Get Mystery Box with random crypto!

አሜሪካ ከኢትዮጲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ቅድመ-ሁኔታዎች መሟላት እንደሚኖርባቸው የአሜሪካ | AHADU RADIO FM 94.3

አሜሪካ ከኢትዮጲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ቅድመ-ሁኔታዎች መሟላት እንደሚኖርባቸው የአሜሪካ መንግስት አስታወቀ፡፡
ይህንን ያሉት የአሜሪካ መንግስት ቃል-አቀባይ ቢሮ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ ሲሆኑ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በተያዘው ሳምንት በኢትዮጲያና በኒጀር የሚያደርጉትን ጉብኝት በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ መሆኑን ቢሮው ለአሃዱ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የቢሮው ረዳት ጸሃፊ ሞሊ ፊ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የሰሜኑ ጦርነት እልባት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ሰፊ ስራ አሜሪካ መስራቷን በውቅቱ ገልጸው በነገዉ እለት ወደ ኢትዮጲያ የሚያደርጉት ጉዞም ከሰላም ስምምነቱ በኋላ የተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን ለመመልከት ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
ከሰላም ስምምነቱ በኋላ አሜሪካ ከኢትዮጲያ ጋር የሚኖራት ግንኙነት የአፍሪካ ነጻ የንግድ ተጠቃሚነት ወይንም ‹‹አጎዋ››ን ጨምሮ ወደ ቀድሞው መደበኛ ግንኙነት የመመለስ እድል አለው ወይ በሚል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄም ረዳት ጸሃፊው ‹‹ፊ››አሜሪካ ከኢትዮጲያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ ቅድመ-ሁኔታዎች መሟላት እንዳለባቸው ነዉ ምላሽ የሰጡት፡፡
አሜሪካና ኢትዮጲያ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት ያላቸው ሃገራት ቢሆኑም ግንኙነት ለማደስ ግን ኢትዮጵያን ለአስርት አመታት ወደ ኋላ እየጎተታት ያለዉን በተለያዩ አካባቢዎች የሚስተዋሉትን የብሄር ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ሊቆሙና መረጋጋትም ሙሉ በሙሉ ሊሰፍን ይገባል ነው ያሉት፡፡
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ነገ ረቡ በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝትም በዋነኝነት የሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት ላይ የሚያተኩር ነው ያሉት ረዳት ጸሃፊው የሁለቱን ሃገራት ግንኙነትም ያድሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ አክለዋል፡፡