Get Mystery Box with random crypto!

'እኔ ችግርና ጭንቅ ገጥሞኝ እሮብ ቀን ከዙህር እስከ ዐስር ባለው ጊዜ ዱዓ አድርጌ አላውቅም አላህ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

"እኔ ችግርና ጭንቅ ገጥሞኝ እሮብ ቀን ከዙህር እስከ ዐስር ባለው ጊዜ ዱዓ አድርጌ አላውቅም አላህ ተቀብሎኝ ጭንቀቴ ቢወገድ እንጂ" ሶሀቢዩ ጃቢር(ረዐ)

ኢማም አሕመድና አል-በዛር ከጃቢር(ረዐ) ባስተላለፉትና አልባኒን ጨምሮ በርካታ የሀዲስ ሊቃውንት ሰሂህ ባሉት ሀዲስ

ነቢዩ(ሰዐወ) ለሶስት ቀናት ሰኞ፣ማክሰኞና እሮብ መስጂደል ፈትህ ላይ ዱዓ አደረጉ እሮብ ከዙህር እስከ ዐስር ባለው ጊዜ መልስ አገኙ ዱዓቸው ሙስተጃብ ሆነ ደስታውም ፊታቸው ላይ ተነበበ።

ሀዲሡን ያስተላለፉት ሰሓቢይ ጃቢር እንዲህ አሉ "እኔ ችግርና ጭንቅ ገጥሞኝ እሮብ ቀን ከዙህር እስከ ዐስር ባለው ጊዜ ዱዓ አድርጌ አላውቅም አላህ ተቀብሎኝ ጭንቀቴ ቢወገድ እንጂ" አሉ

ኢማሙል በይሀቂይ ዱዓ መቅቡልከሚሆንባቸው ቀናቶች አንዱ ይህው ቀንና ሰዓት እንደሆነ ገልጸዋል።

ኢብኑ ተይሚያም በዚህ ሀዲስ በርካታ ዑለሞች ይሰሩበት እንደነበረና የግድ ፈትህ መስጂድ ላይ መሆን እንደሌለበት፣ ጃቢርም ቢሆን እሮብን ቀን እይጠበቁ እንጂ ቦታው ላይ/ፈትህ መስጂድ እየሄዱ ያደርጉ እንዳልነበረ ገልጸዋል።

ዛሬ እለቱ እሮብ ስለሆነ እንጠቀምበት።

ኡስታዝ አህመድ አደም

T.me/ahmedin99