Get Mystery Box with random crypto!

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች መሰረታዊ ችግር ጋር ተያይዞ በመግለጫዉ ያነሳዉ ሀሳብ ሀላፊነት እ | AHADU RADIO FM 94.3

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች መሰረታዊ ችግር ጋር ተያይዞ በመግለጫዉ ያነሳዉ ሀሳብ ሀላፊነት እንደወሰደ የሚያሳይ ነዉ ሲሉ ፓርቲዎች ገለጹ፡፡
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ከፓርቲዎች ጋር ተያይዞ እያጋጠሙ ያሉ ተፅእኖችን እንዴት መፈታት እንደሚገባ በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡

አሀዱም በተለይ የተፅእኖዉ ሰለባ የሆኑ ፓርቲዎችን ያነጋገረ ሲሆን የእናት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ያየህ አስማረም ዋና ሰብሳቢዋ በተለይ ድርጊቱን የፈፀሙት ተጠያቂ እንዲሆኑና ፍትህ ሚኒስቴር ክስ እንዲመሰርት ማለታቸዉ ፤ድርጊቱ በመንግስት ሀይሎች የሚፈፀም ነዉ ብለዉ መሬት ላይ ያለዉን ነባራዊ እዉነት ማንሳታቸዉ ጥሩ ጅማሮ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የባልደራስ ለእዉነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር በቃሉ አጥናፉ በበኩላቸዉ በተለይ ከመሰብሰቢያ አዳራሽ አንፃር የከዚህ ቀደም ጥያቄያችን በምርጫ ቦርድ መሰብሰቢያ አዳራሽ በአማራጭነት መቅረቡና ቦርዱ ይህን ማመቻቸቱ ለዚህም ምላሽ መሰጠቱ ተገቢነት ያለዉ በመሆኑ ፓርቲያችን የሚቀበለዉ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አንዱ ሀላፊነቱ በፓርቲዎች መካከል የሚፈጠሩ ችግር መፍታት በመሆኑ የጀመረዉን ሂደት እንዲሁም በመግለጫዉ የተቀመጡት ዉሳኔዎች እንዲፈጸሙ በተለይም ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንዲችልም ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል፡፡

አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24