Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት እና በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያ | AHADU RADIO FM 94.3

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት እና በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በተከሰተው ድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተደረገውን እርዳታና ያለውን ችግር በማጥናት ይፋ መደረጉ ተገለጸ፡፡
በሰው ሰራሽ እንዲሁም በተፈጥሮአዊ አደጋዎች ምክንያት በዜጎች ላይ በሚደርስ ችግር አማካኝነት በሚደረገው የደጋፍ አቅርቦት ፍትሃዊነት ላይ ጥናትና ክትትል በማድረግ ችግሮቹ እንዲፈቱ ምክረሀሳብ እንደሚቀርብ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር በደል መከላከል ዳይሬክተር አቶ አዳነ በላይ ተናግረዋል፡፡
በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት አማካኝነት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሚደረገው የእርዳታ አቅረቦት ምንይመስላል የሚለውን በመከታተል ያለውን ሁኔታ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ መቻሉንም ጠቁመዋል፡፡
በተፈጥሮአዊ የድርቅ አደጋ ምክንያት በሶማሌ ክልል በሚደረጉ የእርዳታ አሰጣጦች ላይ የሚመጡ ቅሬታዎችን ተከተሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጥ ማድረግ የቻሉበት ሁኔታም እንደነበር ጠቅሰዋል፡፡
ይህንን የተለየ ችግር ለሚመለከተው አካል ማቅረብ በሚያስችለው ረገድ መክረሀሳብ በማቅረብ ጭምር በትብብር እንደሚሰራም ነው ዳይሬክተሩ የሚናገሩት፡፡
በመሰረታዊነት ወቅታዊ የሰው ሰራሽ እና ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ተከትለው የሚታዩ ችግሮችን በማጥናት መፍትሄ እንዲበጅላቸው እንደሚሰሩም አመላክተዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahaduradio
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang