሬን........በዚህ ሳቋ ምክንያት ሌላ መቃብርተኞችም ሳይበጠበጡ አልቀረም።
-አሁንስ አበዛሽው አያቴ ምነው? እንዴ ምን የሚያስቅ አገኘሽ? ከመቼ ጀምሮ ነው በሰው የምታሾፊው?
- መቃብር ላይ ዛፍ መተከል ከጀመረ ጀምሮ?
ቆይ ቆይ ማን ሲል ሰምተሽ ነው በሞቴ(ይች አባባል ዛሬ ትክክለኛ ሰው ላይ ገባች) ምላሼን ለመስማት በጓጓ ድምፅ
- እህ ቅድም የገባሽ መስሎኝ መሪያችን ነዋ!
-ያ ሳቋ ተደገመ፡ ይልቁን ዛፉን ትተሽ እንደዚህ ያለ አይረሴ ቀልድ እየቃረምሽ ብታመጭልኝ እ? ድሮም ዋዘኛ የገዛው እና ብልህ የገዛው እቃ አንዳይነትም ቢሆን አንድ አይነት ጥቅም አይኖረውም።
-የምን ዋዘኛ፣ ብልኸኛ ነው የምትይኝ አያቴ?
- ያኔ አሞኛል ስላቹ ህመሜን እንደቀላል፣ እንደዋዛ፣ እንደቀልድ ባታዩብኝ እዚህ እገኝ ነበር? አዎ ሁሉም ሁሌ ምድር ላይ አይኖርም ግን ልናተርፋቸው የሚቻሉ ሞቶችን ስንሞት አይታቹ አሁን ዛፍ ጥላ ትሉብናላቹ (እልህና ንዴት የተቀላቀለበት ንግግር) እርዳታ አስፈልጎኝ ስማፀናቹ ሳደርሱ አሁን ዛፍ ልተክሉልኝ (ማሰቢያቹ ተናግቷል ተመርመሩት አይነት ናት ይችስ) ነው ሀገሪቱ ሞላችባችሁ እ? የሙቶች መቃብር ላይ ዛፍ እየተከላቹ ቦታ ልታሲዙ ነው? አይዟቹህ ሰው እያለቀላቹ ስለሆነ ቦታ አይታጣም እኮ ። አሁን ሙት መቃብር ላ ዛፍ ተክለሽ ጥላ ነው ጫና የምትፈጥሪው እ? ኧረ ጉድ ነው በኔ አፅም ብስባሽ ዛፉ እንዲለመልም ነው ሃሃሃሃሃ
በይ የሞተ አካል ላይ ዛፍ እየተከልሽ ጥላ ይሁን ከምትይ እየኖሩ የዛፍ ሳይሆን የድጋፍ ጥላ ለሚያስፈልጋቸው ጥላ ሁኚ።አያሰማን የለ አዬ መሞት ደጉ.
-ኧረ መኖር ደጉ ነው ልላት ስል ከእንቅልፌ ባነንኩ እንዲህ ከሆነ መኖር እውነትም መሞት ደግ ነው እሱንም ቀንተን ዛፍ በመትከል ሰበብ ካልበጠበጥናቸው

ምን ማለት ፈልጌ ነው አታነካኩኝ ፖለቲካ አልወድም።

ቤተልሔም ሳሙኤል('ቴጌ ሐበሻዊት)