Get Mystery Box with random crypto!

ከጅቡቲ ወደብ እስከ መሀል ሀገር እቃ ይዘው በሚመጡ የኢትዮጵያ ባህር እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድ | AHADU RADIO FM 94.3

ከጅቡቲ ወደብ እስከ መሀል ሀገር እቃ ይዘው በሚመጡ የኢትዮጵያ ባህር እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተሽከርካሪዎች ዘመናዊ መቆጣጠሪያ መገጠሙ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ባህር እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የጭነት አስተላላፊ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሲራጅ አብዱላሂ የድርጅቱ ተሸከርካሪዎችም ሆነ በአጋርነት የሚሰሩ ሌሎች ተሸከርካሪዎች ላይ ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ቴክኖሎጂ ለመግጠም ስንሰራ ነበር ያሉ ሲሆን የድርጅቱ ንብረት የሆኑ ሁሉም ተሸከርካሪዎች መሳሪያው ተገጥሞላቸዋል ብለዋል፡፡
ተሸከርካሪዎቹ የተገጠመላቸው ጂፒኤስ በማንኛውም ሰዓት የት እንዳሉ እና የስምሪት መስመራቸውን ለመቆጣጠር ያስቻላል ብለዋል፡፡

ነገር ግን ከአገልግሎት ድርጅቱ ጋር በኮንትራት የሚሰሩ የመልቲ ሞደልም ሆነ የብትን ጭነት የሚያጔጉዙ የግል ተሸከርካሪዎች ቴክኖሎጂው እንዳልተገጠመላቸው ገልጸዋል፡፡
አክለውም የትራንስፖርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአዲሱ የትራንስፖርት ማህበራት አደረጃጀት ተሸከርካሪዎቹ እነዚህን ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊ ሲያደርጉ አጠቃላይ ዘርፉን አሰራር ያሻሽለዋል ብለን እንጠብቃለን ብለዋል፡፡

በዚህ ዓመት የተሽከርካሪዎች የጂቡቲ ወደብ ቆይታ በአማካይ ስምንት ቀን ለማድረስ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም እቅዱን ማሳካት እንዳልተቻለ እና ቆይታቸው ሃያ አራት ቀን እንደሆነ መገለፁ የሚታወስ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24