Get Mystery Box with random crypto!

ሳውዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች እንዲከፈል የወሰነችው የክፍያ ተመን ዝቅተኛ የሆነው | AHADU RADIO FM 94.3

ሳውዲ አረቢያ ለኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞች እንዲከፈል የወሰነችው የክፍያ ተመን ዝቅተኛ የሆነው ከ5 አመት በፊት የተደረገውን ስምምነት ተከትሎ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
የሳውዲ አረቢያ የሰው ሃብት ሚንስቴር በተለያዩ 8 አገራት ለሚመጡ የቤት ሰራተኞች የክፍያ ጣሪያ ተመን ይፋ ያደረገ ሲሆን ለኢትዮጵያውያን እንዲከፈል የተወሰነው ግን ከሁሉም አገራት ዝቅተኛው ሲሆን ይህም 6900 የሳውዲ ሪያል እንደሆነ አስታውቋል፡፡
ይህንንም አስመልቶ የኢትዮጵያውያኑ ክፍያ በምን ምክንያት ከሌሎቹ ዝቅተኛ ሊሆን ቻለ ሲል አሐዱ የስራ እና ክህሎት ሚንስቴርን ያነጋገረ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ከሳውዲ አረቢያ የሰው ሀብት ሚንስቴር እንዲሁም ከሀገሪቱ አምባሳደር ጋር ውይይት መደረጉን የስራ እና ክህሎት ሚንስቴር የሰራተኛ ዘርፍ ሚንስቴር ዲኤታ አቶ አሰግድ ጌታቸው አስታውቀዋል፡፡
ክፍያው በዚህ ልክ ዝቅተኛ የሆነበት ምክንያት ከክፍያ ጋር በተያያዘ ለመጨረሻ ጊዚ የሁለትዮሽ ስምምነት የተደረገው ከ5 አመት በፊት የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ ማሻሻያ ስላልተደረገበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
በቅርቡም 3 ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሰራተኞች ክፍያ ጋር በተያያዘ አዲስ የሁለትዮሽ ስምምነት እንደሚደረግ ገልጸው አሱን ተከትሎም ይፋ በተደረገው የክፍያ መጠን ላይ ተገቢውን ማሻሻያ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም አሁን ላይ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አገራት የሚያቀኑ የቤት ሰራተኞች ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ብቃት እና የመግባባት ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያግዝ ስልጠና እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ይህንን ታሳቢ ያደረገ ክፍያ እንዲያገኙ ከአገሪቱ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/