Get Mystery Box with random crypto!

ሽፋኑ «አማራ» በሚል ይሁን «ሙስሊሞች» ላለፉት ዓመታት በጅምላ ሲጨፈጨፊ እንደነበረው ሁሉ የወሎ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ሽፋኑ «አማራ» በሚል ይሁን «ሙስሊሞች» ላለፉት ዓመታት በጅምላ ሲጨፈጨፊ እንደነበረው ሁሉ የወሎ ሙስሊሞች በዚሁ በሰኔ ወር እንኳ ለሁለተኛ ጊዜ ዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ መንገድ በቄለም ወለጋ በኦነግ ሸኔ በጅምላ እንደተገደሉ ሰማን።እጅግ የሚያሳዝንና የሚወገዝ እኩይ ተግባር!

ሰላማዊ ዜጎችን በማንነታቸው ኢላማ አድርጎ ግድያ ሲፈጸም ጉዳዩ ግድያ ብቻ አይሆንም። ኢሰብኣዊነትና በሰው ህይወት ቁማር መጫወት ነው! ጀግና ነኝ ያለ ኃይሉን መሳሪያ ባልታጠቁ ንጹኻን ላይ ሳይሆን ከታጠቀ ወታደር ጋር ይግጠምና ያሳይ!

ላለፉት ዓመታት በተደጋጋሚ ንጹኋን ሲጨፈጨፉ በተመሳሳይ መንገድ ጮህን፣አወገዝን።«እርምጃ እየተወሰደ ነው» ተባለ።ከፖለቲካ ሸፍጥ በራቀ ሁኔታ መፍትሄው ላይ በማተኮር የእውነት ከልብ መነጋገር ባለመቻሉ ንጹኻንን መታደግ አልተቻለም!

በተመሳሳይ መንገድ የንጹኻን ጭፍጨፋ ለስንተኛ ጊዜ መሆኑ ነው? አሁንም እንደከዚህ ቀደሙ በዚያው መንገድ ቀጣዩ ግድያ እስኪፈጸምና ይህኛውን እስኪያስረሳ ድረስ የዛሬውን ግድያ በማውገዝና በመጮህ ብቻ መፍትሄ ይመጣ ይሆን? ባለፉት ዓመታት ከተጓዝንበት በተለየ መንገድና ዓይን ጉዳዩን ለመረዳት ሞክረን የተለየ መፍትሄ ካልፈለግን በሀገራችን የንጹኻን ዜጎች እንዳይቀጥል ያሰጋል! ሁሉን የምታውቀው አምላኬ ሆይ! ሰላምና ምህረትህን! '