Get Mystery Box with random crypto!

የህጻናት አድን ድርጅት በቦረና በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ህፃናት እና እናቶች ድጋፍ በማሰባሰብ ላ | AHADU RADIO FM 94.3

የህጻናት አድን ድርጅት በቦረና በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ህፃናት እና እናቶች ድጋፍ በማሰባሰብ ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

አለማቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት ሴቭ ዘ-ችልድረን በኢትዮጲያ ባሳለፍነው ሳምንት በሰጠው መግልጫ በትግራይ ክልል በጦርነቱ ለተጎዱ እናቶች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል፡፡
በቦረና በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ህፃናት እና እናቶች ድርጅቱ ምን እያከናወነ ነው ሲል አሐዱ የጠየቃቸው የዓለምአቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ህይወት እምሻው እንደገለጹት ድርጅቱ በአፋር ክልል እና በሶማሊያ ክልል አስፈላጊውን እርዳታ ሲያደርግ እንደነበር ገልጸው በአሁኑ ወቅትም በቦረና ዞን በድርቅ ለተጎዱ ህፃናት እና እናቶች አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ የኦሮሚያ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ገንዘብ የማሰባሰብ ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የዓለምአቀፉ የህጻናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24