2023-09-09 20:18:58
Imala Gara Boorana Yaabelloo
ጉዞ ወደ ቦረና ያቤሎ
ከወራት በፊት በረመዳን ዘጠኙ ሰለምቴዎች በቢረና ያቤሎ ለህዝባቸው ኢስላማዊ ዳዕዋን ለማድረስ «ዳሩሰላም» የተሰኘ መርከዝ በማቋቋም እያደረጉት ያለውን ጥረት በመግለጽ የጀመሩትን መርከዝ ለማጠናቀቅ እንድናግዛቸው ጠይቄ ነበር።አላህ ይቀበላችሁና ከፊላችሁ የየአቅማችሁን ተሳትፋችኋል። 9ኙ ሰለምቴዎች ባገኙት መጠነኛ እገዛ መርከዛቸውን አጠናቀው ለምረቃ ጥሪ ስላደረጉልኝ ወደ ቦረና እያመራሁ ነው።አልሀምዱሊላህ በሰላም አርባምንጭ ገባሁ። በአርባምንጭ አየር ማረፊያም ከያቤሎ ቦረና ሊቀበሉኝ የመጡ ወዳጆችና የአርባምንጭ ከተማ በመስከረም 6 ቀን 2016 የሚመረቁት የአል ኢህሳን መድረሳ የቁርኣን ሂፍዝ ተመራቂ ህፃነት አቀባበል አደረጉልኝ። ከአርባምንጭ ወደ ቦረና ያቤሎ በመኪና ጉዞ ጀመርን።ከዚህ በታች ከዚህ በፊት ስለ 9ኙ ሰለምቴዎች የለጠፍኩትን ጽሁፍ ዳግም እንዲያነቡ እጋብዛለሁ።
Imala Gara Boorana Yaabelloo
Baati muraasa dura baati Ramadaanaa darbeetti waa'e warrootan Islaaman saglaan isnif barreesseen turee. Akka jarri eega Islaamummaa fudhatani booda markaza Daarusalaam jedhamu dhaabun ummata isaanif da'waa akka godhaaturani fi markaza jarri jalqaban xumuruf akka gargaarsaan bira dhaabbatan yaamicha isinif godheen ture. Gariin keessanis bira dhaabbatani turtan. Waanuma argatan muraasan markaza jaraa haguma danda'amu xumurani eebbaaf nayaamnan gara Boorana Yaabelloo imalaan jira. Yeroon buufata xayyaaraa magaalaa Arbaamincci gahu oboleewwan booranaa, ulamoota booranaa fi barattoota hifzi Qur'aana madrasaa al Ihsaan(kan fulbaana 6,2016 eebifaman) na simatan. Konkolaataan imala gara Yaabelloo booranaa eegallee.
Barreefama waa'ee sochi da'waa warraa Islaaman sagglan barreessee irra deebin armaan gaditti isni maxxanseera dubbisa.
9ኙ ሰለምቴዎችና የኛ ነገር
በቦረና አከባቢ ሕዝባቸው ኢስላምን እንዲገነዘብ ከደሞዛቸው ቀንሰው እያዋጡ እንዲሁምና ሰውን እያስተባበሩ የቻሉትን እየለፉ ነው።ዘጠኝ ሰለምቴዎች ናቸው። 8ቱ ኢስላምን የተቀበሉት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እያሉ ነበር።
በቦረና ባለፉት ዓመታት በነበረው ድርቅ የአክፍሮት ሃይላት በሺህ የሚቆጠሩ ልጆችን «እናስተምርላችሁ» ብለው ወስደው ሃይማኖታቸውን በማስቀየርና ወላጅ ዘመዶቻቸውን ዲን እንዲያስለውጡ እየተሰራ ያለው ነገር ያሳስባቸዋል። እንደምሳሌ አንዱ ድርጅት ብቻ አንድ ሺህ ልጆችን «ትምህርት ላስተምርላችሁ» ብሎ ከወላጆቻቸው ወስዶ ዲናቸውን በማስለወጥ ላይ እየሰራ ያለውን ሥራ በቅርበት ያያሉ።አቅሙ ኖሯቸው እነርሱም በስፋት ለዲናቸው ለመስራት ከፍተኛ ጉጉት አላቸው።
የአቅም ዉስንነት ቢኖርባቸውም እጃቸውን አጣምረው አልተቀመጡም።በአቅማቸው ህዝባቸው ዲኑን እንዲያውቅ ለማድረግ ከሁለት ዓመታት በፊት ከኦሮሚያ መጅሊስ «ዳሩሰላም መርከዝ» በሚል ፈቃድ ወስደው በራሳቸው ጥረትና እንደ ሼህ አሊ ጅማ ባሉት እገዛ በቦረና ያቤሎ ከተማ መርከዝ በማቋቋም 56 ልጆች ተቀብለው ኢስላምን እያስተማሩ ነው። ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ወደየአከባቢያቸው በመመለስ ህዝባቸውን ዲን እንዲያስተምሩ አልመዋል።
