Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ከ26 ወራት በኃላ ወደ ህንድ አባሳደሯን ልትልክ ነዉ፡፡ የተከፋፈለው የአሜሪካ ሴኔት ረ | AHADU RADIO FM 94.3

አሜሪካ ከ26 ወራት በኃላ ወደ ህንድ አባሳደሯን ልትልክ ነዉ፡፡

የተከፋፈለው የአሜሪካ ሴኔት ረቡዕ መገባደጃ ላይ የሎስ አንጀለስ ከንቲባ የነበሩት ጋርሴቲ በህንድ የአሜሪካ አምባሳደር መሆናቸዉን 52 ለ42 በሆነ ድምጽ አረጋግጧል፡፡
አሜሪካ በህንድ ውስጥ የአምባሳደርነት ስራዋን ለ26 ወራት ባዶ አድርጋ ትታዉ መቆየቷን ያስታወሰዉ ዘገባዉ ይህም በህንድና በአሜሪካ ግንኙነት ዉስጥ ያለ አባሳደር ግንኙነት የቆየ ረጅሙ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ክፍተቱ የመጣው ዓለም አቀፋዊ ውጥረት እየጨመረ በሄደበት ወቅት ነው፡፡ ምንም እንኳን የአሜሪካ እና የህንድ መሪዎች ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የቅርብ አጋር ሆነናል ቢሉም ያለ አባሳደር ሹመት 26 ወራት ግኙነታቸዉ ቀጥሎ እንደነበር ይጠቀሳል፡፡

የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ባለፈው አመት ለጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እንደተናገሩት “በምድር ላይ ካሉን በጣም ቅርብ ከሆኑት ወዳጆቻችን መካከል ህንድ ቀዳሚዋ ናት ማለታቸዉ ይታወሳል።
ህንድ በሕዝብ ብዛቷ በዓለማችን ከሚጠሩ ሀገራት መካከል ናት፡፡ አሜሪካ ደግም ብዙን ጊዜ በእስያ በምታደርገዉ ቅኝት ህንድን ከ2 ሺ ማይል በላይ ድንበር ከምትጋራት ቻይና ጋር እንደ አንድ የምሽግ ስፍራ አድርጋ ትቆጥራታለች ነዉ የሚባለዉ፡፡
ዘገባዉ የኤን ፒ አር ነዉ፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24