Get Mystery Box with random crypto!

ሐባን ኢብኑ ሙንቂዝ [ረዐ] እንደዘገቡት: «አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ሐባን ኢብኑ ሙንቂዝ [ረዐ] እንደዘገቡት:

«አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: ‐ «የአላህ መልክተኛ ሆይ! የዱዓዬን ሲሶ(አንድ አራተኛ) ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?»

እርሳቸውም:‐ «ከፈለግክ አዎን!» አሉት።

«ሁለት ሶስተኛውን ላድርገው?» አላቸው።

«አዎን!» በማለት መለሱለት።

«ሁሉንም ለርሶ ሶለዋት ላድርገው?» ጠየቀ።

የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ አሉ:‐ «እንደዚያ ከሆነ ያሳሰበህን የዱንያም ሆነ የአኺራን ነገር አላህ ይገላግልሀል።»

ሹዐቡል‐ኢማን ላይ በይሀቂይ ዘግበውታል።