አቅም ኖሯቸው እንደሌሎቹ በሺህ የሚቆጠሩ ልጆችን፣ ባይሆን እንኳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ልጆችን ተቀብለው በዙሪያቸው የከበባቸውን የአኩፍሮት ሀይላትን መመከት የሚችሉ ልጆችን ቢያስተምሩ ደስታውን አይችሉትም።
ነገር ግን እንኳንስ ይህን በአቅማቸው ሊያደርጉ ቀርቶ በስንት ትግልና ጥረት የጀመሩትን የመርከዝ ግንባታ እንኳ ማጠናቀቅ ተስኗቸው ለማቆም ተገደዋል።
በዚህ ሁኔታ እያሉ ባለፈው ወር ወደ ጂንካ እንደምንመጣ ሰሙ።ይህን ጊዜ ሰባቱ ወጣቶች እኛን በማግኘት ያሉበትን ተግዳሮት ሊያካፍሉንና በመፍትሄ ፍለጋ እንድናግዛቸው ለመንገር ከቦረና 215 ኪሎ ሜትር ተጉዘው ጅንካ ድረስ መጡ።በጅንካም ተገናኘን።
በአከባቢያቸው ያለውን ተግዳሮት አብራሩልኝ።ወጣቶቹን ለዲናቸው ያላቸውን ቀናኢነት፣በግል ተነሳሽነት ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ስሰማ በእጅጉ ተደመምኩ። ሕዝባቸው ዲንን ሳይረዳ በአክፍሮት ሃይላት እንዳይወሰድ ያላቸው ጭንቀት አይቶ አላህ ህልማቸውን ያሳካላቸው።
ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢስላምን ተቀብለው ለዲናቸው እንዲህ እየተጉ ያሉትን የእነኚህን 9ኙ ሰለምቴዎችን ጥረት ለማገዝ ምን ያክል ዝግጁነን? አንተስ? አንቺስ? እናንተስ? እነኚህ የቦረና ወንድሞቻችን እንዲህ በማለት ነበር ተማጽኖዋቸውን ያቀረቡልኝ: -
«የጀመርነውን መርከዝ ጨርሱልን። እንደሌሎቹ በሺህ ቤት የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀብለን ማስተማር እንፈልጋለን። እርዱን።ይህን ባትችሉ እንኳ ተማሪዎችን የመቀበል አቅማችንን እንድናሳድግ ተጨማሪ ክፍሎችን ገንቡልን። ሌላው ቢቀር የጀመርነውን የመርከዝ ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ አግዙን። በተለያየ መንገድም ከጎናችን ቁሙ።»
ከጥቂት ዓመታት በፊት ኢስላምን ተቀብለው ስለህዝባቸው በመጨነቅ ከደሞዛቸው ተቆራጭ እያደረጉ ጭምር ለዲናቸው የሚለፉትን የእነኚህን ወጣቶችን ጥረት ለማገዝ ምን ያክል ዝግጁ ናችሁ? አንተስ? አንቺስ? እናንተስ?
ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰለሙት እነኚህ ወንድሞቻችን ለዲናቸው እንዲህ ቀናኢ ሆነው ህዝባቸው በአክፍሮት ሃይላት እንዳይወሰድ ሲተጉ እኛ ለበርካታ ዓመታት በሙስሊምነት የቆየነው ምን ያክል ሚናችንን እየተወጣን ነው?
በቦረና ዞን በያቤሎ ከተማ የሚገኘውን የዳሩሰላም መርከዝን ግንባታ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጋቸው 6 ሚሊየን ብር ብቻ ነው። ይህንን ገንዘብ ለመሸፈን ደግሞ: -
አንድ ሚሊየን ብር የሚያዋጡ 6 ጀግኖች፣
500ሺህ ብር የሚያዋጡ 12 ጀግኖች፣
100ሺህ ብር የምታዋጡ 60 ሰዎች ፣
50ሺህ ብር የምታዋጡ 120 ሰዎች።
10ሺህ ብር የምታዋጡ 600 ሰዎች ታስፈልጉናላችሁ።
የአካውንት ስም:- ዳሩሰላም መርከዝ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000512577192
የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ:-1014200050856
አዋሽ ባንክ :- 014251146550800
መልዕክቱን ለሌሎችም ሼር በማድረግ፣ ለምናውቃቸው ኸይር ፈላጊዎች በመጠቆም አጅራችንን እናብዛ። አላህ ይቀበለን። ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ በውስጥ ይላኩልን።
(ከስር በምስሉ ላይ ከጀርባ ቆመው የምትመለከቷቸው ከ9ኙ ሰለምቴ ወንድሞች መካከል እኛን ለማግኘት ከቦረና ጅንካ ድረስ በመጡ ጊዜ አብረውን የተነሱት ፎቶግራፍ ነበር።)
ለዳሩሰላም መርከዝ ተጨማሪ ክፍሎችን ለመገንባት አልያም መርከዙ እንዲጠናቀቅ ለማገዝ አልያም ለበለጠ መረጃ
13.1K views17:18