Get Mystery Box with random crypto!

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የጥቅም ግጭት ሲፈጠር፣ የሚፈታበትና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚ | AHADU RADIO FM 94.3

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ የጥቅም ግጭት ሲፈጠር፣ የሚፈታበትና አስተዳደራዊ እርምጃዎች የሚወሰድበት ሥርዓት በራሳቸው እንዲፈጥሩ የሚያስገድድ መመሪያ መውጣቱ ተገለፀ።
በኢትዮጵያ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ፀድቆ የወጣው መመርያ፣ በድርጅቶቹ ውስጥ ከጥቅም ግጭት ጋር በተያያዘ፣ የድርጅቱ አባላት የሆኑ የሥራ መሪዎች፣ ሠራተኞች፣ ሌሎች አካላት አቤቱታ ሲያቀርቡ፣ የሚያጣራ ውሳኔ ሰጪ አካል እንዲያቋቁሙ የሚያዝ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካው ሞላ ለአሀዱ ተናግረዋል፡፡
የተወሰኑ የሲቪል ማኅበራት ሥርዓት ዘርግተውና ፖሊሲ አውጥተው ሲተገብሩ እንደነበረ አስታዉሰዉ አብዛኛው ግን ከዚህ ጋር በተያያዘ የዳበረ ሥርዓት አልነበራቸውም ብለዋል፡፡
የሲቪል ማኅበራቱ በውስጥ አሠራራቸው እርምጃ የሚወስዱበትን አግባብና አጠቃላይ የተወሰደውን እርምጃ ለባለሥልጣኑ እንደሚያሳዉቁ ገልጸዋል፡፡
የሲቪል ማኅበራት ሠራተኞች ከራሳቸው የግል ጥቅም ይልቅ የድርጅቶችን ተቋማዊ ጥቅም አስቀድመው መሥራት እንዳለባቸው ኃላፊነት የሚጥል መመርያ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በራሱ መንገድ ተገዥ የሆነ የሲቪል ማኅበር ድርጅት መፍጠር የባለሥልጣኑ ዋነኛ ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ድርጅቶቹም ተገቢ ምርመራ ካላካሄዱና ውሳኔ ካልሰጡ፣ ባለሥልጣኑ በራሱ መርምሮ ውሳኔ ሊሰጥ እንደሚችል አቶ ፋሲካዉ አክለዉ ተናግረዋል፡፡
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ድህረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/ahadutelevision
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ትዊተር፦https://twitter.com/ahadu_radio?lang=en