Get Mystery Box with random crypto!

የጤና መድህን አገልግሎት በግል የህክምናና የላቦራቶሪ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በቅርብ ጊዜ ውስጥ | AHADU RADIO FM 94.3

የጤና መድህን አገልግሎት በግል የህክምናና የላቦራቶሪ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በቅርብ ጊዜ ውስጥ እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

የጤና መድህን አገልግሎትን በግል የህክምናና የላቦራቶሪ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለማስጀመር እየሰራን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ጤና መድህን የአገልግሎት ሰጪዎች ጥራት ማረጋገጥ ዳይሬክተር ወይዘሮ ፈለጉሽ ብርሃኔ ገልጸዋል፡፡
ይህም ከህብረተሰቡ በጤና ተቋማት የተሟላ አገልግሎት አለማግኘት ላይ ለሚነሱ ቅሬታዎች አንዱ መፍትሄ እንደሚሆን ተነግሯል፡፡

ህብረተሰቡም የአልትራሳውንድ የራጅ እንዲሁም ሌሎች የላቦራቶሪ ምርመራዎችን በጤና መድህን አገልግሎት ከግል የህክምና መስጫ ተቋማት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት በአዲስ አበባ በሚገኙ 9 የፌዴራል ሆስፒታሎች የጤና መድህን አገልግሎትን ለመስጠት ውል መያዙን ገልጸው፤ እነዚህ ውል የያዝንባቸው የህክምና ተቋማት ክፍያ በሚጠይቁበት ጊዜ በውሉ መሰረት አገልግሎት መሰጠቱን በየሶስት ወሩ በሆስፒታሎቹ በመገኘት እንፈትሻለን ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አንድ ታካሚ ህክምና ጨረሰ የሚባለው ምርመራዎቹን አጠናቆ መድሃኒት ይዞ ወደ ቤቱ ሲሄድ በመሆኑ ተቋማቱ ሙሉ የህክምና አገልግሎቶችን ለጤና መድህን አባላት መስጠት ይኖርባቸዋልም ሲሉ አሳስበዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24