Get Mystery Box with random crypto!

የአረፋ ቀን ፆም! ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

‎﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።

ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።

ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።

በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት

ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።