Get Mystery Box with random crypto!

የተባበሩት መንግስታት የኑክሌር ተቆጣጣሪ በሊቢያ 2.5 ቶን ዩራኒየም መጥፋቱን አስታዉቋል፡፡ በጦር | AHADU RADIO FM 94.3

የተባበሩት መንግስታት የኑክሌር ተቆጣጣሪ በሊቢያ 2.5 ቶን ዩራኒየም መጥፋቱን አስታዉቋል፡፡
በጦርነት በምትታመሰው ሊቢያ ውስጥ በአንድ ጣቢያ ውስጥ የተከማቸ 2.5 ቶን የተፈጥሮ ዩራኒየም ጠፍቷል ሲል የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ገልጻል።

የመንግስታቱ ድርጅት የኑክሌር ተቆጣጣሪ ተቋም ባውጣው መግለጫ አሁን ከሊቢያ የጠፋው ግዙፍ መጠን ያለው ዩራኒየም የራዲዮአክቲቭ አደጋ የሚያስከትልና የፀጥታ ስጋት እንደሆነም ነው ያስታወቀው፡፡

እንደ ዓለማቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ተቋም ሪፖርት ከሊቢያ መጥፋቱ የተነገረለት የተፈጥሮ ዩራኒየም መጠን በግምት 2 ነጥብ 5 ቶን እንደሚሆን ያሳያል፡፡

ይኸው ጠፍቷል የተባለው የተፈጥሮ ዩራኒየም መጥፋቱ የተገለጸው በመንግስት ቁጥጥር ስር ካለው ስፍራ ሳይሆን ከሌላ አካባቢ መሆኑንም ነው የዓለማቀፉ የአቶሚክ ሀይል ተቆጣጣሪ ተቋም ያስታውቀው፡፡

በቪየና የሚገኘው አለም አቀፍ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ባወጣው መግለጫ ላይ ዋና ዳይሬክተሩ ራፋኤል ማሪያኖ ስለጎደለው ዩራኒየም ለአባል ሀገራቱ ማሳወቃቸዉን ጠቅሷል።
የተቋሙ ዋና ኃላፊ በሰጡት ማብራሪያ የጠፋውን ዩራኒየም የማፈላለጉና የምርመራ ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

ሮይተርስ በመጀመሪያ ስለጠፋው የሊቢያ ዩራኒየም የማስጠንቀቂያ ዘገባ ሰርቶ እንደነበር የፎክስ ኒዉስ ዘገባዉ አስታዉሷል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24