Get Mystery Box with random crypto!

የስነ-ህዝብ ትሩፋትን የተመለከተ አዲስ ጥናት በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡ በአንዲት | AHADU RADIO FM 94.3

የስነ-ህዝብ ትሩፋትን የተመለከተ አዲስ ጥናት በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡
በአንዲት ሃገር ውስጥ ያለውን የህዝብ ብዛት መጠን ከግምት ባስገባ መልኩ ምጣኔ ሃብታዊ ጥቅምን ለማረጋገጥ የሚነደፉ ስትራቴጂዎችን ያካተተው የስነ-ህዝብ ትሩፋት ጽንሰ-ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ሃገር አቀፍ የህዝብ ቆጠራ መካሄድ እንዳለበት መገለጹ ይታወሳል፡፡ በቀጣዮቹ ሳምንታት የሚጀመረው ጥናትም ኢትዮጲያ በምን መልኩ የስነ-ህዝብ ትሩፋትን በአግባቡ ማግኘትና ተጠቃሚ መሆን ትችላለች የሚለውን ለመመለስ ያለመ እንደሆነ ለአሃዱ የገለጹት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር የስነ-ህዝብ ዘርፍ የቴክኒክ አማካሪው አቶ ተፈሪ ደገፋ ናቸው፡፡
ጥናቱ እያንዳንዱ የመንግስት ሴክተር ያለበትን ስራና ሃላፊነት ከመለየት ባለፈ አዳዲስ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን በውጤትነት ይዞ ይወጣል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጹት አማካሪው ጥናቱ በዋነኝነት በፕላንና ልማት ሚኒስቴር እንደሚከናወንም ተናግረዋል፡፡
ይህንን ጽንሰ-ሃሳብ ተግባራዊ ከሚያደርጉ የእስያ ሃገራት መካከል ደቡብ ኮርያ በዋነኝነት እንደምትጠቀስ ገልጸው ኢትዮጵያም ተሞክሮውን በመውሰድ ጥናቱን አጠናቅቃ ጽንሰ-ሃሳቡን ተግባራዊ ማድረግና ያላትን የህዝብ ምጣኔ ለልማት ማዋል ይኖርባታል ሲሉም ገልጸዋል፡፡
የጥናቱ ዋነኛ ባለቤት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ቢሆንም የተባበሩት መንግስታት የስነ-ህዝብ ፈንድ ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያደርግም አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24