Get Mystery Box with random crypto!

ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት በአስገዳጅነት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት እንደሚተገበር | AHADU RADIO FM 94.3

ከመጪው ዓመት ጀምሮ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት በአስገዳጅነት የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡

ከሁለት ዓመታት በኋላ በ2017 ዓ.ም. በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
በዘንድሮዉ ዓመት በ74 የፌድራል ተቋማት ላይ እየተተገበረ ያለው የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት ከቀጣይ አመት ጀምሮ በሁሉም የፌድራል ተቋማት ላይ በአስገዳጅነት እንደሚተገበር የመንግስት ግዥ እና ንብረት ባለስልጣን አስታወቋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት 169 የፌዴራል ተቋማት የማኑዋል ግዥን አስቀርተው ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር እና የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓትን፣ በሲዳማ ክልል በማሳያነት በማስጀመር በቀጣይ በሁሉም ክልሎች ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልደአብ ደምሴ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡

ወደፊት ወደ ዞንና ወረዳዎች በመውረድ የማኑዋል ግዥ ሥርዓት ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሮኒክ ግዥ የሚቀየርበት ሁኔታ እንደሚፈጠር ገልፀዋል፡፡
እስካሁን ስምንት ሺሕ ያህል አቅራቢዎች እንደተመዘገቡ ገልፀዉ በቀጣይ ሁሉም የፌዴራል ተቋማት ወደ አሠራሩ ሲገቡ ከ30 ሺሕ በላይ አቅራቢዎች ወደ አሰራሩ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓቱ ከንክኪ የፀዳ፣ ወጪ ቆጣቢና ቀልጣፋ፣ እንዲሁም ግልጽ መሆኑ ዘርፎቹ ለሙስና ያላቸውን ተጋላጭነት ከመቀነሱ በተጨማሪ፣ አቅራቢዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ያለ ውጣ ውረድ ተወዳድረው መሸጥ እንደሚያስችላቸዉ አክለዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24