Get Mystery Box with random crypto!

የአይ ኤስ ሀይሎች በኢራቅ በፈጸሙት ጥቃት የኢራቅ ፖሊሶችን መግደላቸው ተነግሯል፡፡ የአይ ኤስ ሀይ | AHADU RADIO FM 94.3

የአይ ኤስ ሀይሎች በኢራቅ በፈጸሙት ጥቃት የኢራቅ ፖሊሶችን መግደላቸው ተነግሯል፡፡
የአይ ኤስ ሀይሎች በሰሜናዊ ኢራቅ በፈጸሙት ከባድ ጥቃት ዘጠኝ የኢራቅ ፖሊሶችን መግደላቸው ታውቋል፡፡
የኢራቅ ፖሊስ ሀይል አባላት የሚጓዙበት ተሸከርካሪ መንገድ ዳር በተጠመደ ፈንጂ በተመታበት ቅፅበት የአይ ኤስ ታጣቂ ሀይሎች የእረምታ ተኩስ ከፍተው ከባድ ጥቃት መፈፀማቸው ነው የተነገረው፡፡
በዚያ የታጣቂዎቹ ጥቃትም ዘጠኝ የፌደራል ፖሊስ ሀይል አባላት መገደላቸው ነው የተሰማው፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው በኪርኩክ ግዛት ነው የኢራቅ የፌደራል ፖሊስ ሀይል ሀላፊ በሰጡት ማብራሪያ በኢራቅ ሰሜናዊ ክፍል የአሸባሪዎቹ አይ ኤስ ሀይሎች እንቅስቃሴ መጠናከሩን አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ዘ ዲፌንስ ፖስት ነው፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቴሌግራም፡- https://t.me/ahadutelevision
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en
አሐዱ ራድዮ 94.3 እና ቴሌቪዥን #አሐዱ_24 #Ahadu_News_24 #News_24 #Ahadu #